ቦርከና
ሰኔ 14 , 2014 ዓ. ም.
ባለፈው ቅዳሜ በወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ በሚባል ቀበሌ የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አስተዳደር ሸኔ እያለ የሚጠራው አክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኛ ታጣቂ ባደረሰው ጥቃት ከአራት መቶ በላይ ንጹሃን የአማራ ተወላጆች አልቀዋል::
በጥቃቱ የተፈጁት አብዛኛዎቹ ህጻናት አና ሴቶች እንደሆኑ ከሃገር ውስጥ አና ከውጭ የተገኙ መረጃዎች አመላክተዋል::
ታጣቂ ቡድኑ አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ በወለጋ አና ሌሎች አካባቢዎች ባልታጠቁ ንጹሃን ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት በመሰንዘር በሺዎች የሚቆጠሩ አማራ ትውልድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ገድሏል::
የኦሮሞ ክልል እና የፌደራሉ መንግስት ባለፈው ቅዳሜ የደረሰውን እልቂት ቢያምንኑም የሟቶችን አና ተጎጂዎችን ቁጥር ይፋ አላደረጉም::
ቅዳሜ ከደረሰው የጂምላ ፍጂት በፊት ሁለቱም አካላት ሸኔ እያሉ የሚጠሩትን ቡድን “አቅሙን አዳክመነዋል ፤ በዜጎች ላይ ተጨማሪ ጉዳት ማድረስ የማይችልበት ደረጃ ላይ አድርሰነዋል” ሲሉ ከርመዋል::
ታጣቂ ቡድኑ በፌደራል እና በኦሮሞ ክልል መንግስት መዋቅር ውስጥ ባሉ አባሎች እና ደጋፊዎች ጭምር ድጋፍ እንደሚደረግለት ይነገራል ::
ከሁለት ዓመት በፊት ቡድኑ በወለጋ ውስጥ በርካታ የመንግስት ባንኮችን እንደዘረፈ ይታወሳል ፤ ከድርጊቱም ጀርባ የመንግስት አካላት ጭምር አንደነበሩበት መዘገቡ ይታወቃል::
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ እና በርካታ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መንግስት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ሃላፊነቱን መወጣት ባለመቻሉ ጠንከር ያለ ትችት ሰንዝረውበታል::
__
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena