spot_img
Saturday, April 20, 2024
Homeነፃ አስተያየትኢትዮጵያን በማንበርከክ ዳግም አፍሪካ ላይ የባርነት ቀንበር መጫን አይቻልም!!! (No More)

ኢትዮጵያን በማንበርከክ ዳግም አፍሪካ ላይ የባርነት ቀንበር መጫን አይቻልም!!! (No More)

ግርማ ቸሩ

 በእግዚአብሄር ቸርነትና ችሮታ እድሜዬ በርክቶ፤  ለአያሌ አመታት በምእራባውያን ሀገሮች ቅኝ ግዛት ስር ወድቀው የነበሩ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን እንዲቀዳጁ ፈር የቀደደውን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታና የነፃነት ጅማሮን በግዜው እንዳየሁ ሁሉ፤ አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ላይ የተፈጠረውን ውስጣዊ ችግር በማጉላትና ምክንያ በመደርደር፤ በውጭ ሃይሎች በሚደረግ ጣልቃ ገብነት አገሬ ስትፈርስ ማየት አልሻም። 

በዚያን ዘመን በርካታ የአፍሪካ ሀገራት በቅኝ አገዛዝ የባርነት ቀንበር ውስጥ የወደቁ በመሆናቸው፤ አፍሪካውያን ነፃነታቸውን ለማስመለስ ይችሉ ዘንድ በኢትዮጵያ ፊታውራሪነት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ በእኛይቱ እዲስ እበባ ከተማ ላይ ለመመስረት ታሪካዊ ጉባኤ ተካሂዶ ከጉባኤ መልስ በቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ በአሁኑ “ብሔራዊ ቴያትር” ቤት መድረክ ላይ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴና በጉባኤው ተሳታፊ የነበሩ 

የሀገራት መሪዎች በተገኙበት ወቅቱን ያገናዘበ ትያትር መቅረቡ የሚታወስ ሲሆን፤ እኔም በቀረበው ተውኔት ላይ ተሳታፊ ሆኜ “የአፍሪካ አባት” በሚል ገፀ ባህሪ በመላበስ (በመተወን) የታሪኩ ተካፋይ ለመሆን በቅቻለሁ። 

እነሆ በዛን ዘመን በጥሩ ቁመናና የአካል ብቃት ላይ ሳለሁ በግዜው የቴያትር ቤቱ ዋና አስተዳዳሪ በነበሩት በአቶ እዮኤል ዮሃንስ ግብዣ መጠነኛ ልምምድ በማድረግ በተሰጠኝ ገፀ-ባህሪ ላይ አፍሪካ ከተጫነባት የባርነት ቀንበር ነፃ ትወጣለች!  በሚል ተስፋን የሰነቀ መልእት በእጄ ላይ የነበረውን ሰንሰለት በመበጠስ አስወግጃለሁ። እነሆ ከላይ በምስሉ የምትመለከቱት ግዜ ቦታና ሁኔታዎችን የሚያመላክት ከመድረኩ ላይ የተወሰደ የኔ ፎቶ ነው። 

እንደሚታወቀው ሁሉ ሀገራችን ኢትዮጵያ እጅግ ውስብስብና አስቸጋሪ ፈተናዎችን አልፋ ያለ ማንም ይሁንታ በራሷ ልጆች ተጋድሎ ነፃነቷን ጠብቃ የኖረች አፍሪካዊት ብቸኛ ሀገር ነች። የዛሬውን ከትናንቱ ፈታኝ የሚያደርገው ግን የውጭ ወራሪና የውስጥ ሆድ አዳሪ ባንዳዎች እየተናበቡ ጥቃት መፈፀማቸው ብቻ አይደለም። ይህ አምና ዘንድሮና ወደፊትም የነበረ ያለና ሊኖር የሚችል የደካማ ሰዎች ባህሪ ነው። ዋናው ችግራችን ወያኔ በዘረጋው መረብ በዘርና በጎጥ ተቧድነንና ከሰውነት በታች ወርደን ባለንበት በዚህ ሰዓት መሆኑን በመገንዘብ ያሉብንን መሰረታዊ ችግሮች ሁሉ ለግዜው ወደ ጎን በመተው እንደ ቀደምት አባቶቻችን በምህረትና በይቅርታ በመታለፍ የመጣብንን ጠላት አንድ ሆነን በመመከት ሉአላዊት ሀገራችንን ሳናስደፍር ነፃነታችንን ማስጠበቅና ለመጪው ትውልድ ማውረስ ከዚያም በዘለለ ለሌሎች አፍሪካውያን ወንድሞቻችን አርአያ መሆን ይገባናል። 

* በዚህ አጋጣሚ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ እውን መሆን ብቻ ሳይሆን በግዜው ሀገራችን ኢትዮጵያ ተደማጭነቷን በማጉላት ከታላላቆቹ ተርታ እንድትቆም ላደረጉና ክብርን ላጎናፀፉን። 

ለግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይል ስላሴ ለክቡር ጸሐፊ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ለክቡር ኦቶ ከተማ ይፍሩ ያለኝን አክብሮት ለመግለፅ እወዳለሁ። ለዚህ ዘመቻ ሉኡል እግዚአብሄር አቅምና ጉልበት ይሁነን። 

አትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ!!! 
ግርማ ቸሩ ዱብ ዱብ በሉ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

2 COMMENTS

  1. It is impossible to colonize Ethiopia, land of heroes fanos who are children of belay zeleke and menilik, told neftegna outlets. However, eritreans and Sudanese people are laughing and mocking at this rhetoric. Eritreans, Turkey, and Sudanese are controlling Ethiopian Economy and land.

    Amhara elites keep n fooling your people .

  2. God bless Ethiopia and Ethiopian thank u for ur service God be with all with this difficult Journey we will win band will not destroy Ethiopia!! Del le Ethiopia always!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here