spot_img
Wednesday, June 7, 2023
Homeነፃ አስተያየትበዓለም ማህበረሰብ ስም በሚጎሰም ጫጫታ ኢትዮጵያ አትፈርስም።

በዓለም ማህበረሰብ ስም በሚጎሰም ጫጫታ ኢትዮጵያ አትፈርስም።

- Advertisement -

በ ሰማነህ ታምራት ጀመረ
ዖታዋ፤ ካናዳ
ጥቅምት 1 2014 ዓ ም

የዓለም ማህበረሰብ የሚባለው በዘልማድ የተባበሩት መንግስታት አባል ሃገራትን ማለት እንደሆነ እንገነዘባለን። በገሃዱና በስውር ግብሩ የምናውቀው የዓለም ማህበረሰብ ግን ኮለኔል መንግስቱ እንዳሉት የኢምፔሪያሊዝም ቁንጮው አሜሪካን እና በG-7 የተካተቱ ሃገራት ናቸው። ያለመሸፋፈን የዓለም ማህበረሰብ ብሎ ነገር በሐቅም፤ በገቢርም የለም። በአመክንዮ የሚአስተባብል እስኪመጣ አባባሉን እንፈትሽ።

አሜሪካ የአዲሱ ዓለም ስርዓተ ማህብር ፈጣሪ ነኝ ብላ ታምናለች። ስርዓቱም በእርሷ አስተሳሰብ፤ እምነት አና የውሸት ማደናገሪያ እንዲቀረፅ ብዙ ለፍታለች። ግራቀኝ፤ ውሸትእውነት፤ ሰሜንደቡብ ነው እያለች በመስበክ ከእውነትና ከሕግ በላይ ሆና ዓለምን ታምሳለች። በአመክንዮ እና በፍቀር ሳይሆን በሃብትና በጉልበት ገዝታ ለርሷ ሎሌ የሚአደርግ ስርዓተ ማህበር ቀርፃለች። ዓለምን እንደ እንዝርት አሽከርክራለች።

የሃሳብ፤ የርዕዮተ ዓለምና የእምነት ነፃነት አከብራለሁ፤ በዴሞክራሲ መርህ እገዛለሁ እያለች የሌሎችን ነፃነትና የፖለቲካ እምነት አጥብቃ ትቃወማለች። ከርሷ እሳቤና ርዕዮተ ዓለም ውጪ የሆነውን ሁሉ ታወግዛለች። ሩሲያና ቻይና በኮምኒስት ዕርዮተ ዓለም ስለተመሩ ብቻ የዓለማችን እርኩስ ሃገር አስመስላ ስላቸዋለች። ቢቻላት እነዚህን ሃገራት ከምድረ ገፅ ብታጠፋ ደስባላት። ከንዚህ ሃገራት ጋር የፖለቲክ፤ የኢኮኖሚ፤ የማህበራዊ፤ የፀጥታና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላቸውን ሃገራት ሁሉ በተጓዳኝ ጨፍለቃ ታሳድዳለች። ቀንደኛ ጠላት አርጋ ስለሳለቻቸው ባገኘችው አጋጣሚ  እነዚህን ሃገራት ሁሉ ትበጠብጣለች። በአፈጋሃኒስታን፣ ቸችንያ፤ የቀድሞው ሶቭየት ሕብረት፤ ታይዋን፤ ሰሜን ኮርያ፤ ኢትዮጵያ፤ ቬትናም እና ኩባ ላይ የፈፀመቻቸው አጉራ ዘለል ተግባራት ጉልህ ማሳያ ናቸው:: 

አሜሪካ ዴሞክራሲ፤ የሕግ የበላይነት፤ የሰው ልጅ መብትና ፍትሕ አስጠባቂ ነኝ እያለች በአደባባይ ትኮፈሳለች። እርሷ ግን ዜጎቿንና አናሳ ብሄሮቿን ታስራለች፤ ሰብዓዊነት በጎደለው ሁኔታ ታሰቃያለች። የ2020 ሰብዓዊ አያይዛ ራፖሯ የሚነግረን ብዙ እውነታ አለው። ጥቁር አሜሪካዊያን በፖሊስ የመገደላቸው እድል ከነጮች በሦስት እጥፍ ልቆ ይገኛል። ባርነት በአፍሪካ አሜሪካውያን ላይ ባሳደረው ተጽዕኖ ምክንያት አባት አልባ ወጣቶች፣ የትምህርት መቋረጥ፣ የሱሰኝነት እና የማንነት ቀውስ በሃገሪቱ ስፍኖ እስከ ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ዘልቋል። በአሜርካ ጥቁር ሆኖ መወለደ ወንጀል እስኪመስል ድረስ በጥቁር አሜሪካኖች ላይ ዘግናኝ ግፋ ትፈጽማለች። በጓንታናሞ እና አፈጋሃኒስታን እስረኞችን ኢ-ሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ አሰቃይታ ገላለች፤ አንገላታለች፤ ዝግናኝ የሆነ ፆታዊ ጥቃት ፈጽማለች። 

የአሜሪካ የሃብትና የስልጣን ድልድል ሲታይ በአብዛኛው አቃፊነትና አሳታፊነት የጎደለው ነው። ከብዙ በትቂቱ ስናይ በ2016-2017 የመጀመሪያዎቹ 10 ሃብታም የሚባሉ ዜጎቿ ሁሉም ነጮች ሆነው እናገኛቸዋለን። ከአሜሪካ ኮንግሬስ አባላት ውስጥ 90% የሚሆኑት ነጮች ናቸው። ከአሜሪካ እስቴት (ክፍለ ሃገር) አስተዳዳሪዎች ውስጥ 96% በንጮች የተያዘ ሲሆን ከፍተኛ የመከላካያና ሕዝብ ደህንነት አማካሪዎች ሙሉ በሙሉ (100%) ነጮች ናቸው። የአሜሪካ ፍሪደም ካውከስ አባላት 96% በነጮች የተያዘ ነው። ከሃገሪቱ የሕዝብ ቁጥር ውስጥ 12% የሚሆኑት ጥቁር አሜርካዊያን በሆኑባት አሜሪካ ጥቅሮችን ምንያህል አግልላ እንደምትገኝ አንረዳለን። እኩልነትና አሳታፊነት ያልሰፈነባት አሜሪካ ሌሎች ሃገራትን ሕዝባዊነት  እና አቃፊነት የጎደላቸው እያለች ስትወነጅል፤ ስታወግዝና መአቀብ ስትጥል አለማፈሯ። ለነገሩ አሜሪካና ትህንግ ሃፍረትና ይሉኝታን መቸ ያውቁና። እንደ መአቀብ ሰብዓዊነትና ፍትሐዊነት የጎደለው ስርዓት ምን ሊኖር ይችላል። ተወደደም ተጠላም ይህ ሁሉ ግፍ ተጠራቅሞ ሃገሪቱን የስባዓዊ ጥሰት ቤተመዝክር አርጓታል።

አሜሪካ የዓለምን ማህበረሰብ ስነልቡና በውዳቂ ባህሏ በርዛለች። በሰከነ በሃላቸውና እምነታቸው የጠኑና አንቱ የተባሉ ሃገራትን ወግ ማዕረግ በገንዘብና በመሳሪያ ሃይል እየበረዘች የ245 ዓመት እርካሽ ባህሏን ጭናለች። ውዳቂ ባህሏ እንደጠቃሚ ሸቀጥ የዓለም ገበያን ወሯል። ዓለም የሐቀኞች መሆኗ ቀርቶ የነአስረሽ  ምችው፤ የስራዓት አልበኞችና የአሸባሪዎች መፈንጫ እንድትሆን አሜሪካ ሰፊ አስተዋፅዖ አርጋለች።

የሚገርመው ሃገራት የአሜሪካን የበከተ ባህል ለመቆጣጠር ሲፈልጉ ቀንደኛ ጠላት አርጋ ትፈርጃቸዋለች። ልታጠቃ ስትፈልግ ፀረ-ዴሞክራሲ፤ ፀረ-ሕዝብና ሕገ አራዊት የሚል ታርጋ ትለጥፍባቸዋለች። የምጣኔ ሃብት፤ የጉዞና የዲፕሎማሲ መአቀብ እየጣለች ታስፈራራለች። ይህ አልሆን ሲል መፈንቅለ መንግስት ታሴራለች። አሜሪካ የጥሩ ባህል መፍለቂያ ተምሳሌት ሆና እንድንቀበላት መደረጉ ግን እጅግ ያሳዝናል። 

ከፖለቲካ አንፃር ዓለም አሜሪካን አምኖ ዴሞክራሲና የሕግ የበላይነት ለማስፈን፤ የዜጎችንና የሴቶችን መብት ለማስከበር ጥረት ሲአደርግ ታደናቅፋለች። የሃገራትዴሞክራሲ አሜሪካን  ካልካመሰለ ማጥላላት፤ ማስፈራራትና ማዋረድ ስራዋ ነው። እኔ ካልሁት ውጭ የሚሆን ዴሞክራሲ፤ የህግ የበላይነት፤ የሰብዓዊ መብት መከበር ላሳር ትላለች። ዴሞክራሲ እንደ ሳይንስ ሁሉ ዓለማቀፋዊ ይዘት ያለው መሆኑን እረስታ ዓለም ብርሷ እጀጠባብ ልክ እንዲሆን መሞከሯ የአምባገነንት መገለጫዋ አርጎታል።

ስለሆነም ለሃገሩና ለወገኑ መልካም ስራ የሚሰራን መሪ አሜሪካ በፅኑ ትቃወማለች። እንዲህ ዓይነት መሪ እንዳይኖር አበክራ ትሰራለች። ኢትዮጵያንና ጠቅላይ ሚንስትስለሆነም ዶ/ር ዓብይን የጠመደቻቸው ከዚህ እሳቤ የተነሳ እንደሆነ ሁሉም ኢትዮዮጵያዊ ሊገነዘበው ይገባል። የሃገሩን ጥቅም የሚአስጠብቅ መሪና ሃገር መኖር ማለት የአሜሪካን ጥቅም አያስጠብቅም ብላ ታምናለች። ዓብይን የመሰሉ መሪዎች፤ ኢትዮጵያን የመሰሉ ሃገራት በዓለም መድረክ ታዋርዳለች። አልሆን ሲላት መሰል አስተሳሰብ ያላቸውን ሃገራት አስተባብራ የኢኮኖሚና የፖለቲካ መዓቀብ በመጣል ታሸማቅቃለች። ገፍተው ሲገዳደሯት የውሸት ምክንያት ፈጥራ ትወራለች። ይህንም ስታደርግ በዓለም ህብረተሰብ ስም እየነገደች የራሷን አጉራ ዘለል በሐሪ ታሰርፃለች።  

ረዥም ታሪክ ሳይኖራት ታሪክ ሰሪ፤ ሃይማኖት ሳይኖራት ሃይማኖት ሰባኪ ሆና ትቀርባለች። እርሷ ያልፈጠረችው ሃይማኖት ሃይማኖት አይመስላትም። አሜርካ የይስሙላ ስብከት እየሰበከች በግሏ አሸሸ ገዳሜ ስትል ትውላለች። ይህን የሚቃወም መንግስት እና ሃገር ሲነሳ የህዝቦችን የእምነት፤ የግብረ ስጋ ግንኙነት እና የግለሰብ ነፃነት ተቃዋሚ በሚል ትፈርጃለች። የግብረ ሰዶማዊ ነፃነትን፤ የእዳጣን ማህበረሰቦችን መብት የሚጋፋ መንግስት በሚል በአደባባይ ታበሻቅጣለች። አልሆን ሲላት የኢኮኖሚ መአቀብ ጥላ ለማሽመድመድ ትሞክራለች። አለያም አሸባሪ ብላ በመፈረጅ ወረራ ትፈጽማለች። ከአጋሮቿ ጋር በማበር ከስልጣን ለማስወገድ የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም። ለዚህ የፈረደባቸው ኤርትራ፤ ኢራክ፤ ሰሜን ኮሪያ፤ ሶማልያና ኢትዮጵያ ምስክሮች ናቸው። እነዚህን በድህነትና በሗላ ቀርነት የሚሰቃዩና የሚንገላቱ ሃገራትንና ድሃ ሕዝቦችን ከማሰቃየትና ከማንገላታት የበለጠ ኢ-ሰብዓዊነትና ኢ-ግብረገባዊነት ሌላ ምን አለ።

በተቃራኒው እርሷ ከአሸባሪ ቡድኖች ጋር ብርድ ልብስ ስትጋራ ውላ ታድራለች። አሜሪካ ከትህንግ ጋር ያላት የጠበቀ ጋብቻ ብዙ ይመሰክራል። ትህንግን ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድን ብላ ፈርጃ ኢትዮጵያን እንዲገዛ በ1991 አዲስ አበባ አስገብታለች። ትህንግ ኢትዮጵያን እንዳልነበረች አርጎ ሰላሳ ዓመት ሲገዛ፤ ሲዘርፍ፤ ሲገድል፤ በሰው ዘር ላይ ፍጅት ሲፈጽም፤ የምርጫ ኮሮጆ ሰርቆ (100%) አሸነፍሁ እያለ ሲአቅራራ የዴሞክራሲ ተምሳሌት አርጋ እየሳለች አኖረችው። ይህ አልበቃ ብሏትዛሬ ትህንግ ተሸንፎ ባለበት ሁኔታ ቢቻላት ሕይወት ሰጣ ባይቻላት አስከሬኑንም ቢሆን ወደ ስልጣን ለማምጣት ሃያ አራት ስዓት ትሰራለች።   

የወረቀት ነብሯ አሜሪካ በፍርሃት የታጀበች፤ ጀግና ሳትሆን በከንቱ የጀገነች ሃገር ለመሆኗ በአፈጋኒስታን፤ በቪየትናም፤ በካምቦዲያ፤ በኮሪያ እና  በሶማሊያ በተደረጉ ጦርነቶች የደረሱባት ሽንፈቶች ምስክሮች ናቸው። ጦርነቱ አልሆን ሲል ድምፅ የለሽ መሳሪያ አርጋ የምትጠቀምበት ዘዴ መዓቀብ ሆኗል። ይሁን እና በመዓቀብ አሽመድምዳ ያጠፋችው ሃገር፤ በማግለል የቀየረችው ፖለቲካና የጣለችው መንግስት አልታየም። የሚገርመው ግን መዓቀብ የጣለችባቸው ሃገራት በራሳቸው እንዲተማመኑ፤ ከምስራቁ ዓለም ጋር ይበልጥ እንዲወዳጁ ረድቷቸዋል። ለዚህ ደግሞ ኤርትራ፤ ሰሜን ኮሪያ፤ ኩባ፤ ቬትናም ይመስክሩ። 

አሜሪካ በሃብቷና በሰራዊቷ ሃይል ተኩራርታ በማንአለብኝነት በዓለም ግፉዓን ላይ ስትጮህ የኖረች ሃገር ነች። በሰራዊቱ ብዛት የገዘፈ ንጉስ በዓለም ታይቶ አይታወቅም:: የግፉዓን ሃይል የሚመነጨው ደግሞ ከእግዚአብሔር ስለሆነ ኢትዮጵያም በሃያሉ እየታገዘች የጎልያድን በትር ትመክታለች። በዓለም ማህበረሰብ ስም በሚመታ ነጋሪትና ማስፈራሪያ ኢትዮጵያ አትደናገጥም። በጫጫታ የፈረሰች ብትኖር እያሪኮ ብቻ ነች።  ስለሆነም በእግዚአብሔርና በአላህ ላይ ፅኑ እምነት ያለን እኛ ኢትዮጵያዊያን አንፈራሽም እና በማዕቀብች ታቀቢ እንበላት።

ውድ ኢትዮጵያዊያን ሆይ፦ ለእኔ አሜርካ ማለት ይሄው ነው። ሌላ ምስጢር የለውም እና ብዙ በመፈላሰፍ እራሳችንን አናድክመው። አሜርካ ጥልቅ አስተሳሰብ የሌላት፤ በእልህና በግብታዊነት የምትወስን፤ ስግብግብ፤ ዓለምን በበላይነት ለመግዛትና ለመቆጣጠር የምትፈልግ ዴሞክራሲያዊ አምባገነን ሃገር ናት። በእብሪት በትዕቢት የታበየው ልቧና አዕምሮዋ ምክር አይሰማም እንጅ ለአሜሪካ የሚበጃት በሰው ሃገር ጣልቃ ገብታ ከመፈትፈት ከቻይና ጋር ያለባትን የ$29 ትሪሊዮን ዶላር ዕዳ ጉዳይ ቅድሚያ ሰጣ ብትሰራ ነበር የሚሻላት። አሜሪካ በሆንግ ኮንግ ላይ መአቀብ ለመጣል ስትራወጥ  ታሪካዊቷ ቻይና መዓቀብ ጣለችባት። በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀር። እሰይ ኢትዮጵያዬ ቅቤ ጠጪ-ለእብሪተኛም አለቃ አለበት።  ሊነጋ ሲል ይጨልማልና አይዟችሁ፤ ኢትዮጵያችን ትሻገራለች። በያላችሁበት ሰላም ሁኑልኝ። 

ሰማነህ ታምራት ጀመረ
__

[1] White fragility by Robin Diangelo (Page 31)
[2] https://www.brookings.edu/research/new-census-data-shows-the-nation-is-diversifying-even-faster-than-predicted/
[3] http://america.aljazeera.com/articles/2015/7/28/obama-draws-criticism-for-saying-ethiopia-is-democratic.html
[4] https://www.youtube.com/watch?v=9C9_t9Fo1j
[5] https://www.thebalance.com/how-much-u-s-debt-does-china-own-41701
[6] https://www.france24.com/en/asia-pacific/20210724-china-imposes-sanctions-on-us-citizens-rights-groups-under-new-law

__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,879FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

2 COMMENTS

  1. አሜሪካ “በቅኝ ግዛት በብስባሽ ላይ ተመችቶት በበቀለ የዱር ሃረግ” ትመሰላለች፤
    ————————————————————–
    ብዛታቸው 13 የምስራቅ አሜሪካ ግዛቶች ከእንግሊዝ አገዛዝ ነጻ በመውጣት በ July4, 1776 የተባበሩት የአሜሪካ መንግስታትን (USA) እንደ ሃገር ሲመሰርቱ በወቅቱ የአሜሪካ የቆዳ ስፋት አሁን ካላው ከሶስት እጥፍ በታች ያነሰ ነበር። አሜሪካ አሁን ያላትን መልክና ቅርጽም የያዘችው በተለይም ከምስራቅ ወደ ምዕራብ አቅጣጫና ወደ ቀረው የአሜሪካ ክፍልና በዙሪያው ወዳሉ ደሴቶች በመስፋፋት ነው። አሜሪካ ቅኝ አልገዛችም ይባል እንጂ የሰራችው ስራ ግን ከቅኝ ገዢ የሚተናነስ አይደለም። የአሜሪካ በዙሪያዋ እየተስፋፋችውም ከፍተኛ ንዋይ (ገንዘብ) በማፍሰስ አጎራባች መሬቶችን ከቀድሞ ቅኝ ገዢዎች ህዝቡን ከመሬቱ ጭምር አንድ ላይ እንደ ሸቀጥ ዕቃ በመግዛት፣ ሲያመች ደግሞ የሃገሩን ነባር የጎሳ መሪዎችን እንደ “ውጫሌ” ዓይነት አወናባጅ ውል በማስፈረምና በማዘናጋት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በጦርነት እና በመሳሰሉት ነው። ለምሳሌ ሊዊዚያና (Louisiana) በ 1803 ከቀድሞ የአካባቢው ቅኝ ገዢ ከሆነችው ከፈረንሳይ በ 15 ሚሊዮን ዶላር እና አላስካን (Alaska) ከራሻ ንጉስ በ7.5 ሚሊዮን ዶላር፣ ፍሎሪዳን ከስፔን የተገዙ ሲሆኑ ሜክሲኮ (Mexico) ደግሞ በጦርነት እና የተለያዩ የአካባቢውን ነባር (Native) የጎሳ መሪዎችን በገንዘብና በውል አዘናግተው በመጠቅለል (Annexation) ነበር። በመሆኑም ታሪክ የሚነግረን ከ13ቱ የምስራቅ አሜሪካ ግዛቶች በስተቀር አብዛኛው የአሜሪካ ስቴቶች አሜሪካዊ የሆኑት ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻ ወጥተው ሳይሆን በግዢና በወረራ ጭምር ነው።

    አሜሪካ ከእንግሊዝ ነጻ ወጥታ እራሷን የቻለች ሃገር ሆነች በተባለበት ጊዜ አባቶቻቸው በሰፈራና በቅኝ ግዛት ወደ ሰሜን አሜሪካ የመጡ አውሮፓውያን የራሳቸውን የነጭ የበላይነት የነገሰበት መንግስታዊ አስተዳደር መሰረቱ እንጂ የሃገሩን ነባር ህዝብ እና ጥቁሩን ህዝብ ባለሃገር አላደረገም። በመሆኑም አሜሪካ እንደ ሃገር ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ፍጹም ከህጸጽ የጸዳች፣ የቅዱሳን ማህበር አድርጎ የሚያይ ተላላ ሰው ካለ ታሪክን ወደኋላ ሄዶ መመርመር ይኖርበታል። አሜሪካን “በቅኝ ግዛት በብስባሽ ላይ ተመችቶት በበቀለ የዱር ሃረግ” ትመሰላለች። በየጊዜው ያልተገረዘ የዱር ሃረግ በአቅራቢያው በሚያገኘው ነገር ላይ ሁሉ እየተጠመጠመ (እያነቀ) ከአንዱ ወደሌላው እየተስፋፋ እንደሚሄድ፣ የአሜሪካም ጉዞ እንዲሁ ነው።

    አሜሪካ “የነጭ ሃገር ብቻ” መሆኗ አብቅቶ የሁሉም መሆን የቻለችው 14th amendment, 1868 መሰረት አሜሪካ ውስጥ የተወለደ ማንኛውም ሰው ሁሉ የአሜሪካ ዜግነት ካገኘ በኋላ ነው። ይሁን እንጂ ጥቁር አሜሪካውያን የአሜሪካ ዜግነት ቢኖራቸውም እስከ 1965 ድረስ መምረጥ አይችሉም ነበር። ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ምስጋና ይግባውና በእሱ መሪነት በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግልና ተቃውሞ በ1965 ጀምሮ ነው ጥቁር አማሪካውያንን በምርጫ መሳተፍ የጀመሩት። . . .

    ለዲሞክራሲና ለሰባዊ መብት ቆመናል የሚሉት አሜሪካኖች በሄሮሺማና ናጋሳኪ የጃፓን ከተሞች፣ በቬትናም ህዝብ ላይ እና በመሳሠሉት ላይ የፈጸሙትን ግፍና ወንጀላቸውን የሚሸፍኑት በሆሊ ውድ ፊልም በተቀንርባበረ ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ ይታወቃል። ለመሆኑ ይህን ሁሉ ግፍና ወንጀል የፈጸሙ የምዕራባውያን መንግስታት ወደፊትስ እንዴት ሊታመኑ ይችላሉ?
    ጎጃም ምን አለ? ክላልኝ አለ!

  2. አሜሪካ “በቅኝ ግዛት በብስባሽ ላይ ተመችቶት በበቀለ የዱር ሃረግ” ትመሰላለች፤
    —————————————————
    ብዛታቸው 13 የምስራቅ አሜሪካ ግዛቶች ከእንግሊዝ አገዛዝ ነጻ በመውጣት በ July4, 1776 የተባበሩት የአሜሪካ መንግስታትን (USA) እንደ ሃገር ሲመሰርቱ በወቅቱ የአሜሪካ የቆዳ ስፋት አሁን ካላው ከሶስት እጥፍ በታች ያነሰ ነበር። አሜሪካ አሁን ያላትን መልክና ቅርጽም የያዘችው በተለይም ከምስራቅ ወደ ምዕራብ አቅጣጫና ወደ ቀረው የአሜሪካ ክፍልና በዙሪያው ወዳሉ ደሴቶች በመስፋፋት ነው። አሜሪካ ቅኝ አልገዛችም ይባል እንጂ የሰራችው ስራ ግን ከቅኝ ገዢ የሚተናነስ አይደለም። በዙሪያዋም እየተስፋፋችው ከፍተኛ ንዋይ (ገንዘብ) በማፍሰስ አጎራባች መሬቶችን ከቀድሞ ቅኝ ገዢዎች ህዝቡን ከመሬቱ ጭምር አንድ ላይ እንደ ሸቀጥ ዕቃ በመግዛት፣ ሲያመች ደግሞ የሃገሩን ነባር የጎሳ መሪዎችን እንደ “ውጫሌ” ዓይነት አወናባጅ ውል በማስፈረምና በማዘናጋት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በጦርነት በመጠቅለል እና በመሳሰሉት ነው። ለምሳሌ ሊዊዚያና (Louisiana) በ 1803 ከቀድሞ የአካባቢው ቅኝ ገዢ ከሆነችው ከፈረንሳይ በ 15 ሚሊዮን ዶላር እና አላስካን (Alaska) ከራሻ ንጉስ በ7.5 ሚሊዮን ዶላር፣ ፍሎሪዳን ከስፔን የተገዙ ሲሆኑ ሜክሲኮ (Mexico) ደግሞ በጦርነት እና የተለያዩ የአካባቢውን ነባር (Native) የጎሳ መሪዎችን በገንዘብና በውል አዘናግተው በመጠቅለል (Annexation) ነበር። በመሆኑም ታሪክ የሚነግረን ከ13ቱ የምስራቅ አሜሪካ ግዛቶች በስተቀር አብዛኛው የአሜሪካ ስቴቶች አሜሪካዊ የሆኑት ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻ ወጥተው ሳይሆን በግዢና በወረራ ጭምር ነው።
    አሜሪካ ከእንግሊዝ ነጻ ወጥታ እራሷን የቻለች ሃገር ሆነች በተባለበት ጊዜ አባቶቻቸው በሰፈራና በቅኝ ግዛት ወደ ሰሜን አሜሪካ የመጡ አውሮፓውያን የራሳቸውን የነጭ የበላይነት የነገሰበት መንግስት መሰረቱ እንጂ የሃገሩን ነባር ህዝብ እና ጥቁሩን ህዝብ ባለሃገር አላደረጉም። በመሆኑም አሜሪካ እንደ ሃገር ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ፍጹም ከህጸጽ የጸዳች፣ የቅዱሳን ማህበር አድርጎ የሚያይ ተላላ ሰው ካለ ታሪክን ወደኋላ ሄዶ መፈተሽ አለበት። አሜሪካ “የነጭ ሃገር ብቻ” መሆኗ አብቅቶ የሁሉም መሆን የቻለችው 14th amendment, 1868 መሰረት አሜሪካ ውስጥ የተወለደ ማንኛውም ሰው ሁሉ የአሜሪካ ዜግነት ካገኘ በኋላ ነው። ይሁን እንጂ ጥቁር አሜሪካውያን የአሜሪካ ዜግነት ቢኖራቸውም እስከ 1965 ድረስ መምረጥ አይችሉም ነበር። ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ምስጋና ይግባውና በእሱ መሪነት በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግልና ተቃውሞ በ1965 ጀምሮ ነው ጥቁር አሜሪካውያን በምርጫ መሳተፍ የጀመሩት። ይህ የሆነው ደግሞ አሜሪካ ከተመሰረተች ከአንድ መቶ ሰማንያ ዘጠኝ (189) ዓመት በኋላ ነው።
    ለዲሞክራሲና ለሰባዊ መብት ቆመናል የሚሉት አሜሪካኖች በሄሮሺማና ናጋሳኪ የጃፓን ከተሞች፣ በቬትናም ህዝብ እና በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የፈጸሙትን ግፍና ወንጀል የሚሸፍኑት በሆሊ ውድ ፊልም በተቀንርባበረ ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ ይታወቃል። ለመሆኑ ይህን ሁሉ ግፍና ወንጀል የፈጸሙ የምዕራባውያን መንግስታት ወደፊትስ እንዴት ሊታመኑ ይችላሉ?
    ጎጃም ምን አለ? ክላልኝ አለ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here