spot_img
Sunday, May 26, 2024
Homeነፃ አስተያየትየኢሀዲጋዊያን ፓርቲ የመጀመሪ ጉባኤውን ያደርጋል

የኢሀዲጋዊያን ፓርቲ የመጀመሪ ጉባኤውን ያደርጋል

አዎ አልተሳሳታችሁም፣ የኢሀዲጋዊያን ፓርቲ ነው ያልኩት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ጉባኤዎች እና ሚዲያ ከሚገልፁት ብልፅግና በስተቀር ያው ኢህአዴግ እንዳለ አለ፡፡ እጅግ የሚበዙት የፖለቲካ አመራሩ የፖለቲካ አስተሳሰባቸው፣ ድርጊታቸው አሁንም ኢህአዴግ ነው፤ የተቀየረ ነገር ካለ ኢህአዴግ ጃኬቱን ገልብጦ ለብሶ ብልፅግና መስሎ ቁጭ ብሏል፡፡ ለአብነት ያህል፤

  1. አሁንም ያለው የኢህአዴግ አወቃቀር ነው፡፡ 

ብልፅግና ግንባር ወይም ቅንጅት ሳይሆን አንድ ፓርቲ ይመስላል ነገር ግን እንደ ኢህአዴግ የኦሮሞ ቅርንጫፍ፤ የአማራ ቅርንጫፍ፤ የደቡብ ቅርንጫፍ፤ ወዘተ በሚል የተከፋፈለ ነው፡፡

  1. የፖለቲካ ማጠንጠኛው አሁንም ዘረኝነት፣ ጎሰኝነት ነው፡፡ 

በአገሪቱ በሁሉም አካባቢ በሚባል ደረጃ በአንድ ስፍራ ከአንድ ብሄር በላይ የተለያዩ ብሄሮች ያሉበት ነው፡፡ ነገር ግን ያለው የፖለቲካ አመራር ወይም ተወካይ የሚመራውን ወይም የተወከለበትን ስብጥር ዜጋ ሁሉ መሰረት ያደረገ ፖለቲከኛ አድርጎ የሚያይ ሳይሆን፣ ራሱን የጎሳው ተወካይ አድርጎ የተቀመጠ ነው፡፡ ለምሳሌ የአንድ ከተማ ወይም ቀበሌ የፖለቲካ አመራር የከተማው የተለያዩ ብሄሮች ወካይ አመራር መሆን ሲገባው፣ አሁንም ያው እንደ ኢህአዴግ ፖለቲካ የኦሮሞ ወይም የአማራ ወይም የሲዳማ ወዘተ የፖለቲካ አመራር ሆኖ የተቀመጠ ነው፡፡

  1. ዘረኝነት፣ ብሄርን መሰረት ያደረገ ግድያ እና መፈናቀል እየከፋ የመጣበት ነው፡፡ 

በአገሪቱ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ያልታየ ብሄርን መሰረት ያደረገ ሰቅጣጭ ግድያ እና መፈናቀል በአሁኑ የኢህአዴግ መንፈስ ልጅ (ኢሀዲጋዊያን ብልፅግናዎች) ወቅት በስፋት ይታያል፡፡ (እዚህ ጋር ግን የሶማሊ ክልል፣ የጋምቤላ ክልል እና የአፋር ክልል አብዛኛውን አመራር አይመለከትም፡፡ በተለይ የሶማሊ ክልል ሙስጠፌ ከፍተኛ ምስጋና ይገባቸዋል)

ሌላው ግር የሚል ነገር የሚፈጥረው ደግሞ ቀደም ሲል አገር አገር ይሉ የነበሩ የረፈደ ብሄረተኛ (ጎሰኛ) ስሜት ማቆጥቆጥ ጀምሯል፡፡ ይሄም ዘላቂ ጠቃሚ ፋይዳ የሌለው ከረፈደ ብቅ ያለ ገለባ አስተሳሰብ ነው፡፡

  1. ቀደም ሲል የተሻለ አካታችነት የነበረው ደቡብ ክልል በኢሀዲጋዊያን (የኢህአዴግ መንፈስ ልጅ የሆኑ ብልፅግናዎች) ዱለታ በሚመስል መልኩ እየፈራረሰ ይገኛል፡፡
  2. የኢሀዲጋዊያን ብልፅግና ድርጅት፣ ፖሊሲ የማስፈፀም አቅም የሌለው የተልፈሰፈ ድርጅት ነው፡፡ የወጡ ፖሊሲዎች በመንፈስ አባቱ (ኢህአዴግ) ጊዜ እስከ ቀበሌ ድረስ ተፈፃሚ የማድረግ አቅም ነበረ፡፡ ከፌደራል እስከ ክልል እና ቀበሌ ድረስ ተፈፃሚ የማድረግ አደረጃጀት ነበረ፡፡
  3. የኢሀዲጋዊያን (የኢህአዴግ መንፈስ ልጅ የሆኑ ብልፅግናዎች) የፖለቲካውም ሆነ የፐብሊክ ተቋሙ አመራር በአምቻ ጋብቻ (ዝምድና) እና የመጠቃቀም ባልንጀራዎች አደገኛ ትስስር (networking) የተሞላ ነው፡፡ የአገሪቱን ዕምቅ አቅም ስራ ላይ የሚያውል አይደለም፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩም የክልሎች የመፈፀም እና የማስፈፀም አቅም ምን ያህል እንደሆነ የሚያውቁም አይመስልም ወይም ያውቃሉ የሚያስብል ጠንካራ አመላካች ነገር የለም፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ የፌደራል ተቋማትንም ሆነ እራሳቸው የሾሟቸውን ባለስልጣናትንም የሚያውቁአቸው አይመስሉም፡፡ እርግጥ ነው ተሸዋሚዎቿቸው ለቴሌቪዥን ሾው በጣሙን የሚጨነቁ ናቸው፡፡ ይሄ ከሆነ ኢሀዲጋውያን ብልፅግናዎች አገሪቱን ወዴት እንደሚወስዱአት አነጋጋሪ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሆይ ሁሌ የጫጉላ ሽርሽር (Honeymoon) የለም፡፡ እንደ መጀመሪያው ባንወድዎትም እስካሁን እይታችን ወደ ጥላቻ አልተቀየረም፡፡ ስለዚህ ጠቅለል ሲደረግ ከቃላት ማሳመር እና ከቅዠት ፈንጠዝያ ወጥተው መሬት ላይ የሚታይ ነገር ይፈለጋል፡፡

__
በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here