ከአማራና ከአፋር ህዝብ ጎን እንቆማለን!
በአገርና በህዝብ ላይ የሚፈጸመውን ወረራና ውድመትን እናወግዛለን
የኢትዮጵያ ህዝብ ባጠቃላይ የአማራው ህዝብ በተለይ ለነጻነቱ ለመበቱና ለህልውናው እንቅፋትና ጠንቅ የሆነውን የወያኔን የጎሳ ስርአት ለማስወገድ ያካሄደው ትግል በአብይና ግብረ አበሮቹ በረቀቀ የተንኮል ዘዴ የህዝብን ንጹህ ቅንነትና ኢትዮጵያዊ ፍቅሩን በማታለያነት በመጠቀም፣ትግሉ እንዲቀለበሰ ሆነ። ይህም ዛሬ የአገራችንን ሕልውናና የህዝቧን አንድነት ከምንጊዜውም የበለጠ ስጋት ላይ አድርሶታል። የአማራ ህዝብ ለኢትዮጵያ አገሩ ታማኝነትንና ጀግንነትን ስለ አበረከተ፣ ማንነቴ ኢትዮጵያዊነቴ በማለቱ፣ ኢትዮጵያዊ አብሮነትን በመውደዱ፣ አንድነትና ፍቅርን በመምረጡ፣ጽንፋዊ ልዩነትን፣ የሀሰት ትርክትና ጥላቻን ባነገቡ ጎሰኞች በጠላትነት ተፈርጆ ለጥቃት እንዲዳረግ ሆኖ ቆይቶል። ይህ ጥቃት በቅድሚያ በአማራ ህዝብ ላይ ቢነጣጠርም ዛሬ ለአማራ ብቻ ሳይሆን ራሱን በኢትዮጵያዊነት ለሚያይ ሁሉ እጣ ፋንታ መሆኑን በአፋር ህዝብ ላይ የሚደርሰው ግድያና ወረራ ሌላ ገጽታዊ ምስክር ነው።
ዛሬ ለሚገደሉትና ለሚሰቃዩት ወገኖቻችን ማዘን ብቻ ሳይሆን፣ ትግላቸውና የፈሰሰው ደማቸው ከንቱ እንዳይሆን፣ለአማራው ህዝብ ህልውናና ደህንነት እንዲሁም ለኢትዮጵያ ትንሳኤ መንፈሳዊ የኃይል ምንጭ ይሆን ዘንድ የጀግኖቻችንን አላማ ህያው ማድረግ ይጠበቅብናል። ስለዚህ በአማራና በአፋር ማህበረ ሰብ ላይ የሚካሄደው ጦርነት፣ በደልና ጥቃት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት መሆኑን በመገንዘብ፣ በአንድ ድምጽ ድርጊቱን ማውገዝና ማስቆም ወቅቱ የሚጠይቀው የጋራ ሃላፊነት ነው። ይህ የጥፋት ሂደት በአፋጣኝ ካልተገታ ግን ለትውልድ የሚተላለፍ ልዩ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ቀውስ ከፊታችን ተደቅኖ የሚጠብቀን መራራ ሃቅ ይሆናል።
ስለዚህም አገራችንና ሀዝባችንን ከዚህ አስከፊ የጥፋት መንገድ ለማዳን በሚከትሉት የትግል ዘርፎች እንደንተባበር ጥሪ እንዳርጋለን፤
- ስለዚህ የአማራና የአፋር ህዝብም ከሌሎች ኢትዮጵውያን ወገኖቹ ጋር በመተባበር የኦነግ/ወያኔን አላማ የሚያራምደው፣ አብይ አህመድንና የሚመራውን አገር አጥፊ አስተዳደርን አስወግዶ ኢትዮጵያዊ መንግስት መመስረት አገርንና ህዝብን ከጥፋት ያድናል፣ ዘለቄታዊ መፍትሄም ነው ብለን እናማናለን። ይህ አገራዊ የነጻነት መፍትሄ እውን የሚሆነውም ዛሬ በተቀነባበረ መንገድ የኢትዮጵያ ጣምራ ጠላቶች፣ በአማራ ህዝብ፣ በአፋር ህዝብና ባጠቃላይ በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርሱትን ጉዳትና ያወጁትን ጦርነት በአግባቡና በሚመጥነው ደረጃ ስንታደግ ብቻ ነው።
- የችግራችን ምንጭ የሆነውን በአብይ አህመድ የሚመራውን የወያኔ /ኦንግ የጎሳ ስራአት ባስቸኮይ ማስውገድ እጅግ አስፈላጊና አጣዳፊ ተግባር መሆን አለበት። በዶ/ር አብይ የሚመራው ጸረ ኢትዮጵያ፣ ጸረ አማራ፣ የኦነግ/ወያኔ የጎሳ የፖለቲካ ስርአትን ማስወገድ የማንኛውም ህሊና ያለው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሊያስተውለው የሚገባ ወሳኝ ወቅታዊና ቁልፍ ጉዳይ ነው ብለን እናማናለን።የወያኔ/ኦነግ/ኢህአደግን መሰርታዊ አላማና ግብ ለማስካት አስፍፈጻሚ የሆነውን አብይ አህመድን ከስልጣን አስወገዶ ኢትዮጵያዊና ህዝባዊ የሽግግር መንግስት መመሰርት ወሳኝና አስፈላጊ የመፍትሄ ሂደት ነው።
- ወንጀለኛውን አብይ አህመድ በሙሉ ሃላፊነት ተጣያቂ በማደርግ የመጀመርያው የአገር ማዳን ተግባር ሲሆን፣ በአማርና በአፋር ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን ኢሰብአዊ ተግባር፣ እልቂትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ማሳወቅና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ በመወሰድ የአብይና ግብረ አበሮቹ ለፍርድ እንዲቅርቡ የሚያስፈልገውን ዲፕሎማሲያዊና ህጋዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፣
- ኢትዮጵያውያን በአብይ መንግስትና ኦነግ/ወያኔ የኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ ጥቅሞች ላይ ማእቀብ እንዲደረግ ማደረግና፣ ማህበራዊ ድጋፍ ማሳጣት። የአማራው ማህርሰብ ለአገር ከፍተኛ ግብር ከፋይ ሆኖ ነገር ግን በሚከፍለው ግብር የመንግስት ጥበቃና አገልግሎት ሳይሆን የሚያገኘው የመንግስት ጥቃት የሚፈጽምበት ህዝብ በመሆኑ ለመንግስት ግብር አለመክፍልና ተመሳሳይ አድማና ማእቀብ ማድረግ፣
- አመታት ያስቆጥሩት በደንቢደሎ በአማርነታቸው የታፈኑት ወጣት ተማሪዎች ጉዳይ እስካሁን ድረስ መልስ አልተገኘም፤ ለእንዚህ ወጣቶች ህይወት፣ ሆነ በየእለቱ በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመው ግፍና አረመናዊ ተግባር መንግስት ነኝ ባዩ እያወቀው የሚደረግ ተግባር ብቻ ሳይሆን በዋናነት የሚያቀነባብረውና የሚመራው የዘመናችን ናዚ/ሂትለር የኦንጉ አብይ አህመድ መሆኑን በመገንዘብ ተጥያቂ ማድርግ።
- የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ርስቱና ቅርሱ መላው ኢትዮጵያ መሆኑ አጠያያቂ አይደልም፣ ህያው እውነት ነው። ሆኖም ዛሬ በራያና ቆቦ፣ ወልቃይት ጠገዴና የመሳስሉ የአማራ ሀዝብ ታሪካዊ የመኖሪያ ቦታውችን ለመቀማትና የኦነጉ አብይ አህመድ ለወያኔ መደራደሪያ እጅ መንሻ ለማደርግ የሚደረገውን መሰሪ ቁማርና ሴራን አጥብቀን እናወግዛለን ከህዝቡም ጎን እንቆማለን።
- ጸረ ኢትዮጵያው ወያኔና የአብይ አስተዳደር የፈጠሩት ጦርነት ይህ ነው የማይባል ከፍትኛ የህዝብ እልቂትና የእኮኖሚ ውደቅትና ድህነትን አስከትሎል። ለደረሰውም ውድመት የአብይን መንግስትና ወያኔን ህጋዊና ታሪካዊ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደርጋለን፣ ጦርነቱንም በስቸኮይ እንዲቆም እንጠይቃለን። አብይ አህመድ በሰልጣን ለመቆየት ማንኝውንም አረመናዊ ተግባር ሁሉ እንድሚያድርግ በተደጋጋሚ ገልጾል፣ በተግባርም አሳዩታል፣ ይህ ተግባሩ እንድይቀጥል ማድረግ የእኛ የኢትዮጵያውያን ሃላፊንት ነው።
- በተለይም በጦርነት ወቅት የመከራ ገፈት ቀማሽ ሴቶችና ልጆች በመሆናቸው አስፈላጊውን እርዳታ ሁሉ እንዲያገኙ ማድረግ አጣዳፊ ማህበራዊ ግዴታችን ነው። ባለፈው አራት አመት በሚሊዮን የሚቆጠሩ በርካታ ሲቶች በገዛ አገራቸው ተሰደዋል፣ ተፈናቅውል፣ ተግድለዋል። ነፈሰ ጡሮችና ህጻናት ቤታቸው በላያቸው ላይ ፈርሶ መንገድ ላይ ወድቀዋል፣ በርካታ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ጭካኔ ለተሞላበ ጥቃትና ሞት ተጋልጠዋል። ይህን አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ለመወጣት አስፈላጊውን ሁሉ እንድናደርግ አለም አቅፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የትብብር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
- በዚህም መሰረት፣የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የሴቶች ድርጅት በዶ/ር አብይ መሪነት በአማራውና በአፋር ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን ማንኛውን አይነት ጥቃት አጥብቀን እያወገዝንና የተቃጣውንም የጥፋት ዘመቻ ለማስቆም ማንኛውንም መንገድ በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዳንደርግ፣ ለጥቃት ኢላማ ለተደረገው ህዝብ፣ እንዲሁም ለሴቶችና ለልጆች ድምጽ በመሆን የሚያስፈልገውን ሁሉ እንዳርግ ዘንድ ይህንን የትግል ትብብር ጥሬ እናስተላፋለን። እኛ ኢትዮጵያውያን ሴቶች፣ እንደ ጀግኖች ቅድመ አያቶቻችን ተባብረን ከተነሣን አላማችንን ከማሳካት የሚያግድን ምንም ሀይል አይኖርም፣ የአማርን፣ የአፋርን ህዝብ ከጥቅት እንዳናልን ኢትዮጵያም ትነሳለች።
ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ጀግንነት ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች!!
አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት
የካቲት 2014