spot_img
Wednesday, March 22, 2023
Homeነፃ አስተያየትከኢትዮጲያዊያን ማሕበር በአውሮፓ የተሰጠ መግለጫ! 

ከኢትዮጲያዊያን ማሕበር በአውሮፓ የተሰጠ መግለጫ! 

- Advertisement -

ሰኔ 28 , 2014 ዓ. ም.

በንጹሃን ደም እጁን ያጨማለቀው አቢይ መራሹ የብልጽግና መንግስት ሀገር ለመምራት የሚያስችለውን ሞራል ሙሉ በሙሉ ተነጥቌል ! 

ስለዚህም በትረ ስልጣኑን በአስቸኴይ ለሽግግር መንግስት እንዲያስረክብ የኢትዮጲያዊያን ማሕበር በአውሮፓ በአጽንኦት ይጠይቃል-!!! 

እኛ በ16 የአውሮፓ ሃገራት ዉስጥ የምንገኝና ከአሜሪካ ለሽግግር መንግስት ከካናዳ ከአፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ አባላት ያሉበት ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያን ከዚህ የሚከተለዉን የአቋም መግለጫ አዉጥተናል :: 

United kIngdom, Ireland, Spain, Netherlands, Germany, Spain, Finland, Norway,  Belgium, Switzerland, Italy, Sweden, Denmark, Luxemburg, France, Austria, USA.  Canada, Bahrain, Saudi Arabia, Quwait, Ethiopia, Kenya. 

፠ መግቢያ፦ 

የኢትዮጲያዊያን ማሕበር በአውሮፓ በኢትዮጲያ ኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞን ግምቢ ቶሌ ቀበሌ በሚኖሩ የነገደ አማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ጭፍጨፋን እጅግ በብርቱ ሀዘን እና ቁጭት ተረድታል። በጭፍጨፋው እስካሁን ባለን መረጃ መሰረት ከ2000ሺህ በላይ አማራዊያን አስከሬን መሰብሰብ የተቻለ መሆኑን እና በአጠቃላይ ከ3000ሺህ በላይ አማራዊያን የጭፍጨፋው ሰለባ መሆናቸውን እጅግ እያመመን ማወቅ የቻልነው ሀቅ ነው። 

የቀበሌዋ አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ ኑዛዜያቸውን ሲናገሩ የጊምቢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባጫ እና የወረዳው ሰላም እና ጸጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ በስልክ ደውለው ከላይ የተላለፈ ትዕዛዝ አለ አስፈጽም ብለው እውነታውን በህዝብ ፊት ተናዘዋል፡፡ ይህ የሚያመለክተው ትዕዛዙ በቀጥታ ከመንግስት አካላት የተላለፈና በተለይ የኦህዴድ ባለስልጣናት የተካፈሉበት መሆኑን ነው:: 

በጭፍጭፋው ምክንያትም ከ40 በላይ ታዳጊ ህጻናት እናትና አባቶቻቸውን ተነጥቀው አሳዳጊ ፍለጋ በሆስፒታል ተጠልለው እንዳሉ ውስጣችንን በሚያሳምም ሁኔታ ለማወቅ ችለናል። የቶሌ ቀበሌ ጭፍጨፋ በአይነቱ የመጀመሪያ እንዳልሆነ ሁሉ የመጨረሻውም ይሆናል ብለን አናምንም። 

ከዚያው ከወለጋ ሳንወጣ በምስራቅ ወለጋ ዞን በሆሮ ጉድሩ ፣በጉሊስና በኪረሙ ቀበሌዎችና ወረዳዎች በተፈጸሙ  ተከታታይ ጭፍጨፋዎች በሺህ የሚቆጠሩ የነገደ አማራ ተወላጆች መጨፍጨፋቸውን እና ይህንንም ጭፍጨፋን ተከትሎ በስልጣን ላይ ያለው አቢይ አህመድ መራሹ የብልጽግና መንግስት አንዳችም እርምጃ ያልወሰደ የ ሃዘን ቀን ያላወጀና እስከዛሬዋ እለት ድረስም አንድንም ሰው በተጠያቂነት ይዞ ለፍርድ ሲያቀርብ ያላየንበት የጭፍጨፋ ዘመቻ በመሆኑ መንግስት እንደ መንግስትነቱ ኋላፊነቱን እንዳልተወጣና ይባስም ብሎ ኋላፊነቱን ለመወጣት ፈቃደኝነቱ Political Will እንደሌለው አረጋግጦልናል። መንግስት በነገደ አማራ ተወላጆች ላይ የተከፈተውን የማንነት ተኮር ጭፍጨፋን ለማስቆም ፈቃደኝነት Political Will የሌለው ብቻ ሳይሆን የጭፍጨፋው ዋና ቀያሽ ፈጻሚና አስፈጻሚ

ሆኖ የአማራ ተወላጆችን በመጨፍጨፍና በማስጨፍጭፍ ተግባር ላይ የተሰማራም ኋይል ሆኖ የተገኘ በመሆኑ የመንግስትን ቅቡልነት ብቻ ሳይሆን የመንግስትን አምባገነን ሆኖ እንኴን ሀገር የመምራትን ሞራላዊ ብቃት ሙሉ በሙሉ ያጣ ሆኖ እንድናየው አድርጎናል። 

፠ በአውሮፓ የኢትዮጲያዊያን ማሕበር በወቅታዊው የሀገራችን ጉዳይ ላይ ያደረጉት ውይይትና ያስተላለፈት ውሳኔ፦ 

በምእራብ ወለጋ በግምቢ ቶሌ ቀበሌ በሺህ የተቆጠሩ የአማራ ተወላጆች መጨፍጨፍ በኋላ ማሕበራችን ባለፈው ቅዳሜ ጁን 25ቀን 2022 አምስት ሰዓት በላይ የፈጀ ውይይት አድርጔል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በሙሉ ማለት በሚያስችል መልኩ በወለጋ የተፈጸመውን አማራ ተኮር ጭፍጨፋን በጽኑ አውግዘው መንግስት እንደመንግስትነቱ የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ያልቻለ – ከፍም ሲል በንጹሃን ዜጎች ላይ በነገዳቸው የአማራ ብሔር ተወላጅ በሆኑት ላይ ሆን ብሎ የጭፍጨፋ ዘመቻ ከፍታል ብሎ ከመግባባት ላይ ደርሷል። 

ተወያዮቹ በጭፍጨፋው ላይ ይህንን አቌም ከመያዛቸውም በላይ በአጠቃላይ በሀገራችን ጉዳይ ላይ የሚከተለውን አቌም በመያዝ ለመላው የኢትዮጲያ ሕዝብና ብሎም ለተቀረው ዓለም አቌማቸውን ለማሳወቅ ወስነዋል። 

በዚህም መሰረት፦ 

��1ኛ – በነገደ አማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለውን መንግስታዊ ጭፍጨፋን በተመለከተ፦ 

በአውሮፓ የኢትዮጲያዊያን ማሕበር በወለጋ ግምቢ ቶሌ ቀበሌ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ በጽኑ ያወግዛል- የጭፍጨፋው ተጠያቂም ቁጥር አንድ መንግስታዊ መዋቅሩን የተቆጣጠረውና የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለበት የብልጽግና መንግስት ኋላፊነቱን ባለመወጣትና ኋላፊነቱን ለመወጣትም ፈቃደኛ ባለመሆን ሀገር የመምራቱን ሞራል የተገፈፈ ስለሆነ በአስቸኴይ ስልጣኑን ለሕዝብ እንዲያስረክብ በአውሮፓ የኢትዮጲያዊያን ማሕበር በጽኑ ይጠይቃል!!! 

��2ኛ- ሀገራችንን ከጨፍጫፊ ኋይሎች እጅ ለማላቀቅ የኢትዮጲያዊያን ማሕበር በአውሮፓ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል፦ 

��2-1 መላው በዲያስፖራ የሚኖረው ኢትዮጲያዊ የስርዓቱ የውጭ ምንዛሬ የጀርባ አጥንት የሆነውን ለወገኖቻችን ማስጨፍጨ ፊያ መሳርያ መግዣ ገንዘብ ወደ መንግስት ከመላክ እንዲታቀብ ጥሪ እናስተላልፋለን:: 

��2-2 መላው በዳያስፖራ የሚኖር ኢትዮጲያዊ አማራ ሆነ አልሆነ -ኢትዮጲያዊ እስከሆነ ድረስ የአማራዊያኑን የህልውና ትግል ሙሉ በሙሉ በመደገፍ የፋኖን አደረጃጀት በገንዘብ፣ በሀሳብ፣ በሎጀስቲክስ፣ በመረጃና በዲፕሎማሲ እንዲደግፍ ጥሪ እናቀርባለን:: 

��2-3 በዳያስፖራ የሚኖረው መላው ኢትዮጲያዊ በሙሉ እጃቸውን በንፁሀን ደም ያጨማለቁትን የዚህን ስርዓት ቁንጮዎችን በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ክስ በመክፈት ለፍርድ እንዲያቀርብ ጥሪ እያቀረብን በእኛ በኩል ሙሉ በሙሉ ለመተባበር ቃል የገባን መሆናችንን በይፋ ለማሳወቅ እንወዳለን!! 

��3ኛ- በሀገር ውስጥ ላለው ሰፊው የኢትዮጲያ ሕዝብና በተለይም የጭፍጨፋው ኢላማ በሆንከው የአማራ ሕዝብ የተላለፈ መልእክት፦ 

��3-1 በሀገር ውስጥ ያለህው መላው የኢትዮጲያ ሕዝብ ከወገንህ የአማራ ሕዝብ ጎን ተሰልፈህ ይህንን ዘረኛ ተረኛና ደም አፍሳሽ የሆነውን የብልጽግናን ስርዓት እንድትታገል ጥሪያችንን እናቀርባለን:: 

��3-2 በሀገር ውስጥ ያለህው መላው የነገደ አማራ ተወላጆች በሙሉ ከልጆችህ ከፋኖዎች ጋር ሆነህ ይህንን ሰው በላ ስርዓትን እንድትታገል ጥሪያችንን እናቀርባለን!!! 

��3-3 ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የምናስተላለፈው መልእክት አንተ የሀገራችንን ዳር ድንበር የምትጠብቅ የሕዝብ ሰራዊት ነህ እንጂ የዘመን አመጣሹ ገዢው ስርዓት አገልጋይና ጠባቂ አለመሆንህን አውቀህ- የመንግስት መምጣትና የመሄድን ለውጥ ስናይ የሀገር እና የሕዝብ አይቀየሬነትን ተረድተህ እራስህን የስርዓቱ አገልጋይ ባሪያ ሳይሆን የሕዝብና የሀገር አገልጋይ ኋይል በማድረግ ከሕዝብ ጋር እንድትወግንና ከታሪክ ተጠያቂነት እራስህን እንድታድን አጥብቀን እንጠይቃለን።

��3-4  

ለኢትዮጲያዊያን ምሁራን ክፍል፣ የሃይማኖት መሪዎችና በህብረተሰባችን ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ለሆናችሁ በሙሉ  በአውሮፓ የኢትዮጲያዊያን ማሕበር ሚናችሁን ከጨፍጫፊውና አስጨፍጫፊው ገዢው የብልጽግና ፓርቲ ጋር ሳይሆን ከሰፊው ሕዝብ ጋር በማድረግ ይህንን ሰው በላ ስርዓት አምርራችሁ እንድትታገሉ አበክረን እንጠይቃለን። 

፠ ለአቢይ መራሹ የብልጽግና መንግስት የተላለፈ መልእክት፦ 

��1ኛ – የብልጽግና መንግስት በአማራ ክልል የከፈተውን ዘመቻ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ በአስቸኴይ እንዲያቆም:: 

��2ኛ – አቢይ መራሹ የብልጽግና መንግስት በግፍ ያሰራቸውን እና ያፈናቸውን ፖለቲከኞች፣ጋዜጠኞች፣የማህበረሰብ አንቂዎችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ በአስቸኴይ እንዲፈታ 

��3ኛ – አቢይ መራሹ የብልጽግና መንግስት ከአሸባሪው ትህነግ ጋር እያደረገ ላለው ድርድር አማራን የሚወክሉ በራሱ በአማራው የተመረጡ ተወካዮች እስካልተሳተፉና ዛሬ በእነ ደመቀ ሞክንን ተመስገን ጥሩነህ ተወካይነት የሚደረገውን ድርድር የአማራን ሕዝብ ፍላጎት የማይወክል ስለሆነ በድርድሩ ለሚተላለፍ ማንኛውም አይነት ስምምነትም ይሁን አለመስማማት የአማራን ሕዝብ የማይወክል በመሆኑ የማንቀበለው መሆኑን ለመንግስት ለማሳወቅ እንወዳለን። 

፠ መደምደሚያ 

በኢትዮጲያ ውስጥ ለሚፈጸም የአንድ ሰው በግፍ መገደል ሙሉ በሙሉ ተጠያቂው የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለበት መንግስት ነው። ስለሆነም ይህ አቢይ መራሹ የኦህዴድ ብልጽግና ወደ ስልጣን ከመጣበት ሚያዚያ 24 ቀን 2018  ጀምሮ በኢትዮጲያ በግፍ ለተጨፈጨፉ ንጹሃን ነፍሶች ሙሉ በሙሉ ተጠያቂው የብልጽግና መራሹ መንግስት ነው ብሎ ማሕበራችን ያምናል። 

እንደ መንግስት ኋላፊነቱን እና ግዴታውን መወጣት ያለመፈለግና ያለመቻልም አልፎ መንግስት ባዘጋጃቸው ዘርፈ ብዙ ኢ መደበኛ ታጣቂ ሰራዊት መጠነ ሰፊ የጭፍጨፋ ዘመቻን እያጧጧፈ ያለ ኋይል ሆኖ በመገኘቱ በአስቸኴይ ከስልጣን ይውረድ ብለን ስንጠይቅ ይህንን ጥያቄያችንንም እውን በማድረግ አንጻር ከማንኛውም ኢትዮጲያዊ ኋይል ጋር በጋራ ሆነን ለመታገል ጽኑ አቌም በመያዝ ነው። 

የንጹሃንን ጭፍጨፋ ማስቆም የሚቻለው ጨፍጫፊውን ኋይል ለፍርድ በማቅረብ ብቻ ነው-!!!! 

ከአቢይ መራሹ የብልጽግና መንግስት የሕዝባችን መጨፍጨፍን እንጂ የሕዝባችን ከጨፍጫፊዎች መጠበቅን ስላላየን መፍትሔ ስጠን ብለን የምንጠይቀው አንዳችም ነገር የለም። 

እኛ ከተባበርን ግፈኞችን ጨፍጫፊዎችን እና አስጨፍጫፊዎችን ማንበርከክ ይቻለናል- ለዚህ ደግሞ ሁላችንም በያለንበት ለፍትህ ለእኩልነት ለሰላምና ለአንድነት በጽናት እንታገል-!!! ኢትዮጵያ ከልጆቿ ጋር በሰላም፣ በአንድነት፣ በፍቅር ለዘላለም ትኑር ! የኢትዮጲያዊያን ማሕበር በአውሮፓ – ዋና መስርያ ቤት: ፍራንክፈርት ጀርመን!!
__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena 

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,440FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here