spot_img
Sunday, October 1, 2023
Homeነፃ አስተያየትበአብይ መንግስት የተፈጀው አማራ፣ 500 ሺ አለፈ (ደብሩ ነጋሽ~ ሃኪም)

በአብይ መንግስት የተፈጀው አማራ፣ 500 ሺ አለፈ (ደብሩ ነጋሽ~ ሃኪም)

advertisement

የአዘጋጁ ማስታወሻ ፡ ባለፉት ጥቂት ቀናት በወለጋ አካባቢ በአማራ ተወላጆች ላይ አዲስ ጥቃት ተከፍቶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃኖች ማለቃቸውን በማህበራዊ ድረ ገጽ የሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ ሆኖም ድርጊቱ በአብይ አህመድ መንግስት የተቀናብረ ነው ለማለት የሚያስችል ተጨባጭ ማስረጃ እስካሁን ድረስ ለህዝብ እልደረሰም፡፡ ከታች ባለው ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከና ድረገጽን አቋም እንደማያንጸባርቁ ውድ እንባቢያንን በትህትና እናስታውቃለን፡፡

በአብይ መንግስት የተፈጀው አማራ፣ 500 ሺ አለፈ
በደብሩ ነጋሽ~ ሃኪም
ነሃሴ 19 2013 ዓ ም

 ወያኔ ትግሬ፣ ያማራን ‘ክልል’ ሲወርር ፣ ኦነግም በወለጋ፣ ያልታጠቀን  አማራ መፍጀት ተያያዘው ። በአብይ ዘመነ መንግሥት፣ ኦነግ የፈጀው  አማራ፣ ከግማሽ ሚሊዎን ላቀ። የጸረ~አማራው ዘመቻ ፣ በኦሮሞ  ልሂቃንም ሁሉ የተደገፈ ነው። አባገዳዎቻቸው መቀሌ ለመሸገ ወያኔ፣  ገጸ~በረከት ሲያቀርቡ፣ በመሃላቸው የሚኖርን ያልታጠቀን አማራ፣ ኦነግ  ነፍሰ~ጡርና እመጫትን ሲጨፈጭፍ፣ ሊያወግዙ ቀርቶ አላዘኑም።  

ከጠ/ሚ እስከ መከላከያ ሚኒስቴር፣ እስከ ጦር አበጋዞች እና አየር ኃይል  አዛዥ ኦሮሞዎች ናቸው። የገነገነው የአማራ ፍጅት፣ የኦሮሞው  መንግስት አላማ መሆኑን የሚጠራጠር፣ አስመሳይ ወይ ደነዝ ነው። 65  000 የአማራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም በግፍ ሲባረሩ፣ ያማራ ሴት  ልጆች ከሁለት አመት በላይ ሲታገቱ ፣ አንድ ወንጀለኛ ለፍርድ  ያልመቅረቡ፣ የፌደራሉም ሆነ የክልሉ መንግስት፣ እንዲሁም የአማራ  መንግስት ተብዬው ተባባሪነት፣ አያጠያይቅም።  

 የአብይ ‘’ብልጽግና’’፣ ጸረ~ተዋህዶና ጸረ~አማራ ነው። የብዙሃን  የኢትዮጵያውያን ዕምነት፣ ተዋህዶና እስልምና፣ ናቸው። 95 በመቶው  አማራ፣ የተዋህዶ፣ የእስልምና ፣ የአይሁድ እምነት ተከታይ ነው። ዛሬ  በወለጋው አማራ፣ የግፍ ግፍ የሚፈጽመው የኦነግ መንግስት ነው።  አመራሩም፣ ‘ጴንጤ’ ነው፣ በስም ። በድፍን ኢትዮጵያ አማራ ሲፈጅ፣  መንግስት ሊታደገው፣ ሊያጽናናው ቀርቶ፣ባደባባይ ማዘን ከልክሎታል።  

 አውሮፓ የሚኖሩ አይሁዳውያን፣ ዛሬ በማንነታቸው ስጋት  ስለገባቸው ፣ ልዩ የመታጠቅ መብት ተስጥቷቸዋል። አማራው ግን  በመሰረታት፣ ባቆማት፣ ባቀናት ፣ ለ50 ሺ ዘመናት በኖረባት እናት  አገሩ፣ መጤዎች ትጥቅ አስፈትተው ሲፈጁት፣ አለን አያሰኝም።  

 በጣልያንና በደርግም፣ ኦነጋውያን አማራን ፈጅተዋል። 

 የደርግ ኦነጎች፣ አማራውን በነቂስ ትጥቁን አስፈትተው፣ በመሃይምኑ  ሰራዊትና አጋሮቻቸው አስጨፍጭፈውታል። በጣልያንም ግዜ፣ በጂማ፣ 

በሃረር ፣ ወዘተ፣ እነአባጆቢርን መሰል ኦሮሞዎች፣ እንደ ዛሬ የአማራን፣  ሴቶችና ህጻናትን እንኳን አልማሩም። ወያኔና ኦነግ ጦርነት ያወጁበት  አማራ፣ ደርግ ትጥቁን ያስፈታውን ነው።  

የአብይ መንግስት፣ ከነትጥቁ አገር ያስገባው ኦነግ በወለጋ የዘር መፍጀት  ስራ የገባው፣ የክልሉ ‘መንግስት’’ አማራውን ትጥቅ አስፈትቶለት ነው።  ወያኔና ኦነግ፣ በነደፉት ህገ~መንግስት መሰረት፣ አማራን ከማጥፋት  አላማቸው ዝንፍ አላሉም። የወያኔና የሱዳን ወረራ፣ አጋጣሚ አደለም።  አማራው የተጋረጠበት አደጋ፣ ደጋግሞ የተከሰተ ነው። 

ዛሬ ከጠ/ሚ እና መከላከያ ሚኒስቴሩ እስከ ምርኮኛ የአስር አለቃ ጦር  አበጋዝ፣ ብርሃኑ ጁላ፣ ኦነጋውያን ናቸው። ስለሆነም ፣ በብቃትም ሆነ  በኢትዮጵያዊነት አይታሙም። ከሃዲው ወያኔ ትግሬ ያቋቋመውና ኦነግ  የተረከበው ሰራዊት፣ በጸረ~ኢትዮጵያነት ፣ በጸረ~አማራነት የተሞረደ  

ነው። ምርኮኞቹ ኦነጎችማ፣ እነ አባዱላን፣ በአማራ ደም ጨቅይተዋል።  

የኦነግ አመራር፣ በዘረኞችና፣ ጸረ~ተዋህዶ፣ ጸረ፟~ኢትዮጵያ ባዕዳን  የሚደገፍ ነው ። ኦነግ የጀርመን ፕሮቴስታንትችና እስላም ነን በሚሉ  ጥቁር~ጠል አረቦች አዕምሮ የተቃኙ ፣ ራስ~ጠል ናቸው። የኦነግ የነፍስ  አባት ጀርመኖች፣ 6 ሚሊዎን አይሁዶችን ‘’ከመገላገላቸው’’ በፊት፣  80 000 ሄሬሮዎች (ናሚቢያውያን) በመግደል እጃቸውን ያሟሹ  ነበሩ። ለኦነግ ምጽዋት የሚወረውሩት አረቦችም፣ አባ ጅፋር ከሚሊዎን  በላይ ኦሮሞና ሌሎችን ፈንግሎ ፣ ለባርነት የሼጣቸው ናቸው።  

አማራ፣ ኦነጋውያንን እና ከሃዲ ትግሬን፣ ከባርነት የታደገ ህዝብ  ለመሆኑ፣ ታሪክ ይመሰክራል። በ 1929 አመተ ምህረት ከ 25 000  አርበኞች፣ 23 500 አማራ ነበር። ከቀሪው 1500 ሲዳማው አብላጫው  ሲሆን፣ ቀጥሎ ኦሮሞ፣ ጉራጌ አፋር ሶማሌ ወዘተ ነበሩ። አንድም  የትግሬ አርበኛ አልነበረም። አንድ ሚሊዎን ከተገመተው ፣ በፋሽስት  ከተፈጀው ኢትዮጵያዊ ፣ 90 በ 100 አማራ ነበር። ያዚያ ጌታ፣ ዛሬም  ትልቁን ያገሪቱ ግብር ከፋይ ሁኖ ፣ ላለፉት 30 ዘመናት በማንኛውም  ፈርጅ፣ የሰው በታች እንዲሆን ተፈርዶበት ቆይቷል። ያ ሳያንስ 

በህልውናው ተዘመተበት ። አስራት ወልደየስን የመሰለ ሊቅ፣ አስማረን፣  ጎቤን፣ አሳምነውን የመሰሉ ልጆቹን ጠላት ነጥቆታልም።  

የኦሮሙማው ፋሽስት ስርዐት ፣ አፍጥጧል አግጥጧል  

አማራው የተቀማ ነጻነቱን ፣ የተደፈረ ማንነቱን የሚያስከብረው  ሲደራጅ ብቻ መሆኑ ቢዘገይም ተገልጦለታል። የኦሮሙማው  ጸረ~ኢትዮጵያዊያ መንግስት፣ በሶስት አመታት ብቻ፣ ግማሽ ሚሊዎን  አማራ ያለከልካይ ፈጅቷል። የ 50 ሺ ዘመናት በኢትዮጵያ ኗርነቱ፣ ልዩ  የደም ገጽታ የሚታይበት አማራ፣ ዛሬ መጤ ተብሎ የሚገድለው፣ ከ  450 አመታት ወዲህ በወረሩ ፣ ነፍሰ~ጡርና እመጫት ማረድ ወጋቸው  በሆኑ፣ አረመኔ ብቻ የማይገልጻቸው ፍጡራን ነው።  

ለሺህ አመታት የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ልሳን የሆነውን አማርኛንም፣  ለማጥፋት ዝተዋል። ኦሮምያ በሚባለው፣ በወረራ በተያዘው የሚኖረው  30 ሚሊዎን በላይ ኢትዮጵያዊ ፣ በአማርኛ የመማር፣ የመገልገልን  መብት ከተነፈገ፣ 30 አመት ሞላው ።  

አዲስ አበባ የተቆረቆረችው፣ የሺ ዐመት ኮኦሮሞ በፊት ነው  ቅርስ ያማያውቁ ፣ ማጥፋት እንጂ መስራት የማይችሉ ወራሪዎች፣ የኛ  በሚሏት አዲስ አበባ ያሉን ቅርሶች እያፈረሱ ነው። የሸዋ አዲስ አበባ፣  አማሮች ቆርቁረው ውቅር ቤተክርስቲያናት ያነጹባት፣ ከ 1500 አመት  በፊት ነው። የኦነግ ምንጅላቶች፣ የሲዳሞንና የባሌን ድንበራችንን  ከመጣሳቸው ከ 1000 አመት በፊት ነበር። ከግራኝ ወረራ በፊት፣  በአለም ድንቅ ከተሞች አንዷ ነበርች ። ዛሬ 85 በመቶ የአዲስ አበባ  ነዋሪ፣ አማርኛ ተናጋሪ ነው። 60 በ 100 ደግሞ አማራ ነው። ኦነጎች  ሊያወድሟት ያስፈሰፉባት ጥንታዊ ከተማ፣ ‘’የሁላችን ናት’’ ስላሉ ነው  እነ እስክንድርን፣ አብይ ዘብጥያ የወረወረው። አዎ ያሰራቸው  የባልደራስ አመራር፣ እንዳሉ አይበገሬ አማሮችም ናቸው።  

 ጡትና ብልት መስለብ መገለጫው የሆነው ኦነግ፣ ያብዬን ወደ እምዬ  ብሎ፣ አማራን ወንጅሎታል። የገትሩትን የጡት ሃውልት ፣ ኦነጉ አብይ  እንዳስገነባው፣ ወገን ልብ ሊል ይገባል። የበታችነታቸው 

የሚያበሳጫቸው ወራሪዎች፣ በረቂቋ ጥንታዊ ኢትዮጵያ ይቀናሉ።  ብቸኛ አኩሪ የጥቁር ህዝብ የግዕዝን ፊደል፣ በፈረንጆ ፊደል ለመተካት  ይታትራሉ። አማርኛን በቋንቋቸው ካልተካን ይላሉ። ኦሮሚፋ፣ አንተና  አንቺን አይለም። ለቀናት፣ ለወራት፣ ለማዕዘን ፣ ላቅጣጫ፣ ለስሜን፣  ለደቡብ፣ ለምስራቅ፣ ለምዕራብ ወዘተ ቃላት ሊኖሩት ቀርቶ፣ ጽንሰ  ሃሳቡ የለም። ለሰዐት፣ ለደቂቃ፣ ላፍታ (second)፣ ቃላት የለውም።  ደፋር ደንቆሮዎች!!  

አማራው ምን ማድረግ አልበት  

አማራው የተቀማ ነጻነቱን ፣ የተደፈረ ማንነቱን የሚያስከብረው  በእልህና በቁጭት ሲደራጅ ብቻ መሆኑ፣ ቢዘገይም ተገልጦለታል።  አብን እና ፋኖ ግፍ የወለዳቸው የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው ።  ያማራው አደረጃጀት፣ ለአማራና ለኢትዮጵያ ሁሉ መድህን ነው።  የመሃል አገሩ የፋኖ ድርጅት ፣ የተበተነውን፣ በዳር አገር ያለ አማራና  ሌሎችንም ኢትዮጵያውያን ይታደጋል። የተደራጀ አማራ፣ ለተገፉ  ኢትዮጵያውያን ሁሉ ተገን ነው። ጨፍጫፊውን ኦሮሙማን ፣ ወግድ  ሊል የሚችል የተድራጀ አማራ ነው። ከሩስያውያን ትምርት  እንውሰድ። ሶቪየት ስትበታተን፣ ሩሲያውያን በየተለያዩ ሀገሮች  ኑሯቸውን በመቀጠላቸው፣ ኦነግን መሰል አረመኔዎች፣ ያጠቋቸው  ጀመር። ሆኖም ሩስያ፣ አዲሶቹን መንግስታት በማስጠንቀቅዋ፣ ዛሬ  ሩስያዊ በያለበት ተከብሮ ይኖራል። አማራ ወራሪን አያሥታምምም።  

‘’አላርፍ ያለች ጣት ፣ ‘ምን’ ጠንቁላ ትመጣለች’’ እንዲሉ  አረቦች፣ አውሮጳን ወረው ለ800 ዘመን ከተንሰራፉበት ማማ፣  በእስፓኒሽና ፖርቱጊዞች ያባረሯቸው ፣ በመጤነታቸው ነበር። በ450  ዐመት ያልለዘበ የኦነግ አረመኔነት ‘’ዕርስት በ ሺ አመቱ ለባለቤቱ’’  እንላለን። አሻፈርኝ ካሉም፣ ‘ጅብ ከሚበላህ፣ በልተሀው ተቀደስ ‘ ነው።  

ደብሩ ነጋሽ፣ 52 ዘመዶቹ በአማርነታቸው፣ ኦነግ ሃረርጌ የጨፈጨፈበት  የቀድሞ የአለም መንግሳታት ሃኪም ነው።

_
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,718FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

1 COMMENT

  1. ዶክተር ደብሩ ነጋሽ ሽክን ባለ አቀራረብ እውነቱን ቁልጭ አድርጎ ገልጾታል::ሐቁ ይህ ነው:: ዐማራው ህልውናውን ለማስጠበቅ አምሮና ታሪክን መሠረት አድርጎ መሮ መታገል አለበት::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here