spot_img
Wednesday, May 29, 2024
Homeነፃ አስተያየትየሰሜን ኢትዮጰያው ጦርነት ድርድርና የአደራዳሪዎቹ ማንነት ያስከተለው ተስፋና ስጋት (አክሊሉ ወንድአፈረው)

የሰሜን ኢትዮጰያው ጦርነት ድርድርና የአደራዳሪዎቹ ማንነት ያስከተለው ተስፋና ስጋት (አክሊሉ ወንድአፈረው)

Ethiopia _ TPLF _ negotiation

አክሊሉ ወንድአፈረው
ነሀሴ 1, 2014  ዓ.ም.

በብልጽግና የሚመራው በኢትዮጵያ መንግስት እና ሀወሀት መሀል ለሚደረገው ድርድር  እስካሁን ሂደቱን  ሲመራ የቆየው የአፍሪካ ህብረት  ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ሀወሀት ድርድሩን  ይመሩ የነበርቱት ኦባሳንጆን ወደ ኢትዮጸያ መንግስት ያዘነበሉ ወገንተኛ ብቻ ሳይሆኑ ዝገምተኛም ናቸው በማለት እርሳቸው ከአደራዳሪነት እንዲነሱና  በመትካቸውም የኬንያው ፐሪዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ አደራዳሪ እንዲሆኑ  በቃል አቀባያቸው እና በተለይዩ መግለጫዎቻቸው በኩል አሳውቀዋል፡፡፡ 

ይህ የሀወሀት ፐሬዚደንት  ኡሁሩ ያደራድሩን የሚለው አቋም በኢትዮጸያ መንግስት በኩል በቀጥታ አይሆንም  የሚል መልስ ባይሰጥበትም  ደግሞ ደጋግሞ ድርድሩ መካሄድ ያለበት በአፍሪካ አንድነት ሰር ነው የሚለውን  አ ቋሙን  ግን ሲያሰማ ቆይቷል ፡፡

የአውሮፓ ፣ የአሜሪካና  የተባበሩት መንግስታትም ለረዝም ጊዜ ሲነግሩን የነበረው እነርሱ  የሚደግፉት ድርድሩ በአፍሪካ ሀብረት በኩል መሆን እንደሚገባው የሚያመላከት ነበር፡፡ ያም ሆኖ የፐሪዚደንት  ኡሁሩን  ወደ አደራዳሪነት መምጣት ሲቃወሙ አልተሰማም፡

በ ሀምሌ 24፣ 2014 ወደ መቀሌ ተጉዞ የነበረው የአሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት የምስራቅ የአፍሪካ ልዩ ልኡካን ይህን የአደራዳሪነት ሚና በተመለከት  ድርድሩ በአፍሪካ  ህብረት በኩል መሆን እንደሚገባው  እንደሚያምኑ አሳውቀው ነበር፡፡

በ ሀምሌ 30፣ 2014  (August 6, 2022)  በሪፖርተር ጋዜጣ የእንግሊዝኛ እትም እንደተዘገበው በአዲስ አበባና መቀሌ ተከስተው የነበሩት እነዚህ የአውሮፓ፣ የአሜሪካና፣ የተባበሩት መንግስታት ልኡካንንና የአፍሪካ ህብረት የሰላም ኮሚቴ አዲስ አበባ ላይ ባደረጉት ስብሰባ  የድርድሩ ሂደት በቀጣይነት በአፍሪካ ህብረቱ ተወካይ በኦባሳንጆ  ስብሳቢነት እንዲካሄድ አሚሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ደግሞ  በአደራዳሪው ቡድን ወስጥ እንዲካተቱ  የሚል ወሳኔ እንዳስተላለፉ ይፋ ሆኗል፡፡

AU Accommodates UN, EU To Broker Peace Between TPLF, Federal Government | The Reporter | Latest Ethiopian News Today (thereporterethiopia.com)

ይህ አዲስ ክስተት  በአጠቃላይ ፍትሀዊና ውጤታማ የድርድር  ሂደት አንጻር ሲመረመር የሚኖረው ጠቀሜታና ጉዳት በአጠቃላይም እንደምታው ምን ሊሆን ይችላል፣ ምንስ ያስከትላል ብሎ መመርመር እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ይህ ጽሁፍም ይህንኑ ይቃኛል፡፡ በማስከተልም የተሻለ ወጤት ለማስገኘት የሚያግዙ ምክረ አሳቦችንም ያቀርባል፡፡

አሽማጋዮች ወይም  አደራዳሪዎች ከወገንተኘነት የራቁ ራሳቸውንም ያወቁ የመሆን አስፈላጊነት

የቅራኔ አፈታት አዋቂዎች በተወሳሰቡ ችግሮችን ለመፍታት አሸማጋዮ ወይም አደራዳሪዎች ወጤታማ ለመሆን ከሚይስፈልጓቸው ጉዳዮች ውስጥ  አንዱና ቁልፉ ጉዳይ ራስን ማወቅ እንደሆነ ያስገነዝባሉ፡፡ 

አሽማጋዮች  ተጻራሪ ተደራራዲዎችን የማቴርያል የዲፐሎማሲ ወዘተ ድጋፍ በመስጠት ፣ የድርድር የሚሆን ወጪን በመሸፈን ሰለ ድርድር አካሄድ እውቀትን በማካፈል ወዘተ ሊያበረክቱት የሚችሉበት ብዙ ጉዳይ እንዳለ ሁሉ  አደራዳሪዎች የሚወክሏቸው መንግስታትና ድርጅቶች የቀደመ ወገንተኛነት፣መኖር   በድርድሩ ሂደት ነጻነትና፣ ተቀባይነት ላይ ታላቅ ተጸእኖ እንደሚኖረው ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ 

በመሰረቱ አሽማጋይ ወይም አደራዳሪነት  በተለይም በአለም አቀፍ ቅራኔ አፈታት ወስጥ  በከፊል የፖለቲካ መሳሪያ መሆኑን በግንዛቤ ውስጥ ማሰገባት ያስፈልጋል፡፡ መንግስታት ወይም ድርጅቶች በድርድር ሂደት በአሽማጋይነት ሲሰለፉ የራሳቸውን የውጭ ጉዳይ ጥቅም  በግንዛቤ ወስጥ አስገብተው እንደሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ አንዳንዱ አሽማጋይነት ውጤታማ እና ዘላቂ ሰላምን ለማስገኘትም ታላቅ አስተዋጸኦ እንደሚኖረው ሁሉ አንዳንዱ ደግሞ  በተፋላሚወች  የተፈጠረውን ችግር ከመፍታት ይልቅ ሁኔታውን አወሳስበው፣ እጅግ አስቸጋሪ  ምስቀልቀልን  በመፈጠር ይበልጥ ጥፋትን ሊጋብዝ ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሀያላኑ በአደራዳሪነት የሚሰለፉት ለችግሩ ቋሚ መፍትሄን ፤ለማስገኘት ሳይሆን የሚታየው ግጭት ከሚገኛበት ደረጃ አልፎ ሰፋ ያለ ጥፋትን ሳያስከትል ባለበት ደረጃ እንዳለ እንዲቆይ ለማድረግም ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌም በኮሶቮና በቦስንያ በ 1990 ወቹ መጨረሻ የሀያላኑ አላማ በከፊል ይህ ነበር፡ ለማለት ይቻላል፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአውሮፓ አቆጣጠር በ2012 ይፋ ባደረገው ዶክመንት በቅራኔ አፈታት ውስጥ  የአሽማጋይነት ሚናን ወጢታማ ለማድረግ ሊሟሉ የሚገባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው ብሎ ካቀረባቸው ስምንት ዋና ዋና ጉዳዮች ውስጥ ፣ የአሽማጋዮች ገለልተኛነት፣ (impartiality)  በተደራዳሪ ወገኖች በኩል  የአሸማጋዮች ተቀባይነት ማግኘት  (consent ) የሽምግልናው ሂደት ሀገር በቀል በሆነ  ባለቤትነት መመራቱ  (national ownership ) የሚሉት ሶስቱ ቁልፍ ጉዳዮች ናቸው፡፡UN Launches Guidance to Ensure Effective Conflict Mediation – Mediate.com

በዚህ አንጻር በሀገራችን የሰሜን ክፍል የተፈጠረውን ውስብስብ ችግር ለመፍታት በአዲስ መልክ በአደራዳሪነት የተጨመሩት የአሜሪካ መንግስት፣ የአውሮፓ ህብረትንና የ ተባበሩት መንግስታት  አቋም ምን ይመስላል? ለመሆኑ በዚህ  ግጭት ውስጥ እነዚህ ክፍሎች ገለልተኛ ናቸውን ፣ ድርድሩን በገለልተኛነት መምራትና ተአማኒ ሊሆኑስ ይችላሉን ለድርድር በሚቀርቡት ጉዳዮች ላይ ሊያስፈጽሙት የሚፈልጉት አቋም አላቸውን  ይህን የአደራዳሪነት መድረክ ተጠቅመው የነርሱን ፍላጎት ለማስፈጸም የሚያደርጉት አካሂድስ ከሀገራችን ፍላጎት ጋር ሲነጻጸር ምን ይመስላል ፣ ለመሆኑ  የመራባውያኑ የአድራዳሪነት መታከል የሁሉንም ተቀባይነት አግኝቷልን፣ የድርድር ሂደቱንስ፣ ሀገር በቀል ወይም አህጉራዊ ባለቤትነት እንዲኖረው ያድርጋል ወይንስ አሳልፎ ለመራብ ሀገሮች ይስጣል የሚሉትን ቀረብ ብሎ ማየት ያስገልጋል፡፡

የአደራዳሪዎቹና እጩ አደራዳሪዎቹ  አ ቋም ሲመዘን

የአሜሪካ መንግስት

የአሜሪካ መንግስት ከስሜኑ ጦርነት እየገፋ መምጣት ጋር ተያይዞ ጦርነቱ እንዲቆምና ችግሩንም ተፋላሚዎቹ ወገኖች በስላም እንዲፈቱ የሚል  እወጃ ሲያሰማ የቆየ ቢሆንም፣ በድርድሩ ውስጥ ዋና ዋና በሚባሉ ጉዳዮች ላይ ደግሞ ግልጽ አቋም ይዞ ይህ መደረግ አለበት የሚላቸውን ለማሰፈጸም በተለይም በኢትዮጰያ መንግስት ላይ ከፈተኛ ተጸእኖ ሲያደርግ ቅይቷል፡፡አሁንም እያደረገ  ነው፡፡  ከነዚህ ተጸኖዎች ውስጥ የተለያየ መእቀብ መጣል፣ የጸጥታ ትብብርናና  የበጀት ድጎማን መከልከል እና በተባበሩት መንግስታት ጸጥታ ምክር ቤት በአጀንዳነት አስይዞ የኢትዮጰያ መንግስት አለም አቀፍ ውግዘትና ተጸእኖ እንዲደረግበት በተደጋጋሚ ማድረጉ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በአሁኑ ሰአት በድርድሩ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረትን ይፈጥራል በሚባለው የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ፣ የአማራ ልዩ ሀይል በዚህ ቦታ የመገኘት ጉዳይ በተመለከትም  የአሜሪካ መንግስት የአማራ ልዩ ሀይል ከአካባቢው መውጣት አለበት በማለት ደግሞ  ደጋግሞ  በተላያዩ ባለስልጣናቱ በኩል መግለጫ ሰጥቷል፡፡  በተጨማሪም  በአካባቢው አለ የሚሉትን የኤርትራ ሰራዊትም ከ ኢትዮጰያ  መውጣት አለበት በማለት ፣ ኢትዮጰያ  የውስጥ አስተዳደር ክልሎች ድንበርን መቀየር የለባትም  ወዘት በማለት በአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ደግመው ደጋግመው በመግባት ሲናገሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ይህ መጠነኛ መረጃ የሚያሳየው የአሜሪካ መንግስት የትግራይ ግጭትን በተመለከተ እጅግ ጠንካራ አቋም ወስዶ እርሱንም ለማስፈጸም ከፍተኛ እርምጃን እእደወሰድ  ነው፡፡ ይህም የአሜሪካ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ገለልተኛ፣ (impartiality)   አለመሆኑን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው፡፡ 

አሜሪካ  በመላው አፍሪካና በተለይም በምስራቅ አፍሪካ  የ ቻይናን በቅርቡም የሩስያን እየተጠናከረች መምጣት አጥብቃ  የምትቃወም  ይህንንም ለማስቆም  የተለያየ እርምጃ እንደምትወስድ ይታወቃል፡፡  ከጥቂት ወራት በፊትም  የቻይና መንግስት በትግራይ በኩል የሚታየውን ግጭት በሰላም ለመፍታት እፈልጋለሁ ብሎ ለዚህ ቀጠና ልዩ መልእክተኛ  መመደቡም የሚታወቅ ነው፡፡ 

ከዚህም በተጨማሪ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የግብጸ መንግስት ፡ የሚያራምደውን አቋም  በአሜሪካ በኩል ለማስፈጸም ያደረገውንና አሁንም እያደረገ ያለውን ጥረት፣ የአሜሪካ መንግስትም ( ከፐሬዚደንት ትራምፐ እንደሰማነው)  የግብጽን አቋም ለማራመድ  ምን ያክል ሊጓዝ እንደሚችል በግልጽ የታየ ነው፡፡ 

በአሁኑ ሰአት የአሚሪካ መንግስት በኢትዮጰያ ጉዳይ ይዞ የሚጓዘውን ዘርፈ ብዙና የተወሳሰብ  ጉዳይ  ስናጤን የአሚሪካ  በአደርዳሪነት  መግባቱ   የሀገራችንን ችግር ከመፍታት ይልቅ እንዳያወሳስበው ያሰውጋል፡፡

የእውሮፓ ህብረት

የአውሮፓ ሀበረትም ከላይ የተነሱትን ጉዳዮች  በ ተመለከት ባለፉት ሁለት አመታት ያሳዩት አቋም ከአሜሪካ መንግስት የተለየ አይደለም፡፡ይህም መሰረታዊ የሆነውን የአሸማጋዮች ገለልተኛነትን አስፈላጊነት የሚቃረን የድርድር ወጤቱንም ከማገዝ ይልቅ አስቸጋሪ ቅርቃር ውስጥ ሊጥል የሚችል  አደጋ ነው፡፡

የተባበሩት መንግስታት

የተባበሩት መንግስታት ብዙውን ጊዜ በተመሳሳይ ቅራኔ አፈትት ሽምግልና ውስጥ ራሱን የሚያስገባው በጸጥታ ምክር ቤት ወሳኔና በቅራኔው ውስጥ የሚገኙት ክፍሎች በሚያቀርቡት ጥያቄ ወይም ግብዣ ነው፡፡የተባበሩት መንግስታት በተመሳሳይ ሂደት ውስጥ ራሱን ለመዝፈቅ እጅግ የሚጠነቀቅ ቢሆንም በተለይም ሀያላሁ መንግስታት የነርሱን አካሄድና ፍላጎት   ድጋፍ ለማስገኘት  ተሳታፊ እንዲሆን ከፍተኛ ግፊት ያካሄዳሉ ፡፡ በሀገራችን ሁኔታ ታዲያ በዚህ የድርድር ሂደት ውስጥ እንዴት ሊገቡ አንደቻሉ፣ የኢትዮጰያ መንግስት እንዲሳተፉ ጥሪ አድርጎ ነበርን የጸጥታው ምክር ቤትስ በዚህ ጉዳይ ላይ ተወያትቶ ወሳኔ አስተላልፎ ነበርን የሚለው ግልጽ አይደለም፡፡ 

በርግጥ የህወሀቱ ዶክተር ደብረጸዮን ተከታታይ ደብዳቤ ለተባበሩት መንግስታት እንደጻፈ ቢታወቅም የኢትዮጰያ መንግስት ተመሳሳይ ግብዣ መቅረቡ ኝ አይታወቅም፡፡

በዚህ አኳያ የተባበሩት መንግስታት በድርድሩ ቀጥተኛ አደራዳሪ ሆኖ መቅረብ ምናልባት ድርድሩ ውስጥ የሚነሱ የአደራዳሪዎች ሀሳብ የኢትዮጰያ መንግስት አልቀበልም ቢል ወታደራዊ ጣልቃ ግብነትን የሚጨምር አለም አቀፍ ተጸእኖ ለማድረግ ታቅዶ የተወሰደ እስትራተጂክ እርምጃ ነው ብሎ መገመትም ይቻላል፡፡

የአሸማጋዮች ተቀባይነት ማገኘት  (consent ) የሽምግልናው ሂደት ሀገር በቀል በሆነ  ባለቤትነት መመራቱ  (national ownership ) 

አለመታደልሆኑ የሰሜኑን የሀገራችንን ችግሮችም ሆኑ ሌሎች  በሀገር በቀል ድርጅቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ለመፍታት ኢትዮጰያውያን እልታደልንም፡፡ ትላንት ከትላንት ወዲያ  እጅግ ውስብስብ ችግሮችን በሱዳን፣ በናይጀሪያ ቢያፍራ ወዘተ ይፈቱ የነበሩ አባቶችና እናቶቻቸን ልጆች እንዳልሆንን ሁሉ እነሆ ዛሬ ቀራኔ ለመፍታት ሳይሆን ለማሽማገልም  አስቸጋሪ እየሆን መጥተናል፡፡

የሰሜኑን ግጭት ለመፍታት ለድርድር ሂደቱ በገራዊ ባለቤትነት ያስፍልጋል ሲባል ኢትዮጰያዊ አደራዳሪ ባይኖርም፣ በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ በአጀንዳ አቀራረጽ ፣ በአሸማጋዩች ምርጫ፣ ወዘተ ላይ ተፋላሚዎች ሙሉ ባልቤትነት ወይም ወሳኝነት እንዲኖራቸው ማድረግ አደራዳሪውም ኢትዮጰያዊ ድርጅት ባይሆንንም  ቢያንስ  አፍሪካዊ  የማድረግን አስፈላጊነት ያሳያል፡፡በዚህ አኳያ አፍሪካ ሰውም ብቃትም እንደሌላት በሚያስመስል ደረጃ የድርድሩን ሂደት ቁልፍ ተግባር፣ ማለትም አደራደሪነትን ለአውሮፓውያንና ለአሜሪካ መስጠትም ሀገር በቀል ባለቢትነት መንፈስን የሚጻረር ነው፡፡

አስፈላጊ ከሆነ የአፍሪካ ህብረት የድርድር ኮሚቴውን በአፍሪካውያን ባለሙያዎች እንዲጠናከር ማድረግ እጅግ መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ በተለይም በመላው አፍሪካ ብቻ ሳይሆን በመላው ጥቁር ህዝብ ዘንድ በነጻነታ ታላቅ ምሳሌ የሆነችው ኢትዮጰያ የውስጥ ችግሯን ለመፍታት ራሷ አለመቻሏ እጅግ አሳፋሪ ቢሆንም ከዚህ አልፎ ከአፍሪካዊ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሳይሆን የምራቡን አደራዳሪነት ማጋበዝ ታላቅ ሰነልቦናዊ ሽንፈትም ነው፡፡ አፍሪካ የደቡብ አፍሪካው የእነ ቶሞ ኢምቤኪ፣ የላይበሪያዋ ኤሊኖር ጆንሰንን የመሳሰሉ ታላላቅ ሰዎች ያሉባት አህጉር መሆኗ ሊዘነጋ ከቶውንም አይገባም፡፡ በዚህ አንጻር ያለ ሁሉም ተደራዳሪዎች ምእራባውያኑን ሀገራት  በአሽማጋይነት ማካተት  የራሱ የተባባሩት መንግስታት መመሪያን ብቻ ሳይሆን የአሸማጋዮች ተቀባይነት ማገኘት  (consent)  ጽነሰ ሀሳብ የሚጻረር ነው፡፡

ምን መደረግ አለበት

በሀገራችን ውስጥ የሰሜን ኢትዮጰያን ችግር ማስቀጥል ለኢትዮጰያ ሀዝብም ሆነ ለገዥው ድርጅት የሚያስገኘው ጠቀሜታ የለም፡፡ በተጻራሪው ግጭቱ እየቀጠለ ሲሄድ በአጠቃላይ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ፣ በኢንቨስተሮች  በካቲታል ፈሰት ፣ በቱሪዝም በሰላም ከቦታ ቦታ በምዘዋወር፣ በህዝብ መፈናቀል  ወዘት የሚያስከትለው አሉታዊ ተጸእኖ እጅግ ሰፊ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ሰላምን መምረጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡ ይሕንም ለማደረግ የተጀመረው ወይም ይጀመራል የሚባለው ድርድር እኩልነትን ተጠያቂነተን የህዝብን መብት፣ የሀገር አንደነትንና ወንድማማችነትን መሰረት ይደረገ ወጤትን ለማሰገኘት በሚችል መልኩ ና ማካሄድ ያስፈልጋል፡፡ ውስብስብ የሆነውን የሀገራችንን ግጭት የበልጥ ሊያወሳስቡ የሚችሉ አለም አቀፍ አጀንዳዎችን በዚህ ውስጥ እንዲታከሉ ማድረግ ጉዳት እንጂ ጥቅም የለውም፡፡ 

በዚህ አንጻር  በአፍሪካ አንድነት የተጀምረው የሽምግልና ሂደት ወጤታም እንዲሆን የሚከተሉትን ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

የኢትዮጰያ መንግስት

በመንግስት በኩል ይህን ጉዳይ ለብቻው ሊወጣው እንደማይችል ሊገነዘብ ይገባል ፡፡ ሀገር ውስጥ ድጋፍ የሌለው የድርድር ሂደት በድርድር ጠረጰዛ  ዙሪያም ተደራራዲዎችን በሙሉ ልብ እንዳይሰሩ ተጋላጭ ያደርጋል፡፡ በዚህ አንጻር የኢትዮጰያ መንግስት / ብልጽግና / ህዝብን በተመለከተ የተሰበረውን መተማመን ለመጠገን የሚያስችለው መሰረታዊ እርምጃዎችን በአስቸኳይ ሊወስድ ይገባል፡፡ የኢትዮጰያ መንግስት አባይን በተመለከት በተደረገው ድርድር በትራምፐ አስተዳደር የተሰነዘረበትን ተጸእኖ ተወጥቶ የሀገርን ጥቅም የሚያስከብር የድርድር አቋም የያዘው በጊዜው መሉ የህዝብ ድጋፍ አብሮት ሰለነበረ እንደሆነ ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ 

አሁንም  በየቦታው ከሚገኘው ማህበረስብ ጋር ግጭት ውስጥ የሚያስገቡትን ጉዳዮች  (ለምሳሌ በአማራ ክልል፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ ) ለመፍታት አዲስ ጥረት በመጀመር መተማመንን መገንባት መጀመር ይኖርበታል፡፡

ከዳያስፖራ ኮሚኒቲውም ጋር አስቸኳይ ምክክርን በማድረግ ቅሬታዎችን ለምፍታት አስቸኳይ እና ልባዊ ጥረት ሊያደርግ ይገባል፡፡

ከውስጥም ከውጭም የሚኖረውን ተጸእኖ ለመቋቋም ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ በአስቸኳይ መማካከር እና የጋራ አቋም በመያዝ  በቀጣይም የተቃዋሚው ድምጽ በድርድሩ ሂደት የሚደመጥበትን ሜካኒዝም ጊዜ ሳይፈጅ ከድርድሩ በፊት ሊያስተካክል ይገባል፡፡

ድርድሩ በአፍሪካ ድርጅት እና በአፍሪካውያን ብቻ መካሄድ እንደሚገባው የምእራባውያኑ ሚና በሚጠየቁበት ጉዳይ ላይ  ድጋፍ ከመስጠት ያለፈ ሊሆን እንደማይገባው  ይህም በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲደረግ በይፋ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

በኢትዮጰያ  ተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች

የተቃዋሚ ድርጅቶች መንግስትን መቃወምና የሀገርን ጥቅም አሳልፎ በመስጠት መሀል ያለውን ልዩነት እንደሚረዱ በመገንዘብ አሁን የመራባውያን  መንግስታት በድርድሩ ውስጥ በአስታራቂ ወይም የሽምጋይነት ለመግባት የቀረበው ሀሳብ ለሀገራችንና ህዝባችን ዘላቂ ጥቅም ላይ ሊያስከትለው የሚችለውን  እንደምታ በመገንዘብ ይህ ሽምግልና የአድራዳሪነት ተግባር ገለልተኛነትን በሁሉም ተቀባይነትን መሰረት አድርጎ ባአፍሪካ ህብረት ስር በሚዋቀር አፍሪካዊ አደራዳሪዎች ብቻ እንዲመራ መታገል ተጸእኖም ማድረግ ጊዜው የሚጠብቀው ተግባር ነው፡፡

ይህ ጉዳይ የሁለት ድርጅቶች ብቻ ሳይሆን የሀገር ጉዳይ ሰለሆን ተቃዋሚው በዚህ ሂደት በቀጣይነት ተሳታፊ ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ እንዲመቻች ለማድረግ ግፊት ያስፈልጋል፡

የአፍሪቃ ህብረት

የአፍሪካ ህብረት በአደራደሪነት ወይም አሽማጋይነት ሊቀርቡ የሚገባቸው ገለልተኛ ድርጅቶች፣ የመንግስታት ተወካዮች እና  ገለልተኛ ግለሰቦች ብቻ መሆን እንደሚገባቸው፣ በእጅ መጠምዘዝና በድብቅ በማስገደድ የሚገኝ መፍትሄ ዘለቄታ ያለው ሰላምን ሊያስከትል እንደማይችል ተረድቶ  በአስቸኳይ አሜሪካን እና የአውሮፓ ህብረትን የአደራዳሪነት ሚና በሌሎች አፍሪካዊያን ሊተካ ይገባል፡፡

የአሜሪካ መንግስት እና የአውሮፓ ማህበር 

የምእራቡ መንግስታትም ሆኑ የቀጠናው ጥቅም ሊጠበቅ የሚችለው በኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም ተቀባይነት ባለው የእርቅ ወይም ሽምግልና ሂደት ውስጥ አልፎ እውን በሚሆን የድርድር የሰጥቶ መቀበል እናም ፍትህና ባካተተ ሂደት ኢትዮጰያ ሰላም ስትሆን ነው፡፡  ይህንንም እውን ለማድረግ የመጀመሪያው ተግባር የአደራዳሪዎችን ገለልተኛ መሆን በሁሉም ተደርዳሪዎች ተቀባይነት ማግኘትን እናም ሂደቱ በተደራዳሪዎች ባለቤትነት ሊካሂድ እንደሚገባው  መቀበል፣ነው፡፡  ባለፉት ሁለት  አመታት የኢትዮጰያ ግጭት ወስጥ አሜሪካንም ሆነ አውሮፓ ህብረት ግጭቱን በተመለከተ ይዘዋቸው የቆዩትን ግልጽና ወገንተኛ አቋም በግምት ውስጥ በማስገባት ራሳቸውን ካደራዳሪነት ሊያገልሉ እንደሚገባ እሙን ነው፡፡ ይህ ማለት የድርድሩ ሂደት የሁለቱንም ሀያላን ድጋፍ አይፈልግም ማለት አይደለም፡፡ 

ሁለቱም ሀያላን ለድርድሩ ሲጠየቁ ቴክኒካል ድጋፍን በመስጠት፣  የድርድሩን ሂደት በፋይናንስ በመደገፍ፣  በተደራዳሪዎቹ የጋራ ፍላጎትና ውሳኔ ሊቀርቡ የሚችሉትን የተለያዩ የድጋፍ ጥያቄዎች  በመመርመርና በመደገፍ ሊተባበሩ የሚችሉበት ሰፊ እድል አለ፡፡እነዚህ ሀያላን ከአሁን በፊት በኢትዮጵጸያ የውስጥ አስተዳደር በሰራዊት አሰፋፈር፣ ወዘተ ላይ ያንጸባረቋቸው አቋሞች ግልጽ ቢሆኑም ከዚህ ወዲህ ግ ን በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ከመሰጠት ሙሉ በሙሉ በመቆጠብ የአደራዳሪዎቹን ነጻነት በማክበር  ይህ ሂደት የራሱህ  ይዞ እንዲጓዝ በማድረግ ገንቢ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሁሉም በኩል የሚገኘው የአትዮጰያ ህዝብ በጦርነቱ የደረሰበትን ጊዜያዊም ሆነ የረጅም ጊዜ ድጋፍ በሚሹ የስብአዊና የልማት  ተግባሮች ላይ ታላቅ ጋፍን በመስጠት እጅግ ጠቃሚ ሚና ሊጫወቱ ይችላል፡፡

የትግራይ ክልል እና አጣቃላዩ  የኢትዮጰያ ህዝብ

የትግራይ ክልል እና ቀሪው የኢትዮጰያ ህዝብም  ( በተለይም የአማራና የአፋር ክልል ነዋሪዎች)  መንግስትና ሀወሀት ራሳቸውን ችለው በውስጣቸው የተፈጠረውን ቅራኔ በሰላም ለመፍታት እንደማይችሉ ወደ ጦርነት የገቡበት እስካሁንም የቆዩበት ሂደት ራሱ በቂ ማስረጃ እንደሆነ ግልጸ ነውው፡፡ አሁንም ሁለቱ ድርጅቶች ለብቻቸው በሚያደርጉት ድርድር የህዝብን ችግር ከሰር ከመሰረቱ  ዘላቂ ሰላምን ሊያስከትል በሚችል መልኩ  ይፈታሉ ብሎ መጠበቅ እጅግ ይከብዳል፡፡ 

ሰለዚህም ህዝባችን ወደ ሌላ አስቃቂ የግጭት መእራፍ የሚያሸጋግረውን ሂደት ለማምከን የሚካሄደውን ድርድር በቅርብ በመከታተል ችግር  ፈጣሪ ወይም አደናቃፊ የሆኑ አካሄዶችንም በየደረጃው በመታገል ህዝባችን በአንድነት፣ በሰላም በወንድንማማችና እህትማማችነት ሊኖርበት የሚችል ድባብን  እውን ለማድረግ ግፊት ሊያደርገ ይገባል፡፡የኢትዮጰያ ህዝብ ሊጠቀም የሚችለው ከሰላም እንጂ ከጦርነት እንዳልሆነ ታሪካችን በተደጋጋሚ አሳይቶናል፡፡ ከዚህ ተምሮ ዳግም እንዳይከሰት መታገል ደግሞ የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት ነው፡፡ 

ሰላም ለኢትዮጰያ

ጸሃፊውን በሚከተለው አድራሻ ማግኘት ይቻላል ethioandenet@bell.net

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena 

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

1 COMMENT

 1. ትችታዊ መልስ ለአቶ አክሊሉ-

  በተለይም ሃይማኖትን አስታኮ የተነሱ አሸባሪ ኃይሎች ከ1980ዎቹ ዓመታት በፊት ያልነበሩና፣ በተለይም አሜሪካ ብቸኛው ኃያል መንግስት ሆኖ ከወጣበት ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ የተከሰት አዲስ ሁኔታ ነው ማለት ይቻላል። ለምሳሌ የአልሻባብን አፀናነስ ብንመለከት ከአልቃይዳ መወለድና ማደግ ጋር በጥብቅ የተያያዘ ነው። አልቃይዳ ደግሞ ሊፈጠር የቻለው የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ሶቭየቶችን ከአፍጋኒስታን ለማስወጣት በነበረው ስትራቴጂ የካርተር አስተዳደር ለታሊባኖች በጊዜው 500 000 000 $ ከመደበ በኋላ ነበር። ከአ1950ዎቹ ዓመታት ጀምሮ እስከ 1980ዎቹ ዓመታት ጊዜ ባለው ውስጥ አፍጋኒስታን ዘመናዊ የነበረችና የእስልምና አክራሪ ኃይሎች የሚታወቁ አልነበሩም። በሌላ አነጋገር፣ ለእስልምና አክራሪ ኃይሎች መፈጠር ዋናውን ሚና የተጫወተው አሜሪካ ነው ማለት ይቻላል። ከዚያ በኋላ የኢስላሚክ ስቴት(ISIS) አፀናነስን ለተመለከተ በሃሰት ውንጀላና በአሜሪካ የማን አለኝበት የሳዳም ሁሴን አገዛዝ እንዲደመሰስ ከተደረገ በኋላና እስከዚያ ጊዜ ድረስ የሳዳም አገዛዝ የገነባቸው ልዩ ልዩ ተቋማት ከፈራረሱ በኋላ ነው ማለት ይቻላል። ብዙ የምርምር ጥናቶች እንደሚያረጋግጡት ከሆነ አክራሪ ኃይሎች በተፀነሱባቸው አገሮች ሁሉ ዋናው ምክንያት የአሜሪካ ጣልቃ ገቢነት እንደሆነና፣ የአሜሪካ የስለላ ድርጅት(CIA) አክራሪ ኃይሎችን በመደገፍና በመገፋፋት ለአሜሪካ አንታዘዝም የሚሉ ኃይሎችን ለመጣል የሚጠቀምበት ስትራቴጂ አንደኛው ዘዴ እንደሆነ ይጠቁማሉ። ይህም ማለት የአሜሪካን ኤምፔሪያሊዝም የመስፋፋት ዕቅድና አገሮችን በእሱ የስትራቴጂ ክልል ውስጥ ማምጣትና የአሸባሪ ኃይሎች አነሳስና መጠናከር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው ማለት ይቻላል።
  ወደ አልሻባብ ስንመጣ አልሻባብ የሰይድ ባሬ አገዛዝ ስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ የሚታወቅ ጉዳይ አልነበረም። ሁላችንም እንደምናውቀው በሰይድ ባሬ አገዛዝ ዘመን የተቋቋመው አገዛዝ በፀና መሰረት ላይ ስላልነበረና፣ በተለይም በ1977 ዓ.ም ለመጨረሻ ጌዜ የአገራችንን የምስራቁ የተወሰነ ክፍል ከወረራና እንዲመለሰ ከተደረገ በኋላ እንደመንግስት ለመቋቋም አልቻለም። ምናልባት የምናስታውስ እንደሆነ በአብዮቱ ጊዜ የሰይድ ባሬ አገዛዝ ኢትዮጵያን እንዲወር አሜሪካና የሰሜኑ የጦር ስምምነት(NATO) ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ያደርጉ እንደነበር ይታወቃል። አብዮቱም ለመክሸፍ የቻለውና የመንግስቱ ኃይለማርያም አገዛዝ እንዲወድቅ የአሜሪካ የስለላ ድርጅትና የአሜሪካ መንግስት ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ወያኔና ሻቢያ አዲስ አበባ ድረስ ለመምጣትና ስልጣን ላይ ቁጥጥ ለማለት የቻሉት ከአሜሪካ የስልለላ ድርጅት ጋር ይሰሩ ከነበሩ ኢትዮጵያውያን የሚሊታሪ፣ የስለላና የሲቪል ቢሮክራቶች አማካይነት ነው። አልሻባብም ቀስ በቀስ መጠናከር የቻለው ወያኔና አሜሪካ በሱማሊያ ውስጥ ጣልቃ ከገቡ በኋላ ነው። የወያኔ ወታደርም ሆነ የአሜሪካን በሶማሌ ውስጥ ጣልቃ መግባት አልሻባብን በምንም ዐይነት አላዳከመውም። ምክንያቱም አሜሪካኖች የሚከተሉት ስትራቴጂ የተሳሳተ ስለሆነ ነው። በአንድ አገር ውስጥ አሸባሪ ኃይልን ለማዳከምና የመጨረሻ መጨረሻም ለማስወገድ የግዴታ ሰፋ ያለና የጠነከረ ተቋማት መገንባት ሲያስፈልግ፣ በዚያው መጠንም ኢኮኖሚው ሰፋ ባለ መልክ መደራጀትና አለበት። በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ የሚመካበት መንግስታዊ ተቋም ካለና ኢኮኖሚውም በጠንካራ መሰረት ላይ ከተገነባ አሸባሪ ኃይሎች የመፀነስ ዕድል አይኖራቸውም ማለት ነው። አሜሪካኖችና የተቀረው የምዕራቡ ካፒታሊስ ዓለም ይህንን ማድረግ አይፈልጉም። አሜሪካንም ሆነ የተቀሩት የካፒታሊስት አገሮች ዕድሜያቸውን ለማራዘም የሚችሉት አገሮችን ወደ ጦር አውድማነት የለወጡ እንደሆን ብቻ ነው።
  ወደ አገራችን ተጨባች ሁኔታ ስንመጣ ከአልሻባብ ይልቅ ለአገራችን ብሄራዊ ነፃነትና ለህዝባችን በከፍተኛ ደረጃ አደገኛ እየሆነ የመጣው ስልጣን ያለው የጽንፈኛው የአቢይ አገዛዝ ነው። አራት ዓመት ያህል ተኩል በተለይም አማራውን ከነበረበት ቀዬው ያፈናቅላል፤ እንዲገደልም ያደርጋል። በወለጋና፣ በሻሸመኔና በሰሜን ሸዋ ለደረሰው የህዝባችን መሞት፣ መንደሮችና ከተማዎች መፈራረስ፣ እንዲሁም ህዝቡ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ ተጠያቂው አቢይ አህመድና ሺመልስ አብዲሳ እንጂ አልሻባብ አይደለም። አቶ አክሊሉ በሀተታህ ውስጥ አንድም ቦታ ላይ የአገዛዙን ፋሺሽስታዊ ድርጊትና ዘራፊነቱን በፍጹም ለማሳየት አልቻልክም።
  የኢኮኖሚውን ጉዳይ ለተመለከተ አሜሪካና ግብረአበሮቹ ማዕቀብ ማድረግ ከጀመሩ ጊዜ አይደለም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መንኮታኮት የጀመረው። በመጀመሪያ ደረጃ መንኮታኮት የሚለው ፅንሰ-ሃሳብ ለሳይንሳዊ ገለጻ የሚያመች አይደለም። ከ1950ዎቹ ዓመታት ጀምሮ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አወቃቀር ለተመለከተ ኢኮኖሚው በጸና መሰረት ላይ የተገነባ አለመሆኑን ነው። በኢኮኖሚው ውስጥ ይታይ የነበረውን የተቋም ቀውስ ለመቅረፍ በደርግ አገዛዝ ዘመን አንዳንድ እርምጃዎች ለመወስድ ቢሞከረም በነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ ጤናማ ኢኮኖሚ ማወቀር አልተቻለም። ወያኔ ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ተግባራዊ እንዲያደርግ የተሰጠው ትዕዛዝ የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚ የሚባለውን በይበልጥ ውንብድናንና ብልግናን የሚያስፋፋና፣ በተለይም ደግሞ ጥቂቱን በማበልጸግ አብዛኛውን ህዝብ የሚያደኸይ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው። የአሜሪካኖችና የተቀረው የምዕራቡ ካፒታሊስት አገሮች ስትራቴጂ ማንኛውም አገር ራሱን እንዳይችል ማድረግ ነው። ይህም ማለት፣ ማንኛውም አገር በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚና ሰፋ ያለ የውስጥ ገበያ ኢኮኖሚ እንዳይገነባ ማድረግ ነው። ስለሆነም በህውሃት አገዛዝ ዘመን አደገ የተባለው ኢኮኖሚ በንግድና በተቀረው የአገልግሎት መስክ ላይ የተመሰረተ እንጂ በትናንሽ፣ በማዕከለኛና በትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ላይ የተመረኮዘ አልነበረም። አንድ አገር ኢኮኖሚዋ ሊጠነከርና ህዝቦቿንም ልትመግብ የምትችለው በሁሉም አቅጣጫ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሰፋ ያለ ኢኮኖሚ ስትገነባ ብቻ ነው። ሌሎች ነገሮች ሁሉ ሊጠናከሩ የሚችሉት በዚያ አማካይነትና በተለያዩ ዘርፎች መሀከል መተሳሰር ሲኖር ብቻ ነው። የውጭው ዕርዳታ ስለቀነሰ ወይም ማዕቀብ ስለተደረገ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ተከሰከሰ የምትለው ትክክለኛ አባባል ያልሆነና ኢ-ሳይንሳዊ ነው። ስለፖለቲካ ኢኮኖሚ፣ ስለብሄራዊ ኢኮኖሚ አገነባብ፣ ሰለመንግስት አወቃቀርና በሰለጠነ ተቋማት ላይ መቆም፣ ስለሙያ ማስልጠኛ ተቋማት መኖር… ወዘተ. ግንዛቤ ካለ የአንድ አገር ኢኮኖሚ የመከስከስ ጉዳይ ሊታይ አይችልም። የአንድን አገር ኢኮኖሚ መጠናከርና መዳከም እንደ ሰውነታችን መታየት ያለበት ጉዳይ ነው። ሰውነታችን በልዩ ልዩ ኦርጋኖች በመደገፍና በስራ-ክፍፍል አማካይነት ነው ሊንቀሳቀስ የሚችለው። ከዚህም በላይ ለጤንነት የሚስማማ ምግብ ከተመገብንና ስፖርትም ከሰራን የማሰብና የመስራት ኃይላችንም ከፍ ይላል። ብዙ ዓመታትም ልንኖር እንችላለን። በአንፃሩ ጤንነትን የሚያቃውሱ ምግቦች ከበላን፣ በየቀኑ አልክሆል ከጠጣንና ሲጋራ የምናጨስ ከሆነ ጤንነታችን ይቃወሳል። የእኛ ሰውነት ጤንነት ሊወሰን የሚችለው ባለን ንቃተ-ህሊና አማካይነት ነው። የአንድ አገርን ኢኮኖሚ፣ የሰላምን መኖር፣ የመፍጠርና የስራን ባህል ማዳበር ጉዳይ ሊወሰን የሚችለው የሚያስብ መንግስታዊ ኃይልና ሰፋ ያለ በሁሉም መስክ ሊሰማራ የሚችል የተማረ የሰው ኃይል ሲኖር ብቻ ነው።
  በአጭሩ የአገራችን ሁኔታ በእኛ የሚወሰን እንጂ በአሜሪካኖችና በተቀሩት የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮች አማካይነት ነው። እንደዚህ ብለን የምናስብ ከሆነ ሰው አይደለንም ወይም እንደሰው አንቆጠርም ብሎ እንደማሰብ ነው። ቻይናዎች በራሳቸው ኢንተለጀንስና በመንግስታቸው ታታሪነት አማካይነት ይኸው እንደምናየው ወደ ኃያል መንግስትነት በመለወጥ ላይ ናቸው። አሜሪካንና የተቀሩትን የካፒታሊስት አገሮች እያሯሯጣቸው ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን ባለን እጅግ ደካማ ንቃተ-ህሊና ምክንያት የተነሳ ሁልጊዜ የምዕራቡን ዓለም እየተማፀን እንኖራለን። ካለነሱ ቡራኬና ፈቃድ ምንም ነገር መስራት የምንችል አይመስለንም። በጣም የሚያሳዝን አስተሳሰብ።
  ለማንኛውም የአገራችን ፖለቲካ አስተማማኝ በሆነ መሰረት ላይ ከተገነባ፤ ህዝባዊ ተሳትፎ ካለ፣ ህዝቡ ከተማረና ከነቃ፤ ዘመናዊና የሰለጠኑ ተቋማት በየቦታው የሚገነቡ ከሆነ፣ ኢኮኖሚው ሰፋ ባለ መልክና ከህዝባችን ፍላጎት አንፃር የሚዋቀር ከሆነ፣ ለሰፊው ህዝብ፣ በተለይም ለወጣቱ የሙያ ማስለጠኛ ተቋማት ከተከፈቱና ከሰለጠነም በኋላ ተቀጥሮ የሚሰራበት ዕድል ካጋጠመው፣ መንደሮችና ከተማዎች በስርዓትና ባህላዊ በሆነ መንገድ የሚገነቡ ከሆነ፣ አንድን አገር አንደ አገር የሚያሰኙት አስፈላጊው ነገሮች ከተነጠፉ… ወዘተ. አልሻባብም ሆነ ሌሎች አሸባሪ ኃይሎች እንደስጋት ሊቆጠሩ አይችሉም። አሸባሪ ኃይሎች የሚፈጠሩት ቀዳዳ ነገሮች በመጠቀም ብቻና ደካማ መንግስት ካለ ብቻ ነው። ስለሆነም ዲሞክራቲክ ኢትዮጵያን ከመገንባት ውጭ ሌላ አማራጭ ነገር ሊኖር በፍጹም አይችልም።
  በተረፈ ሰፋ ላለ ጥናት የሚከተለውን ድረ-ገጽ፤ http://www.fekadubekele.com
  ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here