spot_img
Tuesday, June 25, 2024
Homeነፃ አስተያየትምሕረት ሲሉ : ፍትሕ ስንል ለየቅል!!! (ከቴዎድሮስ ሃይሌ)

ምሕረት ሲሉ : ፍትሕ ስንል ለየቅል!!! (ከቴዎድሮስ ሃይሌ)

                                                                           

       የታማሚው የበሽታ ውጤት መክፉት ያስጨነቀው ዶክተር በደንበኛው ላይ ሊያስከትል የሚ ችለውን የአካል ስቃይና የሞራል ስብራት አለሳልሶ በዘዴ ለመንገር መላ ይዘይዳል:: ታማሚውም ዶክተሩን ሲመለክት እንዴት ነውጤናዬ ሲል ይጠይቃል ? ዶክተሩም ለታማሚው ጥሩም መጥፎ ም ዜና አለ ይላል:: ታማሚም መጥፎው  ምንድንነው? ጥሩውስ ዜና ብሎ ይጠይቃል? ዶክተሩም  መጥፎው ዜና እግርህ የሚቆረጥ ሲሆን ጥሩው ዜና ደግሞጫማህን የሚገዛህ ማግኘትህ ነው::  አለው ይባላል::

              መጥፎና ጥሩን በነገር አዋዝቶ ቢያቀርቡትም ውጤቱን ግን ፈጽሞ ቅንጣት ታህል አይለ ውጥም:: ጨለማና ብርሃን በምንም አይነት ውቡ ቋንቋ ቢገለጽ አንድ አይሆኑም:: ጠቅላይ ሚን ስትር አብይ ዛሬ በነስብሃትነጋና እስክንድር ነጋ ላይ የወሰዱት የምህረት ውሳኔ ከላይ ያነሳንው ሃኪም ሕመምተኛውን አጽናንቶ ለመንገርየሄደበትን እርቀት ያመሳስልባቸዋል ::

                 የሃገርን ብሄራዊ አደጋ የሚመለከቱበት አንግልና ቀውስን የሚፈቱበት አቅጣጫ ጥራትም ግልጽነትም ሁሌም አነጋጋሪ ከሆነ ቆይቷል:: ጠቅላይ ሚንስትሩ በታሪክ አጋጣሚ ከሳቸው በፊ ት ከነበሩ መሪዎች በተሻለ ተቀባይነትናተወዳጅነት በአጭር ግዜ መቀዳጀት ቢችሉም በቀላሉ ተ ገማችና ሊታወቅ የሚችል ጠንካራና የነጠረ የፖለቲካስብዕና የሌላቸው ካለፉት በጣም የተለዩ አ ድርጏቸዋል::

            አመራራቸው ግራ አጋቢ የውሳኔ አሰጣጣቸው አወዛጋቢ የፖለቲካ ርዕዮታቸው አጠራሪ  እንደሆነምቆይቷል:: የቅርብ ደጋፊዎቻቸውና የእርሳቸው አድናቂ የሆኑ ሊሂቃን ጭምር በቅጡ   የማይረዷቸው መሪ ናቸው:: ሕዝባችን የመንግስቱን ሃገር ወዳድነት ; የመለስ ዜናዊን ዘረኝነት የ ሃይለማርያም ደሳለኝን ልፍስፍነት በቅጡተረድቶ ኖሯል:: ጠ.ሚ አብይን ግን ንግግርና ተግባራቸ ው አንዳንዴ የሚጣረስ :  የሚወስዱት አቋም ብዙንውግዜ ብዙሃኑን የሚያምታታ ምን ለማድረ ግና ምን ለማለት እንደፈለጉ የማይገባ የሚሆንበት ግዜ የበዛ ሆኖቆይቷል::

           ሴራ ተንታኞችና የፖለቲካ ተቃዋሚዎቻቸው የአብይን ፍላጎት ለመረዳት የፓርቲያቸውን ወ ሳኝ ሰውናየእሳቸው የቅርብ ታማኝ እንደ ሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ሽመልስ አብዲሳን ማድመጥ ይገባል ይላሉ:: ገራገሩናየበታችነት ስነልቦና ዋግ እንደመታው አገዳ ሕሊናቸውን ያዳሸቃቸው ኦቦ ሽመልስ ብዙ አወዛጋቢ አመጽየሚቀሰስና ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ ንግግር በአደባባይና በግ ላጭ በማቅረብ ይታወቃሉ:: በተለይም አቶሽመልስ በአንድ ወቅት የተናገሩ የምንችለውን convin ce አድርገን፣ ያልቻልነውን confuse አድርገንየድርጅታችንን ፍላጎት የማሳካት እቅድ ዘርግተና ሲሉ  የተናገሩት ንግግር ያሳደረው ተጽዕኖ ከእሳቸው አልፎጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚወስዷቸውን አቋሞ ች ጭምር በዚህ አውድ ስር እንዲታ አድርጎታል።

          ዛሬም የጠቅላይ ሚንስትር አብይ መንግስት የወሰነው ውሳኔ አነጋጋሪ የሆነው ለዚህ ነው:: ወንጀለኛውንደም መጣጩንና ሃገር ሻጩን በየዋኽ የፖለቲካ ታሳሪዎች ጀቡኖ በምህረት ስም ከ ፍርድ መንበር ማራቅ የሕግልዕልናን መናድ ተደርጎ የተወሰደው::  የጦር ወንጀል የፈጸመን በሰላ ም ከታገለውና በፖለቲካ አቋሙ ብቻ ለእስርየተዳረገውን ፖለቲከኛ በአንድ ሚዛን መለካት ተንበር ካኪነት አልያም የconvince  እና confuse  ጭምብል ነውበሚል እያወያየ ያለው።

       የደቡብ አሜሪካ ድራግ ነጋዴዎችና የማፍያ መሪዎች በፍትህ ስርዐቱና በመንግስት ቢሮክራ ሲ ውስጥባላቸው የግንኙነት ሰንሰለትና ሕገ ወጥ የጥቅም ተጋሪነት በአያሌ ንጹሃን ዜጎች ሕይ ወት መጠየቅ ሲገባቸውፍርድ እየተገለበጠ በነጻ የሚወጡበት አሰራር እስከ ዛሬም ድረስ ይተገበ ራል:: በሃገራችንም በዘመነ ሕወሃትሃገር የዘረፉና የንጹሃንን ሕይወት ያጠፉ ግለሰቦች ለነበረ ው የፖለቲካ ስርዐት ካላቸው ቀረቤታና ታማኝነት የተነሳሳይጠየቁ በነጻነት ይኖሩ እንደነበር አይዘ ነጋም:: 

           የአብይ መንግስት እያስወገዘው ያለው መሰረታዊ ጉዳይም ይህው ነው:: የሕወሃት መሪዎ ችና አባላት የሃገርመከላከያ ሰራዊትን ከጀርባ እንዲወጋ አመራር የሰጠ በምክር የተካፈል ግልጽ የሆነ ወንጀል የፈጸመን አካል ከፍሲል በሞት ዝቅ ሲል በእድሜ ልክ እስር ሊጠየቅ የሚገባን ሽብ ርተኛ በምህረት ስም በነጻ መልቀቅ ሊገባን ያልቻለእንቆቅልሽ የሆነው::

            ለውጥ መጣ ከተባለበት ከባለፉት ሦስት አመታት ወዲህ : በተለይ በመንግስት አወቃቀር በፖለቲካናበጸጥታ አመራሩ ዳተኝነት አንዳንዴም ቀጥተኛ የሴራ ተባባሪነትና የአመራር ብቃት ማጣት ዜጎች ተወልደውካደጉበት ሲባረሩ : በግፍ ሲገደሉና ያፈሩት ሃብትና ንብረት ሲወድም አ ንድም ተጠያቂ ለፍርድ ሊቀርብ ለተጎዱትካሳ ለሞቱት ፍርድ ሲሰጥ አላየንም:: እንዲያውም በቁ ጥር ቅቀላ በሟቾች የብሄር ትንተና ሃቅ ሲታጠፍ እውነትሲደፈቅና ፍትሕ ሲደፈጠጥ ማየት በ ተለይ የጠ ሚ አብይ ዘመነ መንግስት ዋና ባህሪ ሆኖ ቆይቷል::

          ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ለንግግራቸው ውበት ለተስፉ ቃላቸው ታማኝነት ሕዝባችን በሺ ዎች እየሞቱበትበቢሊዮን ዶላር ሃብቱ እየወደመበትና በሚሊዮን እየተፈናቀለም ላለፉት 3 አመ ታት በትግዕስትና በበስተዋይነትየመሪውን ቃል አምኖና ተቀብሎ ቆይቷል:: ሊነጋ ሲል ይጨልማል  ለሠላሳ አመታት የተጨማለቀ ቢሮክራሲእስኪጠራ የተሰገሰገው ባንዳና ጥቅመኛ ሲወገድ የመ ሪው ሕልም ይሳካል:: ሕዝብ ከቀውስ ፖለቲካውምከንትርክ እርቆ እንደ መሪው ቃል ያማረና ዘ መኑን የዋጀ የፖለቲካ ስርዐት ይኖረናል በሚል ተስፉ በታላቅመስዕዋትነት በታግዘ ትግዕስት ጠብ ቀናል::

          የትግራይ ወራሪ በተፈጠረበት ተንቤን በርሃ ሰጥሟል:: ሊያሰጋ የማይችል ዱቄት ሆኗል ተባ ለ:: መቀሌከበሻሻ የማትሻል እስትራቴጂያዊም ፖለቲካዊም ተፈላጊነት የላትም ሲሉንም አምነና ል:: መከላከያ ከትግራይየወጣው ለትግራይ ገበሬ የእርሻ ግዜ ላለማውክና የሰላም አማራጭ ለመ ስጠት ነው ሲሉም ተቀበልን:: ዱቄትየተባለው ሕወሃት  በሃገር ፍቅር የተሰለፈውን ሰራዊት በሴ ራና በፖለቲካ አመራሩ ድክመት እየደመሰሰመሳሪያውን እየማረከና የሕዝብን ንብረት እየዘረፈ 8 00 ኪሎ ሜትር አቋርጦ ሰሜን ሸዋ ሲደርስ የመንግስትን  ደካማነት እያወቀም ወቀሳና ቅሬታው ን ውጦ ከመንግስት ጉን ሳይለይ ሕዝብችን  ብዙ እጅግ ብዙ ዋጋ ከፍሏል::

         ብዙ ሸፍጥ እጅግ የከፉ ክህደት አሳፉሪ የአመራር ዝርክርክነት: አስነዋሪ የብቃት ማጣት አ ስገራሚየመሪው ዝና ጥመኝነት የድል ሽሚያ ሁካታ አይተን እንዳለየ አልፈናል:; የእርቅ ጉባኤው ቱማታ የመልሶ ማጥቃቱዘመቻ ወደ ትግራይ አይሻገርም የተባለው መመሪያ የጦርነቱን በድል መ ጠናቀቅ ጮቤ እረገጣ ሁሉ ለሃገርናለህዝብ ሲባል ባይጥምም ባያሳምንም መንግትንና መሪን ለ ማክበር ሲባል ይሁን ተባለ:;

            ብዙ ነገር መጣ ብዙ ነገርን አለፈ:: ሁሉንም ሕዝባችን በጨዋነት ቁጣውንም ተቃሞው ን አምቆ ለሃገርሲል አድርግ የተባለውን አደረገ:: ዘመተ ተሰዋ በደጀንነት ያለውን አዋጣ ደሙን ሰጠ ሁሉን አደረገ:: ዲያስፖራውም በያለበት በቃ ሲል በምዕራባውያን አደባባይ ጮኽ የትግራይ ወራሪዎች ያወደሙትን ሊገንባየተፈናቀሉትን ሊያቋቁም የተራቡትን ሊያካፍል በታኝና ከፉፉዩ ን የስደት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ተቋቁሞከመንግስት ጎን ቆመ:: 

      ኢትዮጵያን የቀውስ ቀጣና የጦርነትና የምስቅልቅል  ዞን አድርገው ሃገሪቷን ለቀው የሌላ ሃገ ር ዜጎች  እንዲወጡ ቀንና ሌሊት ሲቀሰቅሱ የቆዩትን የአሜሪካ መንግስትና የምዕራብውያ ሚድ ያ ሴራ አክሽፎ በመሪውየተላለፈውን ወደ ሃገር ኑ ጥሪ ብዙ ሺህ ዲያስፖራ አክብሮ በአሁኑ ሰዐት  በሃገር ቤት ይገኛል:: ይህ ታላቅ ከፍታወገንን ያኮራና ኢትዮጵያዊነትን ያጠናከረ ሁኔታ ላይ የነዋሪ ውንም እንግዳውንም የደስታ ስሜት ያጠፉ ውሳኔባያደበዝዘው ምንኛ ባማር ነበር ::

           ዛሬ ሃገራችን ላለችበት አደገኛ አጣብቂኝና ውድቀት የእራሱን ድርሻ ያለው የብልጽግና መንግስትናጠቅላይ ሚንስትሩ ዛሬም እንደ ለመዱት በሃገርና በሕዝብ ሕልውና ላይ ሃላፊነት የጎ ደለው ውሳኔ ሰጥተዋል:: ጠቅላይ ሚንስትር አብይና ፓርቲያቸው ብልጽግና በፍትህ ሂደት በሕግ ልዕልና ላይ የፈጸመው ክህደት በወንጀልምበታሪክም የሚያስጠይቀው ይሆናል:: መሪውና ፖርቲ ው ፍትሕን የማያከብር ከህግ በላይ የሚራመዱ ፍጹምአንባገነን ስርዐት የለሽ ለመሆናቸው በዛ ሬው እለት የወሰዱት እርምጃ እንደ ማሳያ ቢቆጠር አይበዛብትም:: 

             በሽብርተኝነት የተከሰሱ በሃገራችን መከላከያ ሰራዊት በሰሜን እዝ ላይ ክህደት ፈጽመ ው ለብዙ ሺየሰራዊት አባላት ሞት እስርና ለሃገር ውድቅት መንስዔ በሆኑ የሕወሃት ከፍተኛ አመ ራሮች ላይ የተሰጠው በነጻየመለቀቅ ብያኔ ሕዝብን ግራ አጋብቷል:: የመንግስትንም ቁርጠኝነት ና ታማኝነት ጥያቄ ላይ ጥሏል:: ሊያስከትልየሚችለውም የሃይል አሰላለፍና የፖለቲካ አውድ ማወ ሳሰብ ሌላ የከፉ ቀውስ እንዳያዋልድም ተሰግቷል:: ግልጽነትም ተቀባይነትም ተነፍጎታል::

           የሴራ ተንታኞች የሕወሃት ካድሬዎች የምዕራቡ ሚድያዎች ባንዶችና የዪቱብ ወሬ ሸቃ ጮችንፕሮፓጋንዳ ታግሶ የመንግስትን እንዝህላልነት እንዳላየ እልፎ እየከረፉውም ቢሆን አፍን ጫውን ይዞ መንግስትንሲደግፍ የቆየው ኢትዮጵያንዊ ዛሬ በሰማው መርዶ ተሸማቋል:: የሽመ ልስ አብዲሳን የቁማር ጨዋት እንዲያስብየወሬ ነጋዴዎችንም ጩኽት መልሶ እንዲሰማ መንግስ ትን እንዲጠራጠር ተገዷል:: ለዚህ ነው የምንጠይቀውዶር አብይ ምህረት ሲሉ እኛ ኢትዮጵያው ያን ፍትሕ ይሰጠን የምንለው::ምህረት በፍትሕ ተመዝና የምትከብር የበረከት ፍሬ እንጂ በጉል በት የምትገኝ ከሆነ የመርገም መንገድ የበቀልዛር የጥፉት አዙሪት ከመሆን አታልፍም:: 

ክብር ለመከላከያ ሰራዊታችንና ለመላው ሕዝባዊ ሃይል!!! 

       ኢትዮጵያዊነት ትላንትም ዛሬም ነገም ያሸንፉል!!

_
በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here