spot_img
Wednesday, May 29, 2024
Homeአበይት ዜናከአፋር ሕዝብ ፓርቲ ስለ ወቅታዊው የትግራይ ወረራ የተሰጠ መግለጫ

ከአፋር ሕዝብ ፓርቲ ስለ ወቅታዊው የትግራይ ወረራ የተሰጠ መግለጫ

አፋር ህዝብ ፓርቲ
ጥር 20/2014 ዓ.ም
ሰመራ፤አፋር፤ ኢትዮጵያ

አምባገነኑ የትግራይ ወራሪ ቡድን ካለፈው አንድ አመት ጀምሮ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ከ21 በላይ የአፋር ወረዳዎችን በከባድ መሳሪያዎች ማለትም በመድፎች፣ ታንኮች፣ ዙ-23፣ ቢኤም፣ ዲሽቃ ወዘተ ያለ ምንም  ርኅራሄ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ንጹሃን ዜጎቻችንን ከመጨረሳቸውም በላይ በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች እጅግ ዘግናኝ የሆኑ ኢ-ሰባአዊ ድርግቶችን ማለትም፤ አስገድዶ መድፈር፣ የንብረት ዘረፋ፣ ለአርብቶ አደሩ የኑሮ ዋስትና የሆኑትን እንስሳት በጥይት በመፍጀት የእብሪታቸውን መጠን ለሀገራችን ሕዝቦችም ሆነ ለሰላም፣ ዲሞክራሲና ሰብአዊ መብቶች ጠበቃ ነን ለሚሉት ለአለምቀፍ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በይፋ አሳይቷል።

ሆኖም ግን እነዚህ አለም አቀፍ ድርጅቶች እና ግለሰቦች አሸባሪው ህወሃት በስልጣን በነበረበት 27 አመታት ከኢትዮጵዊያውያን ጉሮሮ በመንጠቅ ባካበተው ዶላሮች በመደለል ከእውነት በተቃራኒ ቆሟል። እነዚሁ ተቋማትና ግለሰቦች የህወሃት አሸባሪ ቡድን በአፋር እና የአማራ ሕዝብ ላይ ስለአደረሰው ጉዳት ትንፍሽ ሳይሉ የትግራይ ሕዝብ እና ክልል በልዩ ሁኔታ እንደተበደለ የአለምን ሕዝብ እያደነቆሩ ይገኛሉ።

መንግስት የመጀመሪያውን የጦርነት ምእራፍ አጠናቅቃለሁ ብሎ ቢያውጅም አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ሃይል በሰሜን በሚያጎራብቱት የአፋር ወረዳ ቀበሌዎችን እየወረረ ነው። የአፋር ሕዝብም ወረራውን እየመከተ እና አስፈላጊውን መከላከል እያደረገ ባለበት ወቅት ከጥር 15/2014 ጀምሮ በከባድ መሳሪያዎች በመታገዝ ከ40,000-50,000 የሚገመቱ ጀሌዎቹን ልክ እንደ አንበጣ መንጋ በማሰለፍ በመጋሌ፣አብአላ፣በራህሌ፣ኮነባ እና ኢሬብቲ ወረዳዎች ላይ መጠነ ሰፊ ወረራ እያካሄደ ይገኛል። በመሆኑም የአፋር ሕዝብ ፓርቲ የዚህ እብረተኛ እና አሸባሪ ቡድን ወረራ በአስቸኳይ መቀልበስ እንዳለበት ለመላው የአፋር ሕዝብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

እነዚህ የትግራይ ህዝብ ሞት እና መከራን ካላዩ የማይደሰተው እና  በሰው ደም ላይ መረማመድን የለመዱ ሰው በለውዎች በትገራይ  ህዝብ ላይ ዘምን ተሸጋሪ ጠባሳን የሚያስቀር እና ለረዥም ዘመናት አብሮት የኖሩትን ወንድም እና ጎረቤት የሆነው የአፋር ህዝብ ጋር የሚያቃቀር ስራ ስሰሩ ቆይቷል እየሰሩም ይገኛሉ በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ይህን ሀይል አስቁሞ መሰረታዊ የሆኑ ጥያቄዎችን መጠየቅ አለበት፡፡

ወያኔ በአሁኑ ሰዓት የሚጠቀመው ፕሮፖጋናዳ አንዴ የቀይ ባህር አፋሮች ሌላው ጊዜ ደግሞ የኤሪትራ ወታደሮች ወጉኝ ብሎ በሬ ወለድ ወሬን በማናፈስ የአለምን ህዝብ ለማደናገር ሞክሯል፡፡ የኤሪትራ ወታደሮች ትግራይን መውጋት ቢፈልጉ ረዥም ድንበር ከሀገራችን ጋር አላቸውና መውጋት ይችሉ ነበር፡፡

ይህ በሰው ደም ራሱን ማቆየት የለመደው ወራሪ ሃይል በ ሀምሌ 9/2013 የየሎ ወረዳን አንዲሁም ጭፍራን እና ካሰጊታን ሲወር አፋርን አንፈልገም ጉዳያችን ያለው ከማዕከላዊ መንግስት ነው በማለት ለማጭበርበር ቢሞክርም ሳይሳካት ቀርቷል፡፡ አሁን ደግሞ ወደ ማሃል ሀገር ሳይሆን በተቃራኒው ወዳሉ ወረዳዎች ፊቱን ማዞሩ የአፋርን ደም በከንቱ ለማፍሰስ ካለው ፅኑ ፍላጎት የሚመነጭ መሆኑን በግልፅ ያሳያል፡፡

አሸባሪው እና ወራሪው ቡድን የአፋርን ህዝብ ለመከፋፈል ሲሞክር “ እኛ የምንፈልገው የብልፅግና ሰዎች ናቸው” ማለት አፋር ጠላት እና ወዳጅ በማስመሰል ሞክሯል  ስለ እውነት ግን ይህ ሃይል አፋርን ለማንበርከክ ቆርጦ የተነሳ መሆኑን የአፋር ህዝብ ሊገነዘበው ይገባል፡፡ እንደማሳያ በጋሊኮማ በመጠለያ ውስጥ የነበሩ ሴቶች ህፃናት እና አቅመደካሞች በበረት ውስጥ እንደጠላት የተረሸኑት ግመሎች እና ከብቶች ፤ በየሎ ወረዳ ስለ ሰላም ሲሰብኩ የተገደሉት ሀጂ ብልዓይቶን ጨምሮ የሀገር ሽማጊሌዎች፤ከአብዓላ ወደ ኢረብቲ ከከባድ መሳሪያ በመሸሽ ላይ ሳሉ የተገደሉት ህፃናት፤ የተደፈሩት ሴቶች የዚህ ቡድን እኩይ አላማ ግልፅ አድርጎ ያሳያል፡፡ በመሆኑም ይህን ግልፅ የሆነውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ሁሉም የዓለም ህዝብ፤በተለይም የአፋር ህዝብ ሊገነዘበው  እና በዛው ልክ ራሱን ለመከላከል መዘጋጀት ይገባል፡፡

   1. የክልሉ መንግስት የክልሉ ሕገመንግስት በሚደነግገው መሰረት በአካባቢወ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያውጅእና ጠንከር ያለ ኮማንድ ፖስት እንዲያደራጅ እንጠይቃለን::

   2.ሁሉም የአፋር ሕዝብ ስንቁን እና ትጥቁን አደራጅቶ በማንኘውም ጊዜ ሊከሰት የሚችልን ተጨማሪ ወረራን ለመመከት መዘጋጀት አለበት፡፡በተመሳሳይ መንገድ አፋርን በመክዳት ለጠላት መንገድ በማሳየት አፋር እያስወጉ ያሉትን ትቂት ባንዳዎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ካልሆነ ግን የአፋር ህዝብ ከገቡበት ገብቶ ተገቢውን ቅጣት አንደሚቀጣቸው ልናስታውሳቸው እንወዳለን::

   3.በሁሉም አካባቢ የምትገኙ አባላቶቻችን እና ደጋፊዎቻችን ለዘመቻው በምትፈለጉበት መስክ ሁሉ ለሚደረግላችሁ ጥሪ ዝግጁ ሆናችሁ እንድትጠባበቁ::

   4.የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ወራሪው እና አሸባሪው የትግራይ ኃይል በወረራው ከያዛቸው የአፋር አካባቢዎች እስካልወጣና ከባድ መሳሪያዎቹ ለአፋር ሕዝብ ስጋት ወደ ማይሆኑበት ረደጃ እስካልወረደ እና እስኪረጋገጥ ድረስ ከአሸባሪው ቡድን ጋር የሚደረግ ወይንም ሊደረግ የታሰበ ድርድር ካለ የአፋር ሕዝብ ይህንን አካሄድ የማይቀበል መሆኑና እንደ ሀገራዊ ክህደት የሚቆጥር መሆኑን በጥብቅ ያሳስባል።

   5.የትግራይ ሕዝብ ጆሮ ካለህ ሰማ። ለጥቂት እድሜአቸውን ከበሉ እና ልጆቻቸውን በአውሮፓ እና አሜሪካ አንደላቀው እያኖሩ አንተን በጦርነት እያስጨረሱህ መሆኑን አውቀህ ከችግሩ ራስህን ነጻ አውጣ። ሽማጊሌዎቹ እንደሆኑ ወደ ውጭ የሚወጡበት መንገድ በማጣታቸው እንጂ ከአንተ ጋር የተቀመጡት ለአንተ እና ለክልሉ ሁለንተናዊ ሰላም እና እድገት አለመሆኑን ማወቅ ይጠበቅብሃል።

   6.ለአሸባሪው ህወሃት ጥብቅና የቆማችሁ አንዳንድ ሀገሮች እና አለም አቀፍ ድርጅቶች የምናሳስባችሁ ጉዳይ ፣ የአፋር ሕዝብ እየታረደ፣ በከባድ መሳሪያ አየተደበደበ፣ እና አየተራበና በአሸባሪው ክልል እየደረሰበት ያለውን ግፍ በመደገፍ ጭራሽ ለአሸባሪው ቡድን በምታደርጉት ደጋፍ እሰከ ቀጠላችሁ ድረስ የአፋር ሕዝብ ለዚህ እኩይ ተግባራችሁ ምንም አይነት ተብብር አንደመይሰጥ ከወዲሁ እናሳስባችኋለን።

   7. በመንግስት መግለጫዎች ጭምር የአፋርን ችግር ችላ ለማለት ሲሞከር እያስተዋልን በመሆኑ ይህ ጉዳይ በአስቸኳይ ሊታረም ይገባል፡፡ በተጨማሪም የፌዴራል መንግሰት አውጆት የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማንሳት ያቀረበው ሀሳብ የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ያላገናዘበ በመሆኑም በተለይ በአፋር እና አማራ ክልሎች ላይ እንዲቆይ እናሳስባለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ህዝባችን ራሱን እንዲከላከል አስፈላጊውን እገዛ እንዲደረግለትና መሰላም ስም ማዘናጋቱ አንዲቆም ከፍተኛ የስዓዊ ቀውስ ስላለ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጠው እናሳስባለን፡፡

የአፋር ህዝብ ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

ጥር 20/2014 ዓ.ም

ሰመራ፤አፋር፤ ኢትዮጵያ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here