“የአማራ ጥያቄ የሰብአዊነትና የኢትዮጵያዊነት ጥያቄ ነው”
ሰኔ 13፣ 2014
ከቀናት በፊት በሽዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በወለጋ ታርደው እንደውሃ የፈሰሰው የንጹሃን ደም ደንታ ያልስጠው የዐብይ አሕመድ ብልፅግና መንግሥት፣ ወልቃይትን ለወያኔ በሬፈረንደም አሳልፎ ለመስጠት ሽር-ጉድ እያለ መሆኑን ከአገር ቤት የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ::
ይህን የክህደት እቅድ ካለፈው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማ ድንፋታ መረዳት የማይክብድ ቢሆንም፣ ከወለጋው ዘር-ፍጅት ጋር አሁን አስታክኮ መቅረቡ፣ በአማራው ቁስል ላይ ጨው እንደመነስንስ ሆኖ ይታያል:: ከዚህ በፊት በተደጋጋሚነት (በመተከል፥በራያ፣ በኣጣዬ፣በከሚሴ፣በደራና በምንጃር) የመንግሥት ተባባሪነት የታየባቸው ጥቃቶች በኦነግ ፊታውራሪነት ሲፈጸሙ፣ “የሞተው አማራ ብቻ አይደለም፤ የአማራ አክራሪዎች የቀሰቀሱት ነው” በማለት የመንግሥት ሹማምንት አሹፈዋል፣ ግብዝነቱን አሁንም ቀጥለዉበታል።
ትናንት የአማራው ደጀን የሆነውን ፋኖን አዳክሞና ከጭቁኑ ሕዝብ ጎን ቆመዋል ተብለው የተጠረጠሩትን የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ሁሉ በእስር ቤት አጉሮ፣ ዛሬ ይህ በጭካኔና በማን አለብኝነት ሊታወጅ የታለመው እቅድ፣ የአማራውን ሕዝብ አንገት አስደፍቶ፣ የኦሮሙማን የበላይነት ለማረጋገጥ የተቀነባበረ ውጥን መልክ እንዳለው የማያሻማ ሀቅ ነው::
ስለሆነም፣ በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፣ በተለያየ አቅጣጫ አማራውን ለማዳከምና ለማጥፋት የሚደረገውን ሴራ ለማቆም ያለባችውን የታሪክ ሃላፊነት እያስገነዝብን፣ ከዚህ በታች ስማችን የተዘርዘረው ድርጅቶች በበኩላችን አስፈላጊውን አስተዋፅዖ ከማበርከት እንደማናፈገፍግ፣ ለሰላም ወዳጁ ወገናችን ቃል እንገባለን::
በተጨማሪም፣ በምዕራባዊው ዓለም የምትኖሩ፣ ለሰላምና ለፍትህ የቆማችሁ ወገኖች፣ የዐብይ መንግሥት፣ በቅርቡ በወለጋ ለተፈጸመው ወንጀል አላፊነት ወስዶ፣ ገዳዮቹንና ተባባሪዎቻቸውን ለፍርድ በአስችኳይ ካላቀረበ፤ እንዲሁም ወልቃይትን እና ሌሎችንም የአማራ ክፍሎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለወያኔ አሳልፎ የመስጠት ሙከራ ካደረገ፣ በአንድነት ዉጤታማ እርምጃዎችን ለመዉሰድ በዝግጅት እንድትገኙ እጅግ አጥብቀን ልናሳስብ እንወዳለን። ከእነዚህም ዋና ዋናዎቹ፤
1. በሁሉም አካባቢ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የማያቋርጥ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ፤
2. ዘረኛነትንና ጭቆናን ሊያጠናክሩ የሚችሉ የኢኮኖሚ ድጋፎችን በስልጣን ላይ ላለው መንግሥት ከማድረግ መቆጠብ (በተለይም የዉጭ ምንዛሬ ምንጮችን ማድረቅ)፤
3. በሰብአዊ መብት ጥሰት መጠየቅ የሚገባቸውን የመንግሥት ባለስልጣኖች በዓለም ፍርድ ቤት ክስ መመስረት፤
4. የአማራውን ሕዝብ ሰቆቃ ለዓለም ሕዝብ፣ ወዳጅ መንግሥታትና ዓለም-አቀፍ ድርጅቶች ባለማቋረጥ በማስረዳት፣ በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት ከዉጭ የሚያገኘውን መዋዕለ-ንዋይ ድጎማ እንዲቀነስ ማድረግ፤
5. በተለይም፣ በሰሜን አሜሪካና በኣውሮፓ ፓርላማዎች በቀረቡት የተጠያቂነት ረቂቆች ውስጥ ጸረ ኢትዮጵያ አንቀጾች ተወግደዉ፣ የአማራው ሕዝብ ሰቆቃዎች እንዲካተቱ መትጋት፤
6. እንዲሁም በማንኛዎችም የሰላምና የመልሶ ግንባታ ድርድር ላይ አማራው በቁመቱ ልክ፣ የእኔ በሚላቸው፣ በሚተማመንባቸው እና በመረጣቸው ሃቀኛ መሪዎች እንዲወከል ያልተቆጠበ ድጋፍ መስጠት ናቸው።
ፈራሚ ድርጅቶች;
1. All Shewa Ethiopian People Multipurpose International Association 2. Adwa Great African Victory Association (AGAVA)
3. Amhara Dimtse Serechit
4. Amhara Wellbeing and Development Association
5. Bay Area Ethiopian Community Association, California 6. Communities of Ethiopians in Finland
7. Concerned Amharas in the Diaspora
8. Ethio-Canadian Human Rights Association
9. Ethiopian Community Association in Atlanta
10. Ethiopian Community Association of Northern Virginia
11. Ethiopian Dialogue Forum (EDF)
12. Freedom and Justice for Telemt Amhara
13. Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause
14. Global Amhara Coalition
15. Gonder Hibret for Ethiopian Unity
16. Major Lemma Woldetsadik Memorial Foundation
17. Network of Ethiopian Scholars (NES)
18. Radio Yenesew Ethiopia
19. Selassie Stand Up, Inc.
20. The Ethiopian Broadcast Group
21. Tibibir
22. Vision Ethiopia (VE)
23. Worldwide Ethiopian Civic Associations Network (WE-CAN)
__
በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena