spot_img
Thursday, November 30, 2023
Homeነፃ አስተያየትበአሜሪካ አደራዳሪነት የታሰበዉ ዕርቅ ላይ አንዳንድ ሀሳቦች

በአሜሪካ አደራዳሪነት የታሰበዉ ዕርቅ ላይ አንዳንድ ሀሳቦች

advertisement

ጸሀፊ ነጋሽ አብዱራህማን 
ተርጓሚ ጃፈር ሥዩም

ጥር 21 2014 ዓ ም 

እንደ መግቢያ

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ግጭት ለማቆም በአሜሪካ የሚመራ ድርድር እየተካሄደ መሆኑ ግልጽ ሆኗል፡፡ እንዲህ ያለው ድርድር 2 ግዙፍ የስልጣን ባለቤቶችን ይፈጥራል፤ በፈጸመው ወንጀል ጸጸትን የማያውቅ የህወሃት ስብስብ(ወይም በተለያየ ስም የተቀመጠ ህወሃትን የሚመስል ቡድን) እና የተዳከመ ማዕከላዊ መንግስት፡፡

ይህን እቅድ ለማሳካት በጦርነቱ ጉዳት ያስተናገዱትን የአማራ ክልልንና የኤርትራን መንግስት ከሂደቱ መነጠልን ይጠይቃል፡፡

ይህም የቻይናን የምስራቅ አፍሪካ የበላይነት አዳክሞ ለአሜሪካ የአጭር ጊዜ ጥቅም ይሰጣል፡፡ ለኢትዮጵያና ለቀጠናው ግን ቀውስን የሚፈጥር የረዥም ጊዜ አለመረጋጋትና ተጋላጭነት ቀመር ነው፡፡

የታህሳስ 29ኙን ምሽት ስብሃት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ከእስር በድንገት መለቀቅ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ባይደን መካከል የተደረገው የስልክ ውይይት፣ በአሜሪካ መንግስት የተሰጡ የተለያዩ መግለጫዎች፣ የኦሌሴጉን ኦባሳንጆ የትግራይ ጉዞ በሙሉ በህወሃትና በኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት መካከል የነበረውን ግጭት በአሜሪካን መሪነት በድርድር ለማቆም እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ይጠቁማሉ፡፡ 

የተለያዩ ጥያቄዎች ወደ አዕምሮዋችን ይመጣሉ፦ 

  • ከአሜሪካ ግፊት ጀርባ ያሉ ምክንያቶች ምንድናቸው? 
  • የስምምነቱ ዝርዝር ምን ይመስላል? ማን ያሸንፋል? ማንስ ይሸነፋል? 
  • የባይደን አስተዳደር ድርድሩን ለማካሄድ ለምን ፍላጎት አሳየ?
  • አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ ላይ ያላት ፍላጎትስ ምንድነው? 

ስተራቴጂያዊ ጥቅምና እና …  

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አርቃቂዎች በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ መካከል አሜሪካ የማይቆጣጠረው ጥምረት ተቀባይነት እንደሌለው በግልጽ አሳይተዋል። ኤርትራ እና ሶማሊያ በጥምረት 4,300 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን በዓለም ላይ አሉ ከሚባሉት ስተራቴጂያዊ ቦታዎች አንዱ በሆነዉ አካባቢ የባህር ዳርቻ አላቸው። አሜሪካ ለቻይና ጥሩ ፍላጎት ያለው የሚመስለውን እንዲህ ዓይነቱን ጥምረት አስቀድማ መግታት ትፈልጋለች። የባይደን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና የብሄራዊ ደህንነት ተቋም ቁልፍ ሰዎች ኢትዮጵያን ለሶስት አስርት አመታት ያህል ከገዙት ከህወሃት መሪዎች ጋር ያላቸውን ግላዊ ጭምር ግንኙነት ጨምሩበት።

a

ሰብዓዊ መብትን እንደ ማጥቂያ 

ፕሬዝዳንት ባይደን በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ በመጠኑ ተሳትፈዋል። በዚህ ላይ ያለውን አስተሳሰብ በአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ላይ አሻራ ለማሳረፍ ለሚጓጓው ታናሹ እና ግልፍተኛው አንቶኒ ብሊንከን ሰጥቶቷል። ባይደን ቃለ መሃላ ከመፈጸሙ ከረጅም ጊዜ በፊት፣ አንቶኒ ብሊንከን እና ጄክ ሱሊቫን (የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የሆኑት) ሚዛኑን ወደ ትግራይ አማፂያን እንድያጋድል ለመጠበቅ የተነደፈውን የጣልቃ ገብነት ፖሊሲ አዋቅረዋል። ጦርነቱ በጀመረበት በቀናት ዉስጥ፣በህዳር ወር መጀመሪያ ላይ፣ ብሊንከን እና ሱሊቫን በኢትዮጵያ መንግስት እየተፈጸሙ ነዉ ስለሚሉዋቸዉ የጦር ወንጀሎችን እና የዘር ማፅዳትን ያለ ገለልተኛ ማረጋገጫ ይጽፉ ነበር። የባይደን አስተዳደር 1,000 የሚገመቱ መከላከያ የሌላቸው ንፁሀን ዜጎች የታረዱበትን የማይካድራ ጭፍጨፋ የፈጸሙትን የትግራይ ዘር አጥፊዎች ድርጊት ተቃውሞ አያውቅም። በአማራ እና አፋር ክልል ላይ የደረሰውን አስደንጋጭ ውድመት፣ የሰው ህይወት መጥፋት፣ መደፈር እና ሆን ተብሎ የተደረገ የንብረት እና የኢኮኖሚ ውድመት ያንን ተከትሎም በክልሎቹ ህይወትን ወደ ኋላ አስርታት አመታት እንዲመለሱ ሲደረግም በዚህም ጉዳይ ላይ የአሜሪካ መንግስት ዝምታን መርጧል፡፡ አሜሪካኖቹ የሚከራከሩባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት ጉዳዮችን የሚያነሱት ለነሱ ሲመች ቢቻ ነው።

የባይደርን አስተዳደር በጥር 2014 ወደ ስልጣን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ ሰብአዊ መብትን እንደ ማጥቂያ መሳሪያነት ተጠቅሟል፡፡ የነደፉት እቅድ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካንን ምኞት ያደናቅፋሉ ተብለው የሚታሰቡትን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን፣ ኤርትራን እና አማራዎችን አጋንንት አድርጎ መሳልን ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት እውነታውን በተገቢው መንገድ ካለማቅረቡ ጋር ተዳምሮ የኦርዌላውያኑ አጋንንታዊ ስልት ሠርተዋል። አሁን ለውጭው ዓለም ወራሪው ህወሓት ተበዳይ ነው። በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ውስጥ በአማራ እና አፋር ህዝብ ላይ ስለተፈጸመው በቃላት ሊገለጽ የማይችል ወንጀል ማንም አይናገርም።

ሰብአዊ መብቶች ሲባል. . . . 

የሰብአዊ መብቶች በአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ትእዛዞችን ከዋሽንግተን ለመቀበል አሻፈረኝ በሚሉ ሀገራት እና መሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል ማጥቂያ መሳሪያ ነው።


ለምሳሌ፤ ሳውዲ አረቢያ የሰብአዊ መብት ጥሰት ከሚፈጽሙ ሀገራት ግንባር ቀደሟ ነች። ከሕግ ውጪ የሚፈጸሙ ግድያዎች፣ በወህኒ ቤት የሚፈጸሙ ማሰቃያ ቅጣቶች፣ በእስረኞችና በስደተኞች ላይ የሚፈጸሙ ኢሰብአዊ ወይም ክብርን የሚያዋርዱ የጭካኔ ወንጀሎች፣  ሐሳብን በነፃነት መግለጽና በፕሬሱ ላይ የተጣሉ ከባድ አፈናዎች በሳኡዲ በየዕለቱ የሚፈጸሙ መደበኛ የመብት ጥሰቶች ናቸው፡፡ 

በዚህም ሳይገደብ ሳውዲ የገባችበት የየመን ጦርነትም በምድር ላይ ለተፈጸመ ከባድ የጦር ወንጀሎች ዓይነተኛ ምሳሌ ነው። ላለፉት ሰባት ዓመታት እየተናጠ ነው። የአሜሪካንን የጦር መሳሪያ በመጠቀም ከአረብ ሀገራት እጅግ ሀብታም የሆነችዋ ሀገር ከድሃ የአረብ ሀገራት አንዷን ለማጥፋት ጦርነት ገብታለች። የዩናይትድ ስቴትስ የማዕቀብ ወይም የዘር ማጥፋት ክስ ስጋት የለባትም።

አዲሱ የአሜሪካ እሽክርክሪት 

የመንግስት ለውጥ የለም፡፡ መንግስትን ማሽመድመድ ግን ይኖራል፡፡ 

የስርዓተ መንግስት ለዉጥ እንደማይኖር  ለጠ/ሚ  ዶ/ር አብይ አህመድ ቃል የተገባላቸው ይመስላል።  ይሁን እንጂ መንግስትን ማኮላሸት ስርዓት ግን ይኖራል፡፡ 

የመንግስት ስርዓት መኮላሸት መግለጫዎች ምን ምን ናቸዉ?

አሜሪካ  በኢትዮጲያ  መንግስት አንገት ላይ ገመዷን ካጠለቀች በኋላ ደረጃ በደረጃ የሚተገበሩት ክንዉኖች እንደ አዳላጭ ቁልቁለት መንገድ ቀስ በቀስ ይዘው ገደል የሚየገቡ ናቸው።  እነኚህም፣

  • በህወሃት ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል እኩልነትን የሚፈጥር የግዳጅ የተኩስ አቁም ስምምነት 
  • ለህወሃት ታጣቂዎች መረጃ እና ሎጂስቲክስ  አገልግሎቶችን በመስጠት ለሚታወቁ የውጭ ኃይሎች እና የእርዳታ ድርጅቶች ወደትግራይ ያልተገደበ ጉዞ እንዲያደርጉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
  • ህወሃት የሚያደርሳቸዉ ትንኮሳዎችን ተከትሎ መንግስት ለሚሰጣቸው ወታደራዊ ምላሾች የዉጭ አካላት ጣልቃ እንዲገቡ አሳማኝ ምክንያት ለመስጠት ሲባል በንጹሃን ላይ እንደደረሰ ጥቃትና  የጅምላ ጭፍጨፋ አድርጎ ማቅረብ  
  • በትግራይ ስማይ የኢትዮጵያ አውሮፕላኖች እንዳይበሩ መከልከል፤ ያልዚያም  በ “ሰላም አስከባሪ”  ስም የውጭ  ወታድሮችን በአካባቢው ማስፈር
  • በሃገሪቱ ከባባድ ቅድመ ሁኔታዎችን የሚጠይቁ የመልሶ ግንባታ ዕርዳታዎችን እንቁልልጭ ማለት ወይም በሌላ አነጋገር በሁሉም ደረጃ ኢትዮጵያ እርዳታ ከመሰጠቷ በፊት ብቁ መሆኗን ማስመስከር አለባት እንደማለት ነዉ።
  • የህወሃት  መሪዎች የዘረፉት  ሀብታቸው  እንደማይወሰድ ዋስትና መስጠት 
  • የህወሃት መሪዎች በሰሩት ወንጀል እንደማይከሰሱ ዋስትና መስጠት 
  • አማራን  እና  ጎረቤት ሀገር ኤርትራን  ማግለል እና የሆነ ቀለበት ውስጥ ማስገባት፦ ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ በብሄር የርስ በርስ  ክፍፍልን  ከመፍጠሩም ባሻገር ከጎረቤት ሃገር   ኤርትራ ጋርም የሚኖረውን ግንኙነት ያሻክራል፡፡ 
  • የተዳከመ ማዕከላዊ መንግስትን ፈጥሮ፣ ከትግራይ ተቀናቃኞች እንዲሁም በሌሎች የክልል የጦር አበጋዞች ውጊያ በመጥመድ የበለጠ ማዳከም።
  • በስተመጨረሻም ከምዕራባዊያን የምግብ፣ የገንዘብና የሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍን  የሚከጅል ጥገኛ እና የተዳከመ ማዕከላዊ መንግስት፣ መፍጠር

ከኢትዮጵያ አንጻር የተሻለው ውጤት ምንድነው?

እ.ኤ.አ. በ1991 ህወሃትን  ወደ ስልጣን ለማምጣት የአሜሪካንን ተሰሚነት እና ኃያልነት የተጠቀመው አሜሪካዊው አንጋሽ ሄርማን ኮኸን ብዙ ኢትዮጵያውያን መስማት የሚፈልጉትን በቅርቡ በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል። 

ኢትዮጵያ ውስጥ ህወሀት የማይቀረውን የሚቀበልበት ጊዜ አሁን ነው። የአብይ መንግስት ከፍተኛ  ወታደራዊ የበላይነት አለው። የትግራይን ህዝብ ከከፋ ችግር ለመታደግ ህወሀት ህልውናውን ማቆም አለበት፣ አመራሩም ወደ ስደት መሄድ አለባቸዉ። የይቅርታ ስደት ሄርማን ኮኸን ኢትዮጵያውያንን እንዴት ማታለል  እንዳለበት በደምብ ያውቃል እናም ይህንን ሀሳብ የሰነዘረው ኢትዮጵያውያንን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ለመውሰድ  እና ስሜታቸውን እና አስተያየታቸውን ለመለዋወጥ አስቦ ነዉ።

ህወሓት እጁን ከሰጠ፣ ትጥቅ ከፈታ እና መሪዎቹም ከታሰሩ ወይም ከተሰደዱ፣ ሁሉንም ያሳተፈ ብሔራዊ ውይይት ለኢትዮጵያ በርካታ ችግሮች መፍትሄ ሊያፈላልግ ይችላል።

ግን ይህ የሚሆን አይመስልም፡፡. ህወሃት  እንዲጠፋ ማድረግ የአሜሪካ ፍላጎት  አይሆንም። አሜሪካ ዋና ዋና የህወሓት አመራር አባላትን ወደ ካናዳና መሰል ሀገራት ጥገኝነት እንዲያገኙ ማድረግ ትችላለች፡፡  ይህ አይነቱ እርምጃ ለህወሀት አዲስ ስም መስጠትን ተከትሎ ሊመጣ ይችላል።

 ነገር ግን ህወሓትና ርዕዮተ ዓለሙ የሚያመረቅዝ ቁስል ሆነው ይቀጥላሉ።  

በአሜሪካ አደራዳሪነት የሚካሄደው  ድርድር ምናልባትም  ትግራይን ከጥቃት መጠበቅን ያካተተ እቅድ ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባትም ከአየር በረራ ነጻ የሆነ ክልል ወይም እንደ ወልቃይት  በመሳሰሉ ቦታዎች ላይ የ ዉጭ ሃይሎችን ማስፈር፡፡  

የተዳከመው ማዕከላዊ መንግስት ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን በመፍታት እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ለሚሄደው የክልል መንግስታት እና ተያያዥ ሚሊሻዎች ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጥ በስራ ተጠምዶ እንዲቆይ ይሆናል፡፡   በዋና ዋና የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ለመሰማራት የሚያስችል ጥንካሬ እና የመተላለፊያ ይዘት የማይኖረው ከመሆኑም በላይ ትልቅ ጥምረት ውስጥ ለመግባትም ሆነ ከውጭ ኃይሎች ጋር በእኩል ደረጃ መደራደር ጥንካሬና ችሎታው አይኖረውም፡፡ 

***

አሜሪካ  በኢትዮጵያ ላይ ያላት ፖሊሲ በአፍሪካ አህጉር ላይ የምትከተለው ፖሊሲ ቅጥያ  ነዉ፡፡ 

በአፍሪካ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መነሻ ምንድን ነው?   

በአፍሪካ የአሜሪካ የዉጭ ፖሊሲ በሁለት ምሰሶዎች ላይ የቆመ ነዉ፡፡ 

ምሰሶ I.  የአሜሪካን ዓለም አቀፋዊ የበላይነት ማስከበር፦ የአሜሪካ ፍላጎት በሰፊው ለምትቆጣጠረው ዓለም አፍሪካን መገልገያ ማድረግ ነዉ፡፡   

ዩናይትድ ስቴትስ ከሴፕቴምበር 11 ጀምሮ ሽብርተኝነትን የመዋጋት ስራ ላይ ተጠምዳ ቆይታለች፡፡ ለዚህም አፍሪካ አስፈላጊ የምትባለው በወታደራዊ የአሜሪካ ፖሊሲ ቅርጽ አንጻር ነው። በዚሁ አውድ  ውስጥ፣ ጋዜጠኛው እና ደራሲው ሃዋርድ ፍሬንች እንደፃፈው፣ “አፍሪካ ይበልጡኑ ራቅ ተደርጋ እንደምትያዝ ወታደራዊ እና የጸጥታ ችግር ሆና ትታያለች” 

አሜሪካ የአፍሪካ እዝ (AFRICOM) ወይም አፍሪኮምን ፈጥራለች።  አፍሪኮም የአሜሪካ ፖሊሲ በአፍሪካ ላይ ያለውን ወታደራዊ አደረጃጀት ያሳያል። በነገራችን ላይ ካምፕ ሊሞኒየር ተብሎ የሚጠራው በአፍሪካ ብቸኛው ቋሚ የአሜሪካ ጦር ሰፈር  የሚገኘዉ በጅቡቲ  ነው። የዩናይትድ ስቴትስ አዛዥ ጄኔራል ዊልያም ዛና ባሳለፍነው ህዳር በኢትዮጵያ ውስጥ ጣልቃ  እገባለሁ ብሎ ያስፈራራው ከዚሁ ጦር ሰፈር ነው።

ከአፍሪኮም ጋር የማይተባበሩ የአፍሪካ ጦር ሃይሎች በጥርጣሬ ነዉ የሚታዩት ። ለምሳሌ የኤርትራ ጦር ለአሜሪካ መጠቀሚያነት ታስቦ ነበር።  ነገርግን ወዲያው ከውድድሩ ውጭ ሆናል።  እ.ኤ.አ. በ 2013 የወጣዉ  የዩኤስ ዘገባ የኤርትራ ጦር “በታሪክ  አስቸጋሪ በሆነው ክልል ውስጥ ጠቃሚ የአሜሪካ አጋር ሊሆን ይችላል ሆኖም ግን ለወደፊቱ ለዩናይትድ ስቴትስ ከሚጠቅመው ጥቅም ይልቅ የበለጠ ችግር ሆኖ ሊቆይ ይችላል” ሲል  አስቀምጦታል።

ከወታደራዊ ስጋቶች ውጪ፣ አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር የምታደርገው አዎንታዊ የንግድ ግንኙነት እንደ ዘይት እና ማዕድን ባሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ዙሪያ፣ እና ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን እንደ አውሮፕላን ያሉ ቴክኖሎጂዎችን በመሸጥ ላይ ያተኮረ ነዉ ።

የአሜሪካ በጦር ሃይል ላይ ያቶከረ ስልት ሰፊ ከሆነዉ  የቻይና ኢኮኖሚያዊ እና የመሰረተ ልማት ዕርዳታ ጋር ለመወዳደር እየታገለ ነው።ር

ምሰሶ II. የነጭ የበላይነት 

 እ.ኤ.አ. በ2014 የዋሽንግተን ፖስት  ባወጣዉ  አርዕስት ፣ የምዕራቡ ዓለም፣ በተለይም አሜሪካ “አፍሪካን እንደ ቆሻሻ እና በበሽታ የተወረረች  ቦታ አድርጎ  የማየት ረጅም እና አስቀያሚ ባህል አላቸዉ ።” በአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች እና ጋዜጠኞች አስተሳሰብ አፍሪካ በአሉታዊ መነፅር ነው የምትታየው። ይህም በሁሉም ቦታ መጥፎ ዜናዎችን እና አደጋዎችን ማየት ነው”።

ቀጭን እውቀት እና ውስን የፖሊሲ ልምድ  ያላቸው ሰዎች የአሜሪካን ዲፕሎማሲ እንዲቀርጹ እና እንዲመሩ ጥሪ የሚቀርብበት ብቸኛው የአለም ክፍል አፍሪካ ነው። እንደ “ቦኖ፣ ጆርጅ ክሉኒ እና ቤን አፍሌክ ያሉ ተዛማጅነት የሌላቸው ታዋቂ ሰዎች ያለ ቦታቸው በአፍሪካ ፖሊሲ ተፀዕኖ እንዲኖራቸው ይደረጋል

ትራምፕ  የዲፕሎማሲውን ጭንብል አውልቆ  የአፍሪካ አገሮችን “የመጸዳጃ ጉድጓድ  ሃገራት ”  ነበር ያሏቸዉ  ለዛም ወቀሳ ደርሶባቸዉ  ነበር ። ኪሲንጀር “የደቡብ አፍሪካ ነጮች ካሉበት ንቅንቅ አይሏትም ” ብሎ ነበር። ሬጋን አፍሪካውያንን “ዝንጀሮዎች” ብሎ ነው የጠራቸዉ ። ከግል ጭፍን ጥላቻ በዘለለ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከአፓርታይድ ደቡብ አፍሪካ ጋር በድብቅ የሚሠራና የሚረዳ የዘረኝነት ዓለም አቀፍ አንጃ መሪ ነበረች።

በአጭሩ፣ በዘር ላይ የተመሰረተዉ  የአሜሪካ ፖሊሲ በአፍሪካ ላይ እንደሚከተለው ሊጠቃለል ይችላል። 

  1. ስደተኞችሽን  አትላኪብኝ ፤
  2. በሽታዎችዎን ወደ ባህር ዳርቻዎቼ አታምጪብኝ፣ (ብሎም ኦሜክሮን የተሰኘዉን የኮቪድ ዝርያ  መገኘቱን ተከትሎ በደቡ አፍሪካ ተጓዦች ላይ በባይደን የተጣለዉ ምክንያት የለሽ የጉዞ ማእቀብ እና ክልከላ) እና 
  3. አሸባሪዎችን አትፈልፍይ

***

ወደ ኢትዮጵያ እንመለስ

አሜሪካ የህወሃት ታጣቂዎች አበረታችና የነፍስ አባት ሆና ቆይታለች ። በመሆኑም የግጭቱ አካል ሆና ስለቆየች  ገለልተኛ አስታራቂ ልትሆን  አትችልም።

ታዲያ አሜሪካ አደራዳሪ የሆነችበት  ስምምነት ምን ሊሆን ይችላል?

ከ1991 በላይ  አርቃችሁ መመልከት አያስፈልግም ። በ1991 በዩኤስ-አማላጅነት የተደረገው ድርድር አናሳ ጥቂት ቡድን  ወደ ስልጣን እንዲመጣ አስቻለ። በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መልክ ወደ ሶስት አስርት አመታት የሚጠጋ አምባገነንነትን እና ዘረፋ አስከትላል ። ይህ ስርዓትም  ለአሜሪካን ፍላጎት  በሚገባ አገልግሏል። ነገር ግን በኢትዮጵያውያን ላይ በቁሳዊም ሆነ በስነ-ልቦናዊ ሁኔታ ላይ ከባድ ጉዳት አምጥታል። ህወሀትም  እራሱን ብዙ የውጭ ዕርዳታና የብድር ገንዘብ  ለመዝረፍ በቃ። አመራሮቹ ቢጠሯቸው የማይሰሙ ሀብታሞች  ሆኑ ። የኢትዮጵያ ህዝብ ተጎድቶ ሃዘኑን እና ጠባሳዉን ይዞ ቀረ።

ኢትዮጵያውያን እነዚህን የህልውና አደጋዎች እንዴት መቋቋም ይችላሉ?

  1. አንድነትን  ማጠናከር:-  የኢትዮጵያ አመራር፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ዲያስፖራዎች  በጋራ   ሆነዉ  የተገኘውን አንድነት  ለማጠናከር ዘወትር ጥረት ማድረግ አለባቸው።
  1. የሚዲያ አካላት  አስፈላጊነት:-  በእዉነተኛ መረጃ አስደግፎ  ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን አቋም  ማንጸባረቅ። ይህንን ለማድረግ መንግስት የኢትዮጵያን ጉዳይ ፍትሃዊነት አለምን ለማሳመን እና አሉታዊ ትርክቶችን  ለመቀልበስ በሚገባ የተደራጀ፣ የሰለጠነ የሚዲያ ሃይልን  መምራት አለበት።
  1. መልሶ ግንባታ፦ . ሁሉም ኢትዮጵያውያን በተለይም በዲያስፖራ የምንገኝ ወገኖች ህወሓት የአማራና የአፋር ክልሎች ላይ  እያደረሰ ያለውን ውድመት ለመመከት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋችንን እንቀጥል።
  1. የ “No More” እንቅስቃሴ እና የፓን አፍሪካን ትግል ማጠናከር 

ጸሀፊውን ለማግኘት 

Email: ethioanalyst@gmail.com
__
በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here