spot_img
Tuesday, October 3, 2023
Homeዜናወንበር ላይ እያሉ ያላስታወሱትን ሕዝብ ከስልጣን ሲነሱ “በእናንተ ምክንያት ነው” ማለት ሕዝብን...

ወንበር ላይ እያሉ ያላስታወሱትን ሕዝብ ከስልጣን ሲነሱ “በእናንተ ምክንያት ነው” ማለት ሕዝብን መናቅ ነው – የሐረሪ ክልል መንግሥት

advertisement
ሐረሪ ክልል መንግሥት

ቦርከና
ጀማል ሰይድ

ወንበር ላይ እያሉ ያላስታወሱትን ሕዝብ ከስልጣን ሲነሱ “በእናንተ ምክንያት ነው” ማለት ሕዝብን መናቅ ነው ሲል የሐረሪ ክልል መንግሥት ገለጸ።

ክልሉ በተለያየ ምክንያት ለሕዝብ የሚጠብቅባቸውን አገልግሎት መስጠት ባልቻሉ አካላት ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡

ክልሉ በመንግሥትና ሕዝብ መካከል ያለው መሰረታዊ ግንኙነት የአገልጋይና የተገልጋይ ግንኙነት መሆኑን ገልጾ በየደረጃው ያለው የመንግሥት መዋቅር ለሕዝቡ ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋና ጥራት ያለው መንግሥታዊ አገልግሎት ለሁሉም ዜጋ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ብሏል።

ዜጎችም ያለምንም አድሎና እንግልት መንግሥታዊ አገልግሎት የማግኘት መብት አለው ያለው የክልሉ መንግሥት በዚህ መነሻነት በየደረጃው ያለው የመንግሥት መዋቅር የሥራ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን በየጊዜው ማረጋገጥና የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል ነው ያለው።

ከሀረሪ ክልላዊ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተሰጠ የአቋም መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

ወንበር ላይ እያሉ ያላስታወሱትን ህዝብ ከስልጣን ሲነሱ “በእናንተ ምክንያት ነው” ማለት ህዝብን መናቅ ነው!

በመንግስትና በህዝብ መካከል ያለው መሰረታዊ ግንኙነት የአገልጋይና የተገልጋይ ግንኙነት ነው። በመሆኑም በየደረጃው ያለው የመንግስት መዋቅር ለህዝቡ ፍትኃዊ ቀልጣፋና ጥራት ያለው መንግስታዊ አገልግሎት ለሁሉም ዜጋ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

ዜጎችም ያለምንም አድሎና እንግልት መንግስታዊ አገልግሎት የማግኘት መብት አላቸው።

በዚህ መነሻነት በየደረጃው ያለው የመንግስት መዋቅር የስራ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን በየጊዜው ማረጋገጥና የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል።

በመሆኑም በሀረሪ ክልል መንግስት በዋናነት የስራ ውጤታማነትን፣ ብቃትና ስነ ምግባር መነሻ ያደረገ የአመራር ምዘና ለማካሄድ በቂ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል።

የምዘናው ሂደቱንም ግልጽ በሆኑ መስፈርቶች እና ፍትኃዊ በሆነ መልኩ ለማካሄድ የሚያስችል የአሰራር ስርአት ተዘርግቶ በጥብቅ ዲሲፒሊን ይመራል።

በመጨረሻም ሁሉም አካላት ለህዝብ ካበረከቱት አስተዋፅኦ እና ካገኙት ተጨባጭ ውጤት አንጻር የማስተካከያ እርምጃዎች ይወሰዳል።

በዚህም በስራ ድክመት፣ በብቃት ማነስ ወይም በስነ ምግባር ብልሽት ህዝብ የሚጠብቅባቸውን አገልግሎት መስጠት ባልቻሉ አካላት ላይ ተገቢው እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል።

ሆኖም ግን አንዳንድ አመራሮች በስልጣን ዘመናቸው ያላስታወሱትን ህዝብ ግምገማና ምዘና ሲጀመር ውጤታማ ስራ ባለመስራታቸው ቁጭት ሊሰማቸው ሲገባ ህዝቡን “በእናንተ ምክንያት ነው ከወንበሬ የተነሳሁት”ይላሉ።

በስርቆትና ምዝበራ የህዝብ ሀብትን ለግል ጥቅማቸው ሲያግበሱ የነበሩትም ድርጊታቸው ወደ ህግ ሲያመራና ተጠያቂ ሲሆኑ “ማንነቴን”፣ “ብሔሬን” ወይም “ሀይማኖቴን” መነሻ ያደረገ ጥቃት ነው የሚሉም አሉ።

ለመደበኛ ስራቸው ምንም ጊዜ ሳይሰጡ ፣ ተቋማቸውን በአግባቡ ሳይመሩ፣ ጊዜው ባመጣው ማህበራዊ ሚዲያ ብቻ ለገጽታ ግንባታ እያዋለሉ የሚገኙ አመራሮችም የስልጣን ጥማታቸውን በፌስቡክ ጋጋታ ለማርካት ይሞክራሉ።

ደግነቱ ህዝብ እና የጥቅም ተጋሪ ይለያያል። ህዝቡ ማን ምን እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል።
በስልጣን ዘመንህ ህዝብ የሚፈልገውን ግልጋሎት ሳትሰጥ ቆይተህ ከስልጣን ስትነሳ አድኑኝ ብትል አይሰማህም።

ከህዝብ ሰርቀህና መዝብረህ ለህግ ስትቀርብ “የእናንተ ተወላጅ ስለሆንኩኝ ነው” ብትልም ጆሮ አይሰጥህም።

ባይሆን የቀድሞ ጥፋትን በተለያዩ ሽፋኖች ከማለባበስ ይልቅ ችግሮችን ወደ ውስጥ በማየት የራስ ስህተትን ማረም ተገቢ ነው፣ ሁለተኛ እድልም ያስገኛል።

ስለዚህ ዛሬ ላይ ሆነህ ነገ የማትቆጭበትን አድርግ። ህዝብን በፍትኃዊነትና በሀቀኝነት አገልግል።

መረጃው –
የሀረሪ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

__

በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,723FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here