
የዜና መዋእል
ዲ ኤች ኤል
ሐምሌ 29, 2014 ዓ.ም.
ኢትዮየጵያ ውስጥ የሚገኘው አዲሱ DHL Global Forwarding ተቋም ወጪ ቆጣቢ በሆኑ፣ ከጫፍ እስከ ጫፍ የአቅርቦት ሰንሰለት መፍትሄዎች ክልላዊ ንግዱን ሊያሳድግ ነው
- አዲሱ የጭነት ጣቢያ የሀገር ውስጥ ደንበኞችን ጊዜ እና ገንዘብ በመቆጠብ, በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የአቅርቦት ሰንሰለት ሎጂስቲክስ ያሳድገዋል።
- የኢትዮያ መንግስት ይበልጥ ውጤታማ የሆነ ከኮንቴይነር ያነሰ ክብደት ያለውን የባህር/ውቅያኖስ ጭነት ለመጫን የሚያስችል የተቀናጀ ፈቃድ ለ DHL Global Forwarding ይሰጣል።
- DHL Global Forwarding ለንግድ ሥራዎች በጥሩ ዋጋ፣ መንገዶች ጭነት እና የትራንዚት/ማስተላለፊያ ጊዜ አገልግሎት ለመስጠት ኢትዮጵያ ውስጥ ዲጂታል የመንገድ ጭነት መደላድል Saloodo! ያስመርቃል።
አዲስ አበባ፣ 04 ሐምሌ 2022: በዓለም አቀፍ የአየር፣ የባህር እና የመንገድ ጭነት አገልግሎቶች መሪ የሆነው DHL Ethiopian Airlines Logistics Services S.C. ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ የኮንቴይነር ጭነት ጣቢያ ከፍቷል። አዲሱ በሞጆ ደረቅ አካባቢ የሚገኘው 800 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ጣቢያ ወጪ ቆጣቢ የሆኑ የተቀናጁ አገልግሎቶችን ይሰጣል።
የዚህ ጣቢያ መመረቅ ለDHL Global Forwarding በክልሉ ውስጥ ከተገኙ ሁለት ልማቶች ጋር ተገጣጥሟል፡ እነዚህም የኮንቴይነር ጭነት ጣቢያ (CFS) የተቀናጀ ፈቃድ ከኢትዮጵያ መንግስት ማግኘቱ እና በሀገሪቱ ውስጥ የራሱን ደጂታል የመንገድ ጭነት መደላድል Saloodo! ማስጀመሩ ናቸው።
የDHL Global Forwarding Sub-Saharan Africa ዋና ሥራ አስፈጻሚ Clement Blanc እንዲህ ብለዋል፡ “የDHL Global Forwarding ክልላዊ ብቃት ወደር የለውም። ሥራዎቻችንን በማስፋት ለኢትዮጵያ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማምጣት አቅደናል። ሞጆ ደረቅ ወደብ ለክልላዊው የንግድ እድገት ድጋፍ ለማድረግ ወጪ ቆጣቢ የሎጂስቲክስ ችሎታዎችን እንደሚያበረክት እንተማመናለን።”
የተቀናጀው ፈቃድ ከኮንቴይነር ያነሰ ክብደት (LCL) ያላቸውን የወጪ ንግዶች በማካተት ለDHL Global Forwarding በሀገሪቱ ውስጥ የሚሰጣቸውን አገለግሎቶች አድማስ ያሰፋል። ይህም ኮንቴይነር ውስጥ ያለውን ቦታ ለተለያዩ በርካታ ጫኞች ማጋራትን፣ ፈጣን የማስተላለፊያ ጊዜዎችን አጠቃቀም ተደራሽ ማድረግን እና አጠቃላይ የጭነት ወጪን መቀነስን ያካትታል። በተሸከርካሪ ሊጫን ከሚችለው ያነሰ (LTL) ክብደት ላላቸው የመንገድ ጭነቶችም ሞጆ ደረቅ ወደብ ባለው ጣቢያ ተመሳሳይ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።
የDHL Global Forwarding Ethiopia ዋና ስራ አስኪያጅ Silvio Weiland እንዲህ ብለዋል፡ “በተጨማሪም ይህ ፈቃድ DHL Global Forwarding’ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን አቅም እና ቦታ የሚያጠናክር ሲሆን ለኩባንያዎች የምንሰጣቸውን ወጪ ቆጣቢ አገልግሎቶች የሚያሰፋ ይሆናል። በዚህ ሰፊ አገልግሎትም ደንበኞች ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ መርዳት እና የዓም አቀፉን ንግድ አስጨናቂነት እና ውስብስብነት ለማስወገድ አቅደናል።”
የDHL Global Forwarding’ ዲጂታል የመንገድ ጭነት መዳላድል Saloodo! ለጫኞች እና አጓጓዦች ወጪዎችን፣ የጉዞ መስመሮችን፣ ጭነትን እና የትራንዚት ጊዜያትን እንዲያሳድጉ በማስቻል አስተማማኝ እና ለአጠቃቀም ቀላል መገናኛ ይሆናቸዋል። Saloodo! በኢትዮጵያ ውስጥ እና ወደ አራቱ ጎረቤት ሀገራት እና ከነዚህ ሐገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የጭነት እንቅስቃሴዎችን ይደግፋል፡ ኬንያ፣ ሰማሊያ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን
የSaloodo! በክልሉ ውስጥ ስራ መጀመር ተገቢውን የጭነት ጊዜ እይታ በማምጣት በክልሉ ውስጥ ከፍተኛ ግልጥነት እና ውጤታማነት እና ትስስር እንዲመጣ ያደርጋል። ይህ የመገናኛ መደላድል ከጥያቄ እስከ ክፍያ ያለውን አጠቃላይ የትራንስፖርት ሂደት ዲጂታል እንዲሆን ያደርገዋል። በአሁኑ ወቅት ባለው ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ አተያይ መሰረት፣ ቀጣይነት ያለውን የንግድ እና የስራ እድገት ለመደገፍ አሰራሮችን ወደዲጂታል የመለወጡን ሂደት ማፋጠን የግድ ነው።
የSalodoo! ዋና ስራ አስፈጻሚ Tobias Maier መካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ፤ እንዲህ ብለዋል፡ “የSaloodo!ን ሀይለኛ፣ ተገቢ የእይታ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ በማምጣታችን በጣም ተደስተናል። አሁን ከትናንሽ ቢዝነሶች ጀምሮ እስከ ትላልቅ ድንበር ተሻጋሪ ኩባንያዎች ድረስ ተደራሽነቱን ለማስፋት እና ዕድገቱን ለማራመድ በኢትዮጵያ አስተማማኝ የመንገድ ጭነት አጓጓዦችን በቀላሉ ማግኘት ይችላል። የደንበኞቻችን እቃዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ለእኛ አስፈላጊ ነው። Saloodo!ን በሚጠቀሙ ጊዜ ማንኛውም ንኡስ ስራ ተቋራጭ ማንኛውም ኮንቴይነር ከወደብ ወጥቶ ከመጫኑ በፊት ኤሌከትሮኒክ ማህተም (e-seal) እንዲመታበት አበክረን አንመክራለን። የሁሉንም እቃዎች እና ኮንቴይነሮች ደህንነት ለማረጋገጥ ይሄ ለሁም የኢትዮጵያ ጫኞቻችን አንዱ ቅድመ ሁኔታ ነው።”
Blanc ይቀጥላሉ፡ “አዲሱ ጣቢያ የተገነባው ከሶስት ዓመታት በፊት በDHL Global Forwarding እና በEthiopian Airlines መካከል በተቋቋመው ስኬታማ እሽሙር ሽርክና መሰረት ነው። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ በየትኛውም ደረጃ ላይ የሚገኙ የንግድ ድርጅቶች ከታንዛንያ፣ ከኬንያ፣ ከኡጋንዳ፣ ከሴኔጋል፣ ከአይቮሪ ኮስት፣ ከጋቦን እና በአህጉሪቱ ውስጥ ካሉ ከሌሎች ሀገራት ጋር በቀላሉ መነገድ ይችላሉ። ይሄ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ መሻሻል ውስጥ አንድ አስፈላጊ ደረጃ ሲሆን በመላው ዓለም በፍጥነት እያደጉ ከሚሄዱ ኢኮኖሚዎች አንዱ ሆኖ እንዲቆይ ያግዘዋል።”
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena