spot_img
Saturday, April 20, 2024
Homeነፃ አስተያየትግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ:-

ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ:-

ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ:-
አልማዝ አሸናፊ አሰፋ
ሰኔ 21 , 2014 ዓ.ም.
IMZZASSEFA5@gmail.com

ምንም እንኳ ለአመራሮ ያለኝንን ድጋፍ እንድቀንስ ወይም እንዳቆም የሚያደርጉኝ አጥጋቢ ምክንያቶች ባይኖሩም : በእመራሮ ላይ ያለኝን ቅሬታ ከማሰማት አልቆጠብም:: በእርግጥም ትውልደ ኢትዮጵያና የአሜሪካ ዜግነት የተጎናፀፍኩ በመሆኔ እንደ ውጭ ዜጋ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባትን አልደግፍም:: ግን ህዝብ ጥቃትና በደል ሲደርሰት ሳይና ስሰማ በሰብእዊ ጉዳይ ላይ ከመናገር አልቆጠብም:: በጥሩ ስራዎ እንደምደግፎት ሲሳሳቱና ግብዝነቶ ሲታየኝ ሃቁን ሳላሰማዎት አላልፍም ምክንያቱም ሕይወት የተሞላችው በካሮት ብቻ ወይም በዱላ ብቻ ሳይሆን ካሮትንና ዱላን አቅፋ በመያዟ ነው:: ሆኖም አገራችን ከገባችበት አጣብቂኝ ለመውጣት ያልቻለችበት ምክንያት የሚመሯትና ሊመሯት የሚቃጡት ሁሉ ያንድ ወገን አቋም በመያዛቸው ብቻ ነው:: ይህም የመግባቢያ ስልታቸው ካሮትና ዱላ ከማለት ካሮት ብቻ ወይም ዱላ ብቻ ምርጫቸው ስላደረጉት ነው:: አገር ሃይማኖት ብሔር ጎሳና ዘር የሚቆጠረው የሰው ልጆች ሲኖሩ ነው:: የሰው ልጆች ፈጅተን ከምድር ገፅ አጥፍተን እኛ ያቺ አገር ያቺ መሬትና ያቺ ክልል ላይ ተንደላቅቄ እኖራለሁ ብሎ የሚያስብ ከንቱ ጅል ነው:: የኦነግ ሸኔም ሆነ ማንኛውም ጎሰኛና ጎጠኛ የያዘው የዘር ፍጅት አቋም እግዚአብሄርን የሚያሳዝን ሰይጣናዊ ድርጊት ነው:: በወለጋ ውስጥ በአማራ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመው ኢሰብዓዊ ግድያ ተሰምቶት ያልጮኸና ያልተቆጨ አመራር ለሕዝብ ያስባል ለማለት ያጠራጥራል:: ግድያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ስለበዛ በየጊዜው እየወጡ ሃዘኖን ለሕዝብ ቢገልፁ የገዳዮችን ዓላማ ማለትም የግድያው ዜናና ወሬ የበለጠ ያደፋፍራቸዋል : ተደማጭነት ያገኛሉ ብለው አስበው ይሆንም በማለት ከለላ ልሰጦት እሞክርና መለስ ብዬ ይህኮ የንፁሃን ደም ነው:: ሕዝብና አገር በሃዘን ሲሸፈን አንድ መሪ እንደመንግስቱ ኃይለማርያምና እንደወያኔ ገዳይ መሪ ካልሆነ ማስተዛዘንና የሕዝቡን እንባ መጥረግ የጥሩ መሪ ምልክት ነው: እርሶ እርህራሄ የሎትም ለማለት ቅንጣት አላስብም:: ግን ዝምታዎ ግራ አጋብቶኛል:: ለዚህም ነው እየደገፍኮት ይህችን ደብዳቤዬን በይፋ በግልፅ በእትመት ላይ እንዲያነቧት የቦጫጨርኩኝ::

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በወለጋ በተከሰተው የንፁሃን ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ወንድሞቻችን ልጆቻችን እናቶቻችን አባቶችችን አያቶቻችን አክስቶቻችንና እጎቶችችን ጭካኔ የተሞላበት የሰው ልጆች ግድያ ከምንም የበለጠ ትኩረት ተሰጥቶት የንፁሃንን ደም ያፈሰሱ የኦኔግ ሸኔ አረመኔ ወንጀሎች ካልተደመሰሱና ለሕግ ካልቀረቡ : በሙታን ደም እጆን እንደታጠቡ ይቆጠራል:: ይህንን የምልበት ምክንያት የአንድ መንግስት መሪ ኃላፊነቱና ግዴታው ለመላው የአገሪቱ ሕዝብ እንጂ ለፖለቲካ ፓቲው አባሎች ወይም ለመጣበትና ለእደገበት ክልል መንደርና ጎሳ ብቻ አይደለም:: ክዚያም ሌላ መልካም መሪ ስብእና የተሞላበት የሰው ልጆችን በእኩል ደረጃ የሚያይ እንጂ የመጣበትን ጎሳ የሚቆጥር መሆን የለበትም:: እርሶ ለመጡበት የኦሮሞ ጎሳ ያደላሉ የሚል ግምት አላደረብኝም:: ግን ምክንያቱን ሰፊ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመረዳት በተሳነው ሁኔታ እንዲህ ዓይነት በአማራነታቸው አስከፊና አስፀያፊ የሰው ልጆች ግድያ በኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ውስጥ ተሰግስገው ባሉ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ኢትዮጵያውያን ባለስልጣኖች ድብቅ ድጋፍ በአረመኔ ኦነግ ሸኔ ሲፈፀም ያሳዩት ዝምታ ሕዝቡ በእርሶ ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርበት በሩን ከፍተዋል:: በየሶሻል ሚዲያዎችም የሚናፈሰው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኦሮሞ ጎሳና ኦሮሞነትን ከኢትዮጵያዊነት በላይ በማድረግ የኦሮሞን የተረኛነት አገዛዝ ለማጠናከር የሚሰሩ መሪ እንጂ ለመላው ኢትዮጵያ ደንታ የላቸውም የሚለውን ውንጀላ በእዚህ አሰቃቂ ግድያ ማዘኖትን ባለመግልፆት እውን ያስመስለዋል:: ለሰው ልጆች ሕይወት መጥፋት አያዝኑም አይቆረቆሩም አልልም:: በተፈፀመው ግድያ ልቦ እንደተሰበረ ላስብ እችላለሁ:: ግን ይህንን ማስረዳት የሚችሉት እርሶ ነበሩ:: እንደ አንድ አገር መሪ እንዲህ አይነት ኢሰብዓዊ ድርጊት በእርሶ አስተዳደር ዘመን ሲፈፀም ከማንም በፊት ሕዝብ ፊት ቀርበው ድርጊቱን ማውገዝና ሕዝብን ማፅናናት ነበረቦውት:: እርሶ ግን አላደረጉም:: ለምን? ይህ ዝምታ በእርሶ ላይ ለሚነሱት ሃሜቶችና ክሶች ምንጭ ነው::

የጀመሩትና ወደስልጣን የመጡበት ስራ እንዲሳካሎት እኔ እመኝሎታለሁ:: ሆኖም የራሶን አቋም አስተካክለው ለኦሮሞ ብልፅግናና ለኦሮሞ የስልጣን ተረኛነት የቆሙ ሳይሆኑ የመላ ኢትዮጵያውያኖች መሪ በመሆን ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅምና ሰላም መቆሞትን ማሳየትና ማረጋገጥ ይገባዎታል::

ይህንን የምልበት ምክንያት ከላይ እንደጦቀምኩት አብዛኛው የኦሮሞ ጎሳ አካል ያልሆነው ክፍል የሚያሰማውን ቅሬታ በማንበብና በመስማት ነው::
አንዳንድ ቅሬታዎችን ጥቀሺ ቢሉኝ:-

1. የዛሬ አራት አመት ከሁለት ወር ወይም አራት አመት በፊት ኦኔግን ሲያስገቡ ያለአንዳች ገደብ ይህ የወንበዴ ቡድን መሣሪያውን ይዞ እንዲገባ ሲያደርጉ የተቃወሙ ወገኖች የጠረጠሩትን የኦሮሞን ጎሰኞችና ፅንፈኞች ኃይል እንዲጠናከርና ባለተረኝነት ተሰምቶት ኦዴድ ስልጣን እንዲቆራመት የተደረገ ስታራቴጅካል አካሄድ ነው የሚለውን ዛሬ ጎልቶ እንዲታይ አድርጎታል::


2. እርሶ ስልጣን ላይ ከመጡ በሗላ የፈለጉትን ስታቲስቲክስ ቢያቀርቡና የኦሮሞ በላይነት በአስተዳደሮ ውስጥ ጎልቶ አልታየም ብለው ለማስተባበል ቢሞክሩ : የሕዝብ አስተያየት PUBLIC OPINION ይከራከሮታል:: በአገር ቤት ውስጥ የሚኖረው ሕዝብና ከዲይስፖራ የሚሄደው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይህ የኦሮሞ ተርኝነት ስሜት እንዴት ጉዳይ ለማስፈፀም እስቸጋሪና አንገላች እንደሆነ እየተማረሩ የሚናገሩትን በሹክሽክታም ጆሮዎ ውስጥ እንደሚገባ አልጠራጠርም:: ይህንን የሕዝብ ቅሬታ መናቅና ችላ ማለት አዋጪ አይደለም:: የሕዝብን ቅሬታ የሚንቅ መሪ ምን ያህል ግብዝ እንደሆነ ስለሚያሳይ የግብዝ እጣ ፋንታ አስቀያሚ በመሆኑ እርሶ ላይ እንዲደርስ ስለማልፈልግ የሕዝብን እሮርታ ማዳመጥና ማስተካከል ይገባዎታል::


3. ልማት እጅግ ጥሩ ነው:: ክቡርነትዎ:- ልማት ለሰው ልጅ መጠቀሚያ እንጂ የሰው ልጆች ባላጠፉት ጥፋት : መርጠው ባልተቀበሉት ጎሳ ስም እንደከብት አየታረዱ ባሉበት ሰዓት ሕዝብን ከማፅናናት ይልቅ ችግኝ ሲተክሉ በሕዝብ ቴሌቭዥን መታየት ለእርሶስ እንደ መሪ መታወቂያ መልካም ምስል ትክክልኛ አቀራረብ ይመስሎታል? ይህ የሚያሳየው ለስው ልጆች ሕይወት ደንታእንደማይሰጡ ነው::


4. የእርሶ ፖለቲካዊ ፓርቲ ስልጣን ከተጎናፀፈ ጊዜ ጀምሮ የኦሮምያን ክልል ወታደራዊ ኃይሉን በሰፊው እያቀናጀ መሆኑ በሰፊው ይወራል:: ይህንን ሃሜት ሰምተው የወሰዱት እርምጃ ምንድነው? ለምን የኦሮሞ ሆነ የክልል አስተዳደሮች ከፌድራል መከላከያ ውጭ የእራሳቸውን ወታደራዊ ክምችት አስፈለጋቸው? ከወያኔ ድርጊት መማር አቅቶት ነው? የወያኔ ሚሊሽያ ገንቢዎች የደረሰባቸውን ውደመት ማስታወስ እንዴት ያቅታል?


5. በየባንኩ በተለይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደአያይዙ የኦሮሞ ባንክ ሆኖ የአንድ ቡድን መጠቀሚያ እየህነ እንዳለ ሃሜታው እየበዛ ነው:: በየመስሪያ ቤቱ ያለው የኦሮሞ ተረኝነት አይን ያወጣ እንደሆነ የምሰማቸው ወሬዎች እይበዙ ናቸው:: ይህንን ኢፍታዊ የአገር አስተዳደር ነው እርሶ የሚፈልጉት ወይስ ከአቅሞ በላይ ሆኖ ነው?


6. ያስታውሱ እንደሆን ዲያስፖራው በ2022 መግብያ ወደ እገሩ ገብቶ አሻራውን እንዲይስቀምጥ ለወራታት ሲማፀኑና ሲልምኑ ነበር:: ዲያስፖራውም የእርሶን ጥሪ በአክብሮት ተቀብሎ ሚሊዮን ባይሆንም ከማንኛው ጊዜ በበለጠ በብዛት ገባ:: የገባውም እያንዳንዱ በተቻለ አቅሙ ክጎኖ ሆኖ በመዋዕለ ንዋይ ፍሰት INVESTMENT ሆነ ለቤተሰቦቹ ሱቅም ከፍቶ አገሩን ለመርዳት አስቦ ሲገባ እርሶ ቅስሙን ሰበሩት:: ይህም አብዛኛው ዲያስፖራ የሆነው በስደት አእምሮት ሳይሆን በወደቀው የወያኔ አስተዳደር ሞት ወይስ መኖር የሚለው ምርጫ ውስጥ ገብተው ከአገራቸውና ከቤተስቦቻቸው ተለይተውበባእድ አገር የተሰደዱት:: ሆኖም ለአገራቸውና ለሕዝባቸው የተቻላቸውን መልካም አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ እርሶ ባቀረቡት ጥሪ አክብሮዎት ሲመጡ : ገና እግራቸው ከአውሮፕላን ማረፊያ ሳይወጣ : በፍርድ መቀጣት የሚገባቸውን በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ሰቆቃ የፈጠሩትን : ዛሬ ኦሮሞና አማራ መሃል የተከሰተውን የእርስ በርስ ጥላቻ ያስጀመሩትን : ዛሬ በወለጋ ውስጥ 1000 በላይ ኢትዮጵያውያን በአማራነታቸው እንዲጨፈጭፉ ያበቁትን : አረመኔ የወያኔ መሪዎችን ምህረት በማድረግ ምን ያህል ዲያስፖራውን በማስቀየምና በማሳዘን ቅስሙን እንደሰበሩት ይረዱታል? በእድሜያቸው ምክንያት ፍርድ ሳይሰጣቸው በምህረት የተለቀቁት የወያኔ መሪዎችና ሹማምንት ሕይወት እነሱ ከጨፈጨፉትና ካስጨፈጨፉት በሚሊዮን ከሚቆጠረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕይወት በልጦ ነው? የእነዚህ አረመኔዎች ሕይወት ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በአማራ ስም ከተጨፈጨፉት ኢትዮጵያውያን ይበልጣል? እርሶ ማን ሆንው ነው ፍርድ ዩሚገባቸውን አረመኔ ወንጀለኞች ያለፍርድ ቤት ውሳኔ ምህረት የሚያደርጉላቸው? ወይስ የኦሮሞ ጎሰኞችና ፅንፈኞች የሆኑትን ጀዋር “ከበቡኝ” መሐመድን በቀለ “ገለባ” ገርባን ለመፍታት ቅድመ ዝግጅት ነበር? ጀዋር “ከበቡኝ” መሐመድ አልነበር በጥጋቡ በአልበገርም ስሜቱ ሰዓት ኢትዮጵያ ሁለት መንግስታት አሏት:: አንዱ የአቢይ ሌላው የእኔየቄሮ መንግስታት ናቸው ያለው:: ይህንን ዘረኛና ግብረአበሮቹን ለመፍታት ሲባል የወያኔን ወንጀለኞች በመፍታት ኢትዮጵያ እርሶ ጋብዘውት የገባውን ዲያስፖራ ቅስሙን የሰበሩት?


በኦሮሞ ቁንጮ ELITE ዘረኝነትና ፅንፈኝነት ብዙ የሚወሩና የሚያጠራጥሩ ነገሮች አሉ:: ያም ሆኖ እርሶ ቀና ሰው : ለኢትዮጵያ እንጅ ለጎሳ ፅንፈኝነት የቆሙ እንዳልሆኑ ብዬ እከራከርሎታለሁ::

አንድ መሪ ​​ሊኖረው ከሚችላቸው በጣም አስፈላጊ ባህሪያት አንዱ የኃላፊነት ስሜትና አስተማማኝነት ነው:: ይህ ማለት እነዚህን ባህሪያት ኃላፊነትን በግዴታም ሆነ በውዴታ ለተወሰደው እስተዳደራዊ ስራ ውስጥ ማሳየት ዋነኛ ነው:: በተጨማሪም ከሌሎች ጋር መሪው ወይም አስተዳዳሪው ከሌሎች ጋር በሚያደርገው ግንኙነትም ይህንን የኃላፊነትን ስሜትና አስተማማኝነትን ማሳየት ተገቢ ነው::


እርሶ ግን እንጋበዝ ሳይል እርሶ የጋበዙት ዲያስፖራ በኃላፊነት ስሜቶና በእስተማምኝነቶ ላይ ጥርጣሬ በማሳዱር አዝኖ ወደሸለቆው እንዲመለስና ወደፊት በእርሶ ጥሪና አመራር ከፍተኛ እምነት እንዳያድርበት ሆኗል:: ዲያስፖራው ብቻ ሳይሆን አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብና ከኦሮሞ ዘረኞችና ፅንፈኞችና ደጋፊዎቻቸው በስተቀር የኦሮሞ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለእርሶ ያለው ድጋፍ በየእለቱ መቀነሱን መታዘብ የተሳኖት አይመስለኝም:: ምክንያቱም ፈረንጆች እንደሚሉት THE BUCK STOPS WITH ME የሚለውን አነጋገር ተረድተው በአስተዳደሮ ዘመን ለሚካሄደው የሰውሕይወት ጥፋት ኃላፊነት ተሰምቶት የሃዘን መግለጫ አለመስጠትና ለሰው ልጆች ዋጋ እንደማይሰጡት ታዛቢዎቾና ተቃዋሚዎቾ እንዲያስቡ ማድረጎ ነው:: ፈረንጆች ሲተርቱ YOU MAKE YOUR HEAVEN OR YOUR HELL ይላሉ:: ይህንን ለእርሶ መተርጎምም አልቃጣም:: ምክንያቱም የመረዳት ችሎታው የላቀ ስለሆነ ነው:: ግን ጥያቄዬ አመራሮን የመልካምነት ምሳሌ ለማድረግ ምን ያህል ይፈልጋሉ ነው:: የአመራር ጊዜዎን ገነታዊ ወይስ ሲኦላዊ እንዲሆን ደንታ ስለማይሰጦት ነው? ወይስ እንዳሉፉት መሪዎች በግብዝነትና በአልነኬነት ስሜት ተሞልተው በኦሮሞ ዘረኞችና ፅንፈኞች ተጠልተው በአማራነታቸው በግፍ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያንን ደም ፍትሕ እንዳያገኝ ነው ወይ ጥረቶ? እርሶ ከአማራ ኢትዮጵያዊት ጋር ተጋብተው የአራት ልጆች አባት ሆነው የልጆቾን እናት ቤተሰብ ያስጨፈጭፋሉ ብዬ ልገምትም ላስብም አልችልም:: ግን እንደመሪ በወለጋ ውስጥ ሰሞኑን የተደረገውን ጭፍጨፋ ሰምቶ እንዳልሆነ ችግኝ በመትከል ማሳለፍ አንድ ፈርንጅ ያለውን አስታወሰኝ:: ይህም “በጭካኔ ላይ ዝምታ በዓለም ላይ ትልቁ ወንጀል ነው”:: ከቀና መሪ በጭካኔ ሰዓት ዝምታ አይጠበቅም:: የሞቱትን መርሳትና መናቅ ነው:: እነዚህ ሙታን የእርሶና የእኔ ቤተሰቦች ቢሆኑስ? ምንድን ነበር የሚሰማን? በኢትዮጵያ ሆነ በመላው ዓለም በጭፍጨፋ ለሚያልቁት የሰው ልጆች የእራሳችን ወገን እስካልሆነ ዝምታን እንመርጣለን:: የእስልምና ወይም የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ብንሆንም ፈጣሪ ወይም እግዚአብሄር አንድ እንጅ የተለያየ አይደለም:: ሁላችንንም የፈጠረ እግዚአብሔር ነው ብለን ካመንን ለምን የእግዚአብሔር ፍጡር በሰውእጅ ሲጠፋ በጋራ አንጮህም? ወይስ ሃይማኖት የሰዎች መጠቀሚያና ማጭበርበሪያ መሣሪያ ነው?

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ በግሌ እስከዛሬ ድረስ ባደረጉት ሥራ ከሚያጠፉት የሚያለሙት መልካም ድርጊቶች ስለሚበዙ በአንድ አርእስትና አመለካከት ላይ ሳልወሰን ባለሁበት ዋዮሚንግ ስቴት ኦፍ አሜሪካ ጡረታዬን እያስጠበኩ የልጅ ልጆቼን በምፈልገው ሰዓት እየጎበኘሁ እደግፎታለሁ:: ግን ምንም ሳያደርጉ ቤተሰቦቻቸውና ቅድመቤተሰቦቻቸው ኖረው በተወለዱበት መሬት እንደውጭ ጠላት በአማራ ስም የተገደሉት ኢትዮጵያውያን ወገኖቼን ደም ያፈሰሱት ኦሮሞን አሰዳቢ አረመኔዎችን ካላጠፉና ለፍርድ ካላቀረቡ በእውነትም ስብእና የተሳኖት የስልጣን ጥቅመኛና ሱሰኛ መሆኖትን ለማሳየት በምንም ወደሗላ አልልም:: ይህች አዛውንት ሴት ምንም አይነት ለውጥ ልታመጣ አትችልም ብለው ሊመፃደቁ ይችላሉ:: ሆኖም መረሳት የሌለበት በማህበረሰብ ሆነ በድርጅት ውስጥ የሚመጡት ለውጦች የሚጀመሩት በብዙሃን ሳይሆን በነቁና መልካም አስተሳሰብና አመለካከት ባላቸው ነጠላ ግለስቦች መሆኑን ነው:: አንዳንዱ ለግል ጥቅሙ ሰፊውን ሕዝብ መሳሪያ አድርጎ የሚፈልገውን ሲያገኝ ያ ሕዝብ ላይ ሸፍጥ ይሰራል:: እርሶ ይህ እይነት ግብዝነትን ያሳያሉ ብዬ እንዳስብ አልፈልግም:: ማንም ሰው ፍጹም አይደለም:: ሁላችንም ስውር ኃጢአቶቻችን አሉን። ግብዝነት የእለት እለት መመሪያችን ስናደርግና አልበገሬነት ሲወጥረን: የግብዝነት ትርጉም : የራስን ኃጢአት በመካድ ራስን በማታለልና ትዕቢት በውስጣችን እንዲያድግ መፍቀድ ይሆናል። ሆሎኮስትን እምልጦ የወጣው ኤልዬ ዊይዝል የተናገረውን ብናስታውስ “ሰብእዊነት መቋቋም የማይችለውን በእድሜያችን ወይም በሕይወታችን ሰዎችን በሕይወት ያቃጥላሉ ብዬ አላመንኩም ነበር:: ግን ሆነ::” ዛሬ የኦሮሞ ዘረኞችና ፅንፈኞች አማራ ኢትዮጵያውያን ወገናችንን ሲገድሉና ለመውለድ የቀረበችውን እህታችንን ሆድ ወግተው ፅንሱን ሲቀጩ እርሶ ሲሰሙ ምን ተሰማዎት? እንዲህ ዓይነት ጭካኔን በሕይወቴ አያለሁ ብለው አስበው ነበር? ይህንን ነው ኤልዬ ዊይዝል ያስታወሰን::

ክቡርነትዎ ምንም እንኳ በልጄ እድሜ የሚገኙ ቢሆኑም ለያዙት አመራር ለተውለድኩባት አገሬ ኢትዮጵያ ታላክ ክብር ስላለኝ አንቱ በማለት አከብሮታለሁ:: በየድረገፁ እርሶን እያንቋሸሹ ለሚናገሮት የሚሰሳድቡና የሚያዋርዱ እርሶን ሳይሆን አገራቸውንና በአስተዳደሮ ስር ያለውን ሕዝብ መስሎ ስለሚታየኝ እነዚህን በሃሳብ መከራከር ትተው ግለሰብን በመዘርጠጥ ነጥብ ያስያዙ የመሰሉትን በተደጋጋሚ አወግዛለሁ:: የእኔን ግልፅ ደብዳቤ እርሶ ያነባሉ የሚል ቅዠትም የለኝም:: ግን እንብቦ ለእርሶ ቱስ የሚል አይጠፋም በማለት የቦርከና ድረገፅ ባለቤቶቹ ካወጡት ብዬ አቅርቢያለሁ::

ለእርሶ ያለኝ የመጨረሻ መልእክቴ የማንኛውም ኢትዮጵያውያን ደም በከንቱ መፍሰስ የራሶ ስጋ ዘመዶች ደም መፍሰስ መሆኑን ተገንዝበው የፖለቲካ ሂሳብ ማጣጫ የሚደረገውን ግድያና ጭፍጭፋ እንደማይቀበሉና እንደማይደግፉ ለአገሪቱ ሕዝብ በጊዜ ማስታወቅና ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ ግዴታዎ መሆኑን መገንዘብ ይኖርቦታል:: ሕዝብ እየተላለቀና እያለቀ አልሰምሁም የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ማለት ግድያውን እንደመደገፍ ይቆጠራል::

በአማራነት ስም በአረመኔው ኦነግ ሸኔና በኦሮሞ ዘረኝችና ፅንፈኞች የተገደሉትን ኢትዮጵያውያንን ነፍሳቸውን ከመላክቶች ጎን ያስቀምጥልን:: አረመኔ ገዳዮችን ለፍርድ ለማቅረብ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድንና ስልጣንን የተረኝነት ስሜት ያሳደረባቸውን ግብዞችን እግዚአብሔር እንደሰው እንዲያስቡ ልባቸውን ይክፈትላቸው::

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ይበልፅጋሉና ያብባሉ!!

_

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com 


የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena 

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

1 COMMENT

  1. Again, I like the positive attitude of the writer. I too had the same feeling (sometimes doubting) as the writer until the PM last Parliament appearance. The point he tried to make regarding the raising of Oromia flag in Public Schools of Addis Aababa, a Federal City, and sanctioning of students to participate in a divisive regional anthem in addition to blaming some city residents hating Oromos was a last straw. This must have been done purposely to divide and concur. I can’t support such a leader. I wanted to be clear that I was one of the early supporters of the PM. Accidentally, I was in Addis when there was a big rally to support him in Meskel Square. I was present in that rally and saw the happiness of Addis residents. I wonder how most feel at this time.

    I wish people of good continence like the writer of this article keep participating in the affairs of beloved Ethiopia as the writer already promised in the article.

    Most of all I wish the Almighty in His mysterious ways deliver Ethiopia from this Tribalism that is going on for too long now.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here