spot_img
Wednesday, June 7, 2023
Homeአበይት ዜናአክራሪ የኦሮሞ ሓይሎች ዛሬ በወለጋ አድርሰውታል በተባለ አዲስ ፍጂት ከሁለት መቶ በላይ ንጹሃን...

አክራሪ የኦሮሞ ሓይሎች ዛሬ በወለጋ አድርሰውታል በተባለ አዲስ ፍጂት ከሁለት መቶ በላይ ንጹሃን አልቀዋል

- Advertisement -

 

ቦርከና 

መንግስት ሸኔ በማለት የሚጠራው አክራሪ የኦሮሞ ብሄርተኛ ታጣቂ ዛሬ በቄለም ወለጋ አድርሶታል በተባለ እልቂት ከሁለት መቶ በላይ የአማራ ተወላጆች አልቀዋል::

የዛሬ አስራ አምስት ቀን ይሄው ቡድን ባደረሰው ጎሳ ተኮፍ ፍጂት ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ የአማራ ተወላጆች ማለቃቸውን የአይን እማኞችን የጠቀሱ የሃገር ውስጥ ዜና አውታሮች እንደዘገቡት ይታወሳል::

ዛሬ የደረሰውን ሌላ ዙር እልቂት ቀድመው በማህበራዊ ሚዲያ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው ናቸው::  

“የጸጥታ አካላት ከሚያደርሱበት ዱላ የፈረጠጠው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ ነው። በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸዋል።በዜጎቻችን ላይ በደረሰው መከራ እያዘንን ይሄንን አሸባሪ ቡድን እስከመጨረሻው ተከታትለን ከህዝባችን ጋር እናስወግደዋለን”  ሲሉ ጽፈዋል::  

ስለ ሟቾች አሃዝ የሰጡት ፍንጭ የለም::  

ከዚህ ቀደም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወታደራዊ ክንፍ ነው የሚባልልነት እና መንግስት ሸኔ እያለ የሚጠራው ቡድን በዚያው በቀለም ወለጋ አካባቢ ተመሳሳይ ጭፍጨፋ አንዳደረሰ የሚታወስ ነው:: 

የዛሬ አስራ አምስት ቀን ደርሶ በነበረው አማራ ተኮር ጭፍጨፋ ከቀናት በኋላ በመንግስት ግንኙነት የሚኒስትር መስሪያ ቤት በዶክተር ለገሰ ቱሉ አማካይነት መንግስት በሰጠው መግለጫ ከግድቡ ሙሊት ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ ክስተት አንደሚጠብቅ መናገሩ ይታወሳል::  

የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በቶሌ ጊምቢ ከደረሰው እልቂት በኋላ ተመሳሳይ እልቂት እንዳይደርስ መንግስት በቂ የጸጥታ ኃይሎችን በአካባቢው እንዲያሰማራ መወትወታቸው ይታወቃል::

__
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena 

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,879FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here