spot_img
Tuesday, October 3, 2023
Homeዜናኢትዮጵያ የአልሸባብ ጥቃት ያሰጋታል ተባለ

ኢትዮጵያ የአልሸባብ ጥቃት ያሰጋታል ተባለ

advertisement
(ፎቶ ከአዲስ አድማስ የተገኘ)

አዲስ አድማስ

• አገሪቱ ከአሸባሪው ቡድን ሊሰነዘርባት የነበረ ከፍተኛ ጥቃት መክታለች
• ድንበር አቋርጠው ኢትዮጵያ የገቡት የአልሸባብ ታጣቂዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው
• አልሸባብ ወደ ኦሮሚያ ክልል በመግባት ከሸኔ ቡድን ጋር ለመገናኘት አቅዶ ነበር

ኢትዮጵያ ወደ ግዛቷ ዘልቆ የገባው የአልሸባብ አሸባሪ ኃይል የከፈተውን ጥቃት መመከቷንና በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ግን ቡድኑ ተመሳሳይ ጥቃቶችን ሊፈፅም እንደሚችል የአሜሪካው የአፍሪካ ወታደራዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ጀነራል ስቲፈን ታውንሰንስድ ተናገሩ፡፡ በአሜሪካ ወታደራዊ ባለሙያዎች ግምት በትንሹ 500 የአልሸባብ ታጣቂዎች ከኢትዮጵያ ድንበር 150 ኪሎ ሜትር ዘልቀው ገብተው እንደነበርም ዋና አዛዡ ለቪኦኤ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል  ሐምሌ 13 ቀን በ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው በመግባት ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የአሸባሪው አልሸባብ ሃይሎች ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸውንና 13 መኪናዎችም መውደማቸውን የገለፁት የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ፤ ሁሉም የአሸባሪው ቡድን ታጣቂዎች ኢትዮጵያውያን መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡ አገሪቱ ከአልሸባብ የሚሰነዘርባትን ጥቃት ለመመከት ከሱማሊያ ጋራ በሚያዋስናት ድንበር ላይ የፀጥታ ቀጠና እንደምታቋቁም ተናግረዋል፡፡
ከቀናት  በፊት “አቶ” በሚባለው ቦታ ወደ ሱማሊያ ክልል አፍዴር ዞን ገብቶ በነበረው የአሸባሪው አልሸባብ ታጣቂ ቡደን ላይ በተወሰደው እርምጃ የተደመሰሰ ሲሆን ቡድኑ ወደ ኦሮሚያ ክልል በመግባት ሸኔ እየተባለ ከሚጠራው የሽብር ቡድን ጋር ለመገናኘት የነበረው ዕቀድ መክሸፉን መንግስት አስታውቋል፡፡

ቡድኑ በሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል የደረሰበትን ጥቃት ለመቋቋም ባለመቻሉ መደምሰሱንና የተበተነው ጥቂት ሃይልም የያዘውን ከባድ መሳሪያ ጨርሶ ለመደበቅ እየሞከረ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

እነዚህን የተደበቁትን የአሸባሪ ቡድን አባላት ለቅሞ በማውጣት አካባቢውን ለማጽዳት ከፍተኛ ትግል እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል። አሸባሪው ቡድን ይዞት ከገባው አራት የረጅም ርቀት መገናኛ ሬዲዮ መካከል ሶስቱ መማረካቸውም ታውቋል፡፡

ይህንኑ በአሸባሪው የአልሸባብ ቡድን ላይ ሁልሁል የተባለው ስፋራ በመደምሰስ አካባቢውን ከሽብር ጥቃት ያዳነውን የሱማሌ ክልል ልዩ ሃይል  የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ለሌላ አዲስ ተልዕኮ ወደ ድንብር ሸኝተውታል፡፡

አሸባሪው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን በኤልከሬ ወረዳ አልፎ ወደ ኦሮሚያ ክልል  በመግባት ከአሸባሪው የሸኔ ቡድን ጋር ለመገናኘት ዕቅድ ነበረው ተብሏል፡፡

__
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena 

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,723FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here