spot_img
Tuesday, June 25, 2024
Homeነፃ አስተያየትየአክራሪ ኦሮሞዎች የዘር ማጥፋት ዘመቻ ወዴት?

የአክራሪ ኦሮሞዎች የዘር ማጥፋት ዘመቻ ወዴት?

ከሐይለገብርኤል  አያሌው

በኦሮሚያ ክልል የዘር ማጥፋት ዘመቻ በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ሲተገበር ቆይቷል:: ሚኒሊካውያን ሰፉሪ ወራሪና ነፍጠኛ በሚል ቅጥያ ግልጽ ጭፍጨፉ ከተከፈተበት ሦስት አስዕርተ ዐመታት ተቆጥሯል:: የመንግስት ሃላፊዎች ጽንፈኛ ብሄረተኞች የአንድነት ፖለቲካ አቀንቃኞች ጭምር በየግዜው አማራውን ነጥሎ የማጥቃቱን ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ግጭት: ነውጥ : ቀውስ በሚል ሲሸፉፍኑት ኖረዋል:: አማራው ሕዝብ ላይ በተደጋጋሚ የተፈጸመው ጄኖሳይድ እንኳን አለም አቀፉ ማህበረሰብ የገዛ ወገኑ እንኳን በቅጡ ችግሩን ሳይረዳ ቆይቷል:: 

ሃቁን በማወሳሰብና በተቀናጀ ፕሮፓጋንዳ የተዘናጋው የአማራው ሕዝብ የከበበው አደጋ የሚመጥን አደረጃጀት እንዳይኖረው አድርጎታል:: ቢያንስ ግልጽና የተደራጀ አደጋውን የሚተነትን መረጃ ለአማራው ባለሃብቶችና ሰራተኞች ቢኖር ኖሮ ዛሬ ላይ የወደመው በቢሊዮን የሚግመት መዋዕለ ንዋያቸውን ልማት ላይ ከማዋላቸው በፊት ደጋግመው እንዲያስቡና አማራጭ ሁኔታዎችን ለመገምገም በቻሉ ነበር:: በገጠሪቱ ኢትዮጵያን ተሰማርቶ የሚኖረው እርሶ አደር አማራም በልጆቹ ፊት ከመታረዱ በፊት ከአጥቂዎች እራሱ ለመከላከል በተዘጋጀ ነበር:: ነገር ግን ድርጊቱ በመድበስበሱ መፍትሄ ፍለጋ ላይ እንዳይተኮር እድርጏል:: ዛሬም ያው የተለመደ ማምታታት ቀጥሏል:: በድቅድቅ ጨለማ በአራዊት መንጋ ተከባ የምትቃትት ሃገር ገጽታዋ እንዳይበላሽ በሚል ሰበብ በዘራቸው ብቻ የጄኖሳይድ ሰለባ የሆኑ ወገኖቻችን አለም ጮሆ እንኳ እንዳይታደጋቸው የመረጃ ማዛባት ሲሰራበት ቆይቷል ::አሁንም ቀጥሏል::

ሽብርን ወንጀልንና ነውርን በስሙ እለመጥራት በተጎጂዎች ላይ መሳለቅ ብቻ ሳይሆን የፍትህ ሂደትን ማዛባት ይሆናል:: አካፉን አካፉ አለማለት ዶማ አያደርገውም:: እውነትን በመደበቅ የሚጸና መንበር : ሃቅን በመድፈቅ የሚዘልቅ ሰላም አይኖርም:: በተለይ ጉዳት ከደረሰበት ወገን የሚቀርብ ምሁር ጋዜጠኛ ይሁን ፖለቲከኛ ከእውነታው በራቀ አቅጣጭ ሕዝብን ለማሳሳት ሲሞክር ያስተዛዝባል ያስወነጅላል:: 

ጃንደረባ ሎሌ በጌታው ብልት ይፎክራል እንዲሉ አንዳንድ የደረሰው ሰቆቃ የማይሰማቸው ለስልጣን ቅልውጥ የቋመጡ ምንደኞች ሃቁን ለማዛባት መስመር የሳተ ውሸት ጀምረዋል;; ዛሬም ቀጥለውበታል:: እንደነዚህ እይነት አድርባይ ቅጥረኞች ከደረሱበት የሞራል ዝቅጠት አንጻር ነገ ሱሪያችሁን አውልቁ ቢባል ለምን ሳይሉ ቀበቷቸውን ለመፍታት የማያመነቱ ሕብርተሰባዊ አረሞች ልንታገላቸው ልናጋልጣቸምው ይገባል ::

በሃሰት መስካሪነትና በተዛባ ትንተና የሚገኝ ውጤት የለም:: ተራ የፖለቲካ ሂሳብ መቀመር መቼም መፍትሄ ሆኖ አያውቅም:: ለመንግስትም አይጠቅምም ለሃገርም አይበጅም:: ዛሬ ያለምንም ክርክር ተጎጂዎች በአደባባይ ወጥተው በማንነታችን ነው የታረድንው ሲሉን ; አማራን አሳደህ ግደል የሚል ግልጽ ቅስቀሳ እየሰማን ድርጊቱን እንዴት በስሙ መጥራት ያቅተናል:; የስም ዝርዝር ይዘው የሚያርዱና ንብረት የሚያወድሙት እክራሪ ኦሮሞዎች የፈጹሙት ጄኖሳይድ ከሩዋንዳው በምን ይለያል?:: የናዚ የጽዮናውያን ጭፍጨፉ በሃገራችን ከሆነው ያለውን ልዩነት ምንድን ነው?

አማራን አሳዶ መግደል በውስጥ የሚታወቅ የኦነግ ድርጅታዊ ፖሊሲ እንደነበር በይፉ ከምናውቀው በላይ ከፈረሱ አፍ እንዲሉ ከራሱ ከኦነግ አመራር የተነገረንን እውነት እዚህ ላይ ልጠቅሰው ግድ ይለኛል::

ጊዜው የሕወሃት ፍጻሜና የለውጡ ዋዜማ ላይ ነበርን:: የአንድ አማራ ሊቀመንበር የነበረው አቶ ንጉሴ አዳሙና የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ባለበት በተደረገ ውይይት የቀድሞው ኦነግ የበሗላው በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው ኦዲፍ አመራር የነበረ በግዜው በጸረ ወያኔው ትግል በጋራ እብሮን የተሰለፈ ወዳጃችን ቃልበቃል እንዲህ በሚል ነበር የነግረን::

ከቤቴ ስወጣና ኦነግን ስቀላቀል ማንኛውንም አማራ የተባለ ለመግደል ነበር:: እዛ ውስኔ ላይ ለምን እንደደረስኩ ያን ያህል ምን እንዳጨከነኝ ብትጠይቁኝ በእርግጥ በውል አላውቅም ::ብቻ ዛሬ ላይ ሳስበው ስህተት እንደሰራሁ ተገንዝቤያለሁ በአጋጣሚም በእጄ የሰው ሕይወት ባለማለፉም ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ:: ለእናንተ ለወንድሞቼ ይሄን ሃጢያቴን የምንዘዘው ከልብ በመጸጸቴና ፈጣሪም እንዲምረኝ ነው:: እናንተም ይቅር እንደምትሉኝ እተማመናልሁ:: (ሳግ እየተናነቀው በጥልቅ ስሜት ሆኖ) የአማራን ሕዝብ በቅጡ ሳንረዳ የያዝነው አቋም ምን ያህል ለኦሮሞ ጉዳት እንደነበር አሁን ነው አብዛኞቻችን ያወቅንው::የአማራ ሕዝብ ኦሮሞ ወንድሙን እንዴት እንዳልረሳ የኦሮሞ ደም ደሜ ነው በሚል ግንባሩን ለጥይት ሰጥቶ እውነተኛ የቁርጥ ቀን ወንድም እንደሆነ አሳይቶናል:: (በግዜው በጎንደርና በባህር ዳር ስለኦሮሞ ወገናዊነት በእደባባይ የተስተጋቡት መፈክሮች በማንስት ነው::) ካለፈው የስህተት መንገድ ወጥተን ሕዝባችንን በሚጠቅም መስመር ላይ በጋራ ልንቆም ይገባናል:: ነበር ያለን::

ይህ ግለሰብ ቁልፍ የደርግ መንግስት ሚንስትር የነበሩት የአቶ ተስፉዬ ዲንቃ የቅርብ ዘመድ ነው:: ግለሰቡ ዛሬ ያ በግልጽ ተናግሮ የተጸጸተበትን እንባ እየተናነቀው የተናዘዘውን ንስሃ እንደገና ጥሎ መጽሃፍ ‘ውሻ ወደ ትፉቱ ይመለሳል ‘ እንዲል የተፋውን እንደገና እየላሰ ሽብር ሁከትና የእርስ በእርስ መጋደሉ እንዲቀጥል የሳይበር ሰራዊት በመሆን ሰሞኑን ለደረሰው እልቂትና ውድመት ነዳጅ በማርከፍከፍ የበኩሉን ሲገፉ አይተናል:: ግለሰቡ እከሌ ነው ብሎ ከነምስሉ ማውጣት ይቻላል:; ቁም ነገሩ ግለሰቡን በግል ለመንቀፍና ለማሳጣት አይደለም:: የኦሮሞ ጠባብ ብሄረተኞች አማራን የማጥፋት ፍላጎትና ጄኖሳይድ የመፈጸም ጥማት ምን ያህል ጥልቀት እንዳለው ለማሳየት ያህል ነው::

የአማራና የኦሮሞን ሰላምና አንደነት በሰለጠነ ውይይትና በወንድማማችነት ለመፍታት በተደረጉ ጥረቶች ውስጥ ለረጅም ግዜ ተሳትፎ አድርጌያለሁ:: እንዳውም በአማራ ፖለቲካ ውስጥ ከቆዩት ከማንም በላቀ በአማራና በኦሮሞ ኤሊት መካከል ያለውን መራራቅ ለማርገብና ወደቀድሞ አብሮነት ለመመለስ አቅሜ የፈቀደውን ተወጥቻለሁ:

ከዶር መራራ ጋር በሕብረት ጥላ ስር በመተሳሰብና በመናበብ የ1997 ምርጫ ድረስ አብረን ዘልቀናል:: የስደቱም ፖለቲካ ከተቀላቀልን በሗላም ሕብረትን በመወከል ከኦነግ ጋር በተደረጉ ድርድሮችና ውይይቶች ላይ ተሳትፌያለሁ:: አቶ ዳውድ ኢብሳ የኦነግ መሪ ከሆኑ በሗላ በተደረገ ውይይትም የትውልዱን ስሜት ለማጸባረቅ ሞክሪያለሁ:; ኦነግ ከታሪክ እስረኝነት ተላቆ ዘመኑን የሚያዋጅ የፖለቲካ መስመር እንዲይዝ በግልጽ አንስቻለሁ:; ኦሮሞን ከኢትዮጵያ የሚነጥል አቅጣጫ አንድን ማህበረሰብ ኢላማ ያደረገ አካሄድ ለሃገሪቷም በተለይም ለኦሮሞ ሕዝብ ሕልውና ፍጹም አደገኛ እንደሚሆን ወገናዊ ስጋታችንን ሳንደብቅ ገልጸንላቸዋል::

በቅቡም ከለውጡ በፊት ገና ከዋዜማ አንስቶ ከነአቶ ሌንጮ ኦዴግ ጋር በጣም ተቀራርበን ለመስራት ሞክረናል:: ከኦዴግ ከፍተኛ አመራሮች የዛሬው የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪዎች ከእነ ሌንጮ ባቲ ከእነ ዶ/ር ዲማና በየደረጃው ካሉ አንጋፉ የድርጅቱ መሪዎች ጋር በከፍተኛ መቀራረብ ስለሃገራችን መጻዔ እድልና ስለሕዝባችን ሰላም የአቅማችንን ለማበርከት ሞክረናል:: ከድርጅትና ከብሄር በላይ እጅግ የላቀ ፍጹም ወንድማማችነትን ገንብተን እንደታላቅና ታናሽ ወንድም እንተያይ የነበረው የፓርቲው ዋና ጸሃፊ ምርጥና መተኪያ የለሽ ወንድሜ መካሪዬ ጏዴ አቶ ዘውዴ ጉደታ ጋር የነበረን ግንኙነት እጅግ የሚያስቀና ነበር:: ዘውድሻ ነብሱን ይማረው በብዙዎቻን ልብ ትቶት የሄደው የመልካምነት አሻራ በየትኛውም የአክራሪ ኦሮሞ ጭካኔ የማይደበዝዝ ዝንተ አለም አብሮኝ የሚኖር ትዝታ ነው:: 

ከኦዴግ መሪዎች ጋር በስፉትና በጥልቀት ተወያይተናል:: በኢትዮጵያ ሰላምና የተረጋጋ የፖለቲካ ስርዐት ለማምጣት በብዙ መክረናል:: በጁሃር መሃመድ ይመራ የነበረው የኦሮሞ ፖለቲካ ክንፍ በሃይማኖት አክራሪዎች መጠለፉን ከሗላውም አደገኛ አጀንዳ ያነገበ እንደሆነ ስጋታቸውን ደጋግመው እጋርተውናል:; የጁሃር አቅጣጫ ለኦሮሞ ሕዝብ ጭምር የማይበጅ እንደሆነ ደጋመው ነግረውናል::ለመፍትሄውም አማራው ተደራጅቶና ተጠናክሮ ከኦሮሞ ወገኑ ጋር በጋራ በመቆም ሊመጣ ከሚችለው አደጋና ሃገር ከብተና ለመታደግ እንዲዘጋጅ በግልጽ ሲነግሩን ነበር:: በጁሃር የሚመራው የOMN የፕሮፓጋንዳ እንቅስቃሴ ካውንተር ለማድረግ በአቶ ሌንጮ የሚመራው ኦዴግ የእራሱን ሚድያ እከመመስረት ደርሶ ነበር::

ይህን ሁሉ መቀራረብና አብሮነትን ከነእቶ ሌንጮ ጋር ስናደርግ ትላንት ምን እንደተደረገና ምን እንዳደረጉ ሳናውቅ ቀርተን አልነበረም :: እነ እቶ ሌንጮ ከሕወሃት ጋር ተባብረው ዛሬ ሃገራችን ላይ መርግ የሆነው ሕገመንግስት እንዳረቀቁ አልዘነጋንም:: በአርባጉጉ በበደኖና በወተር ዘግናኝ የዘር ማጥፉት ዘመቻ ያላቸውን ድርሻ በማስረጃ ጭምር እናውቃለን:: ነገር ግን የትላንቱን ስቆቃ ለታሪክ በመተው በመጪው ግዜ ሊኖር ለሚገባ ስላምና አብሮነት ቅድሚያ በመስጠት በቀና መንፈስ አብረን ተሰልፈን ለመስራት ብዙ ጥረት እድርገናል:: የደረሰው ሰቆቃ ዘንግተን ቁስሉ ሳይሰማን ቀርቶ አልነበረም;; አሁን እየሆነ ያለው እንዳይመጣ ሕዝብ እንዳያልቅና ሃገር እንዳይፈርስ የስህተቱን የፖለቲካ መስመር ለማረም ከመስራቾቹ የቀረበ አይኖርም ከሚል ቅንነት ነበር:

በእርግጥ አብዛኞቹ የኦዴግ መሪዎች ለዶር አብይ መንግስት አማካሪና ደጋፊ በመሆን የተሰለፉ ቢሆንም ከዘገየ የያዙት ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር አብሮ የመስራትና የመኖር ፖሊሲ በጽንፈኛና አክራሪ የኦሮሞ ቡድኖች እንዲቀጥል በመደረጉ ይሄው ዛሬ ለደረስንበት የዘር ማጥፉት ዘመቻ ምክንያት ሆኗል::

ያለው መንግስት ሃላፊነቱን በቅጡ መወጣት ካልቻለ : የኦሮሞ ማህበረሰብ መሪዎች በግልጽና በድፍረት ወጥተው ትውልዱን ካላረሙት አማራንና ሌሎች ማህበረሰቦች ላይ የሚደረገው ዘር ተኮር ጭፍጨፉ በከፉ መልኩ ለመቀጠሉ መገመት ነብይ መሆን አይጠይቅም:; አሁን በተለይ በኦሮሚያ ያለው ወጣት ለደረሰበት ሰብዐዊነት መንጠፍና ሞራል ውድቀት ለ27 የወያኔ የአገዛዝ አመታት የተዘራበት የጥላቻ ስብከት ውጤት ነው:: ወጣቱ ሳይወድ በተጋተው የተዛባ ትርክት የስህተት አቅጣጫ መያዙ ባያስገርምም በምሁርነታቸው አንቱ የተባሉት በምዕራቡ አለም ከሌላው ሕዝብ ጋር የመኖር ልምድ ያዳበሩ የኦሮሞ ብሄረተኞች የሚያካሂዱትን የዘር ጥላቻና ፍጅት ቅስቀሳ ለሚያይ ገና ብዙ ፈተና እንደሚጠብቀን ማሳያ ይሆናል::

ከዚህስ ወዴት?

የአክራሪው የኦሮሞ መንጋ የሚመራበት መርሕ ባይኖርም ሊያሳካው ያቀደው የጠራ አጀንዳ ግን ዛሬ ላይ ግልጽ ሆኗል:: ኢትዮጵያን አፍርሶ በመቃብሯ ላይ ምናባዊቷን ኦሮሚያ መመስረት ነው:: ለዚህም ግቡ ስኬት መንግስትን በአመጽ ለማፍረስ የሄደበን እርቀት እያየን ነው:: አክራሪው የኦሮሞ የሽብር መንጋ ጥፍሩን ሲነቅሉት ከሰው በትች አድርገው ሲረግጡና ሲንቁት የነበሩት ሕወሃቶች ጫማ ስር በመበርከክ ሃገር የማፍረስ ተባባሪ ሆኗል:: መንጋው አልፎም ተርፎም በአካባቢው ካሉት ጸረ ኢትዮጵያ ሃይላትና ከኢትዮጲያ ታሪካዊ ጠላት ከግብጽ ጋር ተቀናጅቶ ይገኛል:: በመላው የሃገራችን ሕዝብ ላይ በተለይ በአማራው ሕዝብ ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅኗል:: 

በአሁኑ ወቅት የሃገሪችን ሕልውና በግልጽ የተንጠለጠለው በሃገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ላይ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም:: በሃገራች ያሉት ተቋማት ከመሪው ውጪ በራሳቸው ቆመው ለመራመዳ መቻላቸው እጅግ አጠራጣሪ ነው:: ይህን የሚረዱት አክራሪ ኦሮሞዎች ከስልጣን የተባረሩት ወያኔዎች እና የሃገራችን የቅርብና የእሩቅ ጠላቶች ጠቅላይ ሚንስትሩ ለማስወገድ የማይወጥኑት ሴራ እንደማይኖር መገመት ከባድ አይደለም::

ማዕከላዊው መንግስት ፈረሰ ማለት በደቡብና በምዕራብ የኦሮሞ አክራሪ በሰሜን ወያኔ በምስራቅ የሱማሌ አክራሪዎች ሃገሪቱን የጦርነትና የፍጅት ቀጠና በማድረግ ሃገር የማፍረስ ሕልማቸውን ሊያሳኩ መሞከራቸው 

አይቀርም:: መንግስት ቁርጠኝነትና ሃገርን የመታደግ ተነሳሽነት ካለው የመክላከል ብሎም የማጥቃትና የመደምሰስ ቁመና እንዲኖረው ችሎታ ያላችውን የየዘርፉን ባለሙያዎችን ከፖለቲካ ወገንተኝነት ባሻገር በግዜ ከጎኑ ሊያሰባስብ ይገባል::

የመንግስት አካላት ሰላም ወዳድ የኦሮሞ ተወላጆች የአማራው ማህበረሰብ እና የተቀረው ኢትዮጵያዊ በጋራ ሊቆም ሽብርንና ሽብርተኞችን ሊያወግዝ ይገባል:: የባለፈው ይቅርና የሰሞኑን የዘር ማጥፉት ዘመቻ ያለምንም ማንቆለጻጸስ በስሙ ሊጠሩት ወንጀለኞቹም : በጄኖሳይድ ደንብና አግባብ እንዲጠየቁ ማድረግ የመንግስት የፖለቲካና የሲቪክ ተቋማት ግዴታ ጭምር ነው::

ከላይ እንደገለጽኩት አማራን ሊገል ከቤቱ የወጣው የቀድሞ ወዳጄን ጨምሮ አጠቃላይ ትውልዱን ከተቆራኘው የጥላቻ ደዌና ጨለምተኝነት ለመገላገልና መፍትሄውን ለመሻት ግልጽና ችግሩን ተኮር አቅጣጫ ግድ ይላል:: ለዘመናት የተዘራ የጥላቻ ፖለቲካና የተዛባ የታሪክ ትንተና በሃቅ በማስረጃና በውይይት ሊገራ ካልቻለ ግዜና ምክንያት እየጠበቀ የጄኖሳይድ ዙሩ ይቀጥላል:: 

ሁሌ ሌላውን እየገደሉና ንብረቱን እያወደሙ መቀጠል አይቻልም :; የሰውም ተፈጥሮው አይፈቅድም:: መንግስት ስርዐት ያሲዛል የኦሮሞ ሽማግሌዎች ይመክራሉ :; ይህ የጥቂቶች ክፉት ነው :: ብዙሃኑን ኦሮሞ አይወክልም :: ሃገር ሊያፈርስ ከሚችል ምላሽ ይልቅ በትዕግሥት እንመልከት እየተባለ ዛሬ ላይ ተደርሷል:: አማራው ነፍጠኛ ወራሪና ሰፉሪ እየተባለ በሃገሩ የጄኖሳይድ ሰለባና መብት የለሽ ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ ቆይቷል:: ይህ ትዕግስት እየተሟጠጠ ጽዋው እየሞላ ብቀላን እየወለደ ከመጣ የሚሆነው መገመት ይከብዳል;; ጸጥ ያለ ውሃ ጥልቀቱ ረጅም ነው እንዲሉ : ነፍጠኛ የተባለው ሕዝብ ለሺ አመታት ያልተሰበረ እንኳን ጨፈቃ ያያዘ መንጋና ግሪሳ ከሰማይ አይሮፕላን ከምድር ታንክና መትረየስ ጋር በጎራዴ ተዋግቶ ታሪክ ሰርቶ ታሪክ ያስረከበ ሕዝብ ነው:: የተበደለ ሲያምጽ የተገፉ ሲቆጣ ሊያደርስ የሚችለው እልቂት ማንንም አትራፊ አያደርግም:: የሚበጀው ሰላማዊ መፍትሄ ነው:; የሚያዋጣን ፍቅርና አንድነታችን ነው:: ግድያና ማፈናቀሉ ይብቃ!!! 

እግዚያብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

ጠላቶቿን እግሯ ስር ይጣልልን!!!

አሜን

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena 

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here