ከቴዎድሮስ ሃይሌ
ሕወሃት የኢትዮጵያ ሕልውና ለማፍረስ የሰሜን ዕዝን አጥቅቶ የለኮሰውን የክህደት ጦርነት በአጭሩ እንዲቀጭ የኤርትራ መንግስት ሚና ቀላል አልነበረም:: የከሃዲው ቡድን ጎምቱ መሪዎች እንዲደመሰሱ ሕወሃትም ክንፉ ተሰብሮ ወደ ተንቤን ሸለቆ እንዲያፈገፍግ የኤርትራ እገዛ ወሳኝ ነበር:: ይህ የኤርትራ ሰራዊት ወገናዊ ድጋፍ ምንም ለጋራ ደህንነት ቢሆንም ኢትዮጵያውያን የማይዘነጉት የታሪክ አጋጣሚ ነው::
ለዘለቄታውም ሻክሮ ለኖረው ለሁለቱ ሃገር ሕዝቦች በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተ አብሮነት እንዲጠናክር የሚረዳም አጋጣሚ ነው::
የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝብ ባለፉት ዘመናት ለብዙ መከራና መለያየት ቢዳረግም ሊበጠስ በማይችል የረጅም ዘመን የአብሮነት ታሪክ የተሳሰረ ነው:: በተለይም ኤርትራን በቀጥታ ድንብር የሚጋሩት የአማራና የአፉር ኢትዮጵያውያን ከጉርብትናውም በላይ በበዙ ማህበራዊና ባህላዊ መስተጋብሮች የተቆራኙ ናቸው:: የአንዱ ልማትም ሆነ ጥፉት ለሌላኛው ያለው ተጽዕኖ እጅግ በጣም ቅርብ ነው::
የአማራ የአፉርና የኤርትራ ሕዝብ ሰላምና ደህንነቱ ተረጋግጦ ወደ ልማትና ብልጽግና የሚያደርገውን ጉዞ ሊያደናቅፍ የተነሳውን ቅጥረኛውን የሕወሃት ጁንታ በጋራ ተፉልሟል:: ሕወሃት ለነዚህ ሕዝቦች የህልውናጠላት መሆኑን በተጨባጭ ያረጋገጠና ወደፊትም ከተሳካለት በነዚህ ሕዝቦች ላይ ሊፈጽም የሚችለው ሰቆቃየከፉ እንደሚሆን ማስረጃ ማጣቀስ አያስፈልገውም:: ለዚህም ነው ሕወሃትን አምርረው በመታገል ላይ ያሉት::
ከዚህም በላይ የሕወሃት ሕልውናን በማያዳግም መንገድ መቋጨት ለኢትዮጵያውያ ብቻ ሳይሆን ለምስራቅ አፍሪካ ጭምር እፎይታ ነው:: ሕወሃት የሽብር ሃይል የውጪ ሃይሎች ተላላኪ ጸረ ሕዝብ በመሆኑ በማንኛውም መንገድ ከድምሰሳ ተርፎ የቀጠናው ስጋት እንዲሆን የሚተባበረውን ጭምር መዋጋት አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው:: የኤርትራ ሕዝብ ሰላምና ብልጽግና የአማራና አፉሩ ማህበራዊ እረፍትና ልማት የሚረጋገጠው የሕወሃት እስትንፉስ ሲዘጋ ብቻ ነው::
የኤርትራን ሕዝብ ለማንበርከክ በሕወሃት ደላላነትና በጌቶቹ የምዕራቡ ዓለም ደም መጣጭ ኒዖ ኮሎኒስታዊ ሃይሎች ቀጥተኛ ውሳኔ ላለፉት 20 አመታት በመራር የኢኮኖሚ ማዕቀብ ተንገላቷል:: አማራ እንደ ሕዝብ ቃላት ሊገልጹት ከሚችሉት በላይ የሕወሃት የበቀል ሂሳብ ተወራርዶበታል:: አፉር ኢትዮጵያዊነት ማስቀደሙ ከባድ ዋጋ አስከፍሎታል:: ሌሎች ኢትዮጵያውያንም የሕወሃት የግፍ ሰለባ መሆናቸው ባይዘነጋም በነዚህ ሦስት ሃይሎች ላይ ከደረሰው ጋር ግን አይስተካከልም::
ሕወሃት ተራ የመንደር ሽፍታ ተደርጎ ሊናቅ የማይችል በቀጠናው ጂዖ ፖለቲካዊ ፍላጎት ያላቸው የተለያዩ ሃይሎች ለሽብር አላማ ሊጠቀሙበት የሚፈልጉት ሃይል ነው:: የወንበዴው ቡድን መሪዎች እንኳን ለሌላው በስሙ ለሚነግዱበትን ለትግራይ ሕዝብ ጭምር ግድ የላቸውም:: ከግል የበቀልና የስልጣን ጥማቸው እና ከቁስ ሰቀቀናቸው ባሻገር ምንም የማይታያቸው ጭራቆች በመሆናቸው በተባበረ ክንድ ከስራቸው ተነቅለው እስካልተወገዱ ድረስ ቀጠናው ወደ ሰላምና ልማት ፈጽሞም አይሸጋገርም::
ሕወሃት አንብሮት በኖረው እርኩስ የፖለቲካ ርዕዮት አጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሁኔታም በብዙ ችግሮች የተተበተበ እንደሆነ ቀጥሏል:; ሃገሪቷ ካለችበት የቀውስ እዙሪት ለመውጣት የምትችልበት መሪ እቅድና ፕላን መንግስት እጅ ስለመኖሩ አይታወቅም:: የመንግስት ፖሊሲና የአፈጻጸም ብቃትና ቁርጠኝነት ከሁኔታው በታች ነው::ሕወሃት ከፉፍሎ ለመግዛት እንዲመቸው በኢትዮጵያ ላይ ደንግጎት የኖረው ሕገ መንግስትም ዛሬም ከተተከለበት የዘር ማጥ አልተነቀለም::
ይህው የአራዊት ሕግ ኢትዮጵያን ፈንጂ ላይ የቆመች ሃገር አድርጏታል:: በዘር ፖለቲካ ቋያ የምትንገበገብ በውስጥ አድሃሪ በውጪ የቅጥረኛ ማዕበል የምትናጥ አደጋ የተቆራኛት ሃገር ሆናለች:: የዚህ ሁሉ ጥፉት አጋፉሪው ሕወሃት በመሆኑ በዚህ ቡድንና ይዞት በኖረው ጨለምተኛ ተረኮቹ ላይ የሚወሰድ አቋም የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካ ቀንድን ሁኔታ ይወስናል::
ፕሬዜደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ባለፈው ሳምንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያን ሁኔታ ዝም ብለው እንደማይመለከቱ ተናግረዋል:: በተለይም በኢትዮጵያ የተንሰራፉው የዘር ፖለቲካ በጣም እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል:: ኢትዮጵያ ከዘር ፖለቲካ ተላቃ በዜግነት ላይ የተመሰረተ ስርዐት እንድትመራ ያላቸውን ቀና ምኞት በይፉ አሳውቀዋል::
ይሄ የኤርትራው መሪ አቋምና እምነት በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚያምኑበትና ብዙ ዋጋም የከፈሉበት ወሳኝ ጉዳይ ነው:: እንደ ሃገር የመዳኛም መንገድ ነው:: በአንጻሩም ሕወሃትና ተንበርካኪ ግልገሉ ኦነግ በዘር ፖለቲካ የቆረቡና እስከ ምጽዐት እንዲቀጥል የሚፈልጉ ናቸው:: ይህንንም ሕልማቸውን ለማሳካት በቅንጅት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ኦነግና ሕወሃት ቃልኪዳናቸውን አድሰው በጋራ ብዙ ውድምት ማድረሳቸን አይተናል::
ሕወሃትና አስተሳሰቡ ከኢትዮጲያ የፖለቲካ ሜዳ ውስጥ ሊመለስ እንዳይችል መቀበር እንዳለበት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ያምናል:: ለተግባራዊነቱም ተንቀሳቅሷል:: ነገርግን ከቅርብ ግዜ ወዲህ ሕወሃትን በተመለከተ የኢትዮጵያ መዐከላዊ መንግስትና ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚያራምዱት አቋም ግልጽነቱ በጣም አጠያያቂ እየሆነ መጥቷል:: ሽብርተኛው የሕወሃት ሃይል ላይ የሚወሰድ ማንኛውም ውሳኔ የአማራና የአፉርን ጥቅም እንዲሁም የኤርትራን ደህንነት ታሳቢ ያደረገ አካሄድ ለሁሉም የሚበጅ መሆኑ አያጠራጥርም::
ለቀንደኞቹ ወንጀለኛ የሕወሃት መሪዎች የተሰጠው ምህረት እና እነ ጌታቸው እረዳ የሰላም ጥረቱን የኤርትራ መንግስት እያደናቀፈ ነው ብለው መክሰሳቸው ; የጠቅላይ ሚንስትር አብይ መንግስት በስውር ከሕወሃት ጋር እየተደራደረ ነው የሚል ግምት ብዙሃኑ እንዲያምን እያደረገው መጥቷል::
ይህንና የመንግስትን ግልጽነት የጎደለው ውሳኔ ሴራ ተንታኞችና የፖለቲካ ተቃዋሚዎች የሚያነሱት አጀንዳ ተዐማኒ እንዲሆን አስችሎታል:: በርካታ ግራ አጋቢና ሚስጢራዊነት በገዥው ሰፈር ይስተዋላል:: በተለይ የብልጽግናው ኦዴፓ ከእግር ጥፍሩ እስከ እንጥሉ በኦነግ ሲምፐታይዘሮች መጠቃቱን የሚያሳይ ምልክት ለማግኘት ምርመራ አያስፈልገውም:: መጠቃት ብቻ ሳይሆን ተወሯል ባዩም ብዙ ነው::
የመራራ/ጁሃር ኦፌኮም የሕወሃት ሕልውና ጨርሶ መጥፉቱን በስጋት የሚመለከት ነው:: ኦፌኮ ታክቲካል አጋር ለመሆኑ ደፍሮ ይፉዊ መግለጫ ባይሰጥም የፖለቲካ ርዕዮቱ ተጋሪ ነው:: በቅርቡም በሰጠው መግለጫ የሕወሃትን የክህደት ጦርነት ለማውገዝ አልፈለገም:: እንዲያውም ከሰሜኑ ወሳኝ ጦርነት ይልቅ
በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ላይ ትኩረት በመስጠት የሕወሃትን ጉዳይ ባላየ ማለፍን መርጧል:: ይህና ሌሎች ሁኔታዎች ተጨማምሮ የኦሮሞው ኤሊት የሕወሃት ሌጋሲን በሌላ ግልባጭ ጥገናዊ የዘውግ ፖለቲካ የማስቀጠል ፍላጎት እንዳለው ሁኔታዎች ይናገራሉ:: አፍቃሬ ሕውሃትነት በኦሮሞ የፖለቲካ ሰፈር በሸኔ በኩል የማያሻማ ምላሽ አግኝቷል::
በዘር ክልል የተደራጀው የፖለቲካ አወቃቀር ከሌንጮ ለታ እስከ ሽመልስ አብዲሳ ተቀባይነት ያለው ነው:: የኦዴፓም መርሆ የነበረውን ባለበት ከማስቀጥል የሚወጣ አይመስልም:: ጠቅላይ ሚንስትሩም ይህን አስተሳሰብ ይጋሩታል የሚል ግምት ከቅርብ ግዜ ወዲህ በስፉት ይነፍሳል:: ይህ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል:: “እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ” ሃቁ ሊገልጥ ቀኑ ለመቃረቡ መገመት ጠንቋይ አያስብልም::
በጥቅሉ የኢትዮጵያ መዕከላዊ መንግስት ፣ ገዥው ፓርቲና ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሕወሃትንና የዘር ፖለቲካ ሌጋሲው ላይ ያላቸው አቋም ነጥሮ ሲወጣ የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ሃይል አሰላለፍ ምን መሆን እንዳለበት ይወስናል:: የሕዝብና የኤሊቱም የትግል አቅጣጫ ጥራት ያገኛል:: በአንጻሩም የሕወሃት የሽብር ዘመቻ ተጋላጭ በሆኑት የአማራ አፉርና ኤርትራ የነበረው የቀውስና የጦርነት ሁኔታ ሌላ መልክ ይይዛል::
የምዕራባውያን ተጽዕኖ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የፈጠረው የሕልም ተቃርኖ የሃገረ መንግስት አፈጣጠርና የታሪክ አረዳድ ግጭት; የኦሮሞ ኤሊት ለሕውሃት ሌጋሲ ያለው ታማኝነት ተጨማምሮ ሕወሃትን ተመልሶ የፖለቲካ ሕልውና ሊያቀዳጀው የሚችልበት ሁኔታ ሊመጣ ይችላል::
ሕወሃት ተመልሶ የፖለቲካ ሕልውና አገኘ ማለት በተለይ ለአማራ አፉርና ኤርትራ ማባሪያ ለሌለው ቀውስ ተዳረጉ ማለት ነው:: ሕወሃት ዳግም ሕይወት ዘርቶ ሊቆም አይገባም:: ሕወሃት የሞት ነጋዴ የጭካኔ ንጉስ የቅጥረኝነት አውራ በመሆኑ ዳግም እድል አግኝቶ ሕዝባችን ማለቂያ ለሌለው መከራ እንዳይዳረግ በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ ማስወገድ ለመላው ኢትዮጵያዊ በተለይም ለአማራ አፉርና ኤርትራ አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው::
የትግሬ ወራሪ ዘራፊና ሽብርተኛ ሃይል በድንበር ተጎራባች ከሆኑት አማራ አፉርና የኤርትራ ሕዝብ ትላንት ካደረሰባቸው በላይ ለዳግም ጥቃት እንዳይጋለጡ የተናበበና በጥምር የሚመራ የጸጥታ ትብብር ከወዲሁ ሊያስቡበት ይገባል:: ምሁራን የማህበረሰብ አንቂዎችና መላው ሕዝቡ አማራጭ የትግል መንገዶችን በግዜ መፈተሽ ይኖርበታል:: በተለይም የኤርትራ ሕዝብና መንግስት የአማራና የአፉር ማህበረሰብ መተባበር ከቻለ አይደለም ሕወሃትንና ቡችሎቹን ማንኛውንም ምድራዊ ሃይል መቋቋም ይችላል::
ይህ የቢሆን እይታና የፖለቲካ ትንተና በግዜ በቂ ትኩረትን አግኝቶ ዝግጅት እንዲደረግበት ለማስገንዘብ ነው:: አበው “አይሆንምን ትተህ ይሆናልን ጠብቅ” እንዲሉ አሸዋ ላይ የቆመ መንግስትንና ሚናውን ያለየ መሪንተከትሎ ለአደጋ ከመጋለጥ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ አድርጎ መጠበቅ ትርፍ እንጂ ኪሳራ አይኖረውም::
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
ድል ለሕዝባችን!!
_
በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com