
ቦርከና
ጀማል ሰይድ
ከአሜሪካ የአፍሪካ ከቀረጥ ነፃ የንግድ ቀጠና ተጠቃሚነት የኢትዮጵያን መከልከልና ሌሎች የገበያ ተፅዕኖዎችን ለመቋቋም በተደረገ ጥረት የወጪ ንግድ የገበያ መዳረሻዎችን የማስፋት አካሄድ ከኤክስፖርት የሚገኘውን ገቢ ውጤታማ ማድረግ መቻሉን ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የውጭ ንግድ መሪ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ገመቺስ መላኩ እንደገለፁት፤ በጀት ዓመቱ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የአፍሪካ ከቀረጥ ነፃ የንግድ ቀጣና ተጠቃሚነት መከልከልና ሌሎች የገበያ ተፅዕኖዎች ስር የነበረችበት ጊዜ ነው።በዓለም አቀፍ እና የውስጥ ችግር የተፈተነችው ኢትዮጵያ የወጪ ንግድ የገበያ መዳረሻዎችን በተለያዩ አገራት በማስፋፋት ኤክስፖርቱን ውጤታማ ማድረግ ችላለች።
ኢትዮጵያ ገበያዋን አስፋፍታ ተጠቃሚ የሆነችባቸውን አገራት በየዘርፉ ከፍለው የተናገሩት አቶ ገመቺስ፤ እሥራኤል፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች፣ ቬትናም፣ ሲንጋፖርና ቱርክ ከኢትዮጵያ የቅባት እህሎችን በከፍተኛ ደረጃ ሲቀበሉ የነበሩ አገራት ናቸው ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ ሕንድ፣ ኢንዶኔዥያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች፣ ፓኪስታንና የመን ከ10 ሺህ ቶን በላይ የኢትዮጵያ የጥራጥሬ ሰብሎች የተቀበሉ አገራት መሆናቸውን ጠቅሰዋል።በበጀት ዓመቱ ሶማሊያና ጅቡቲ ከፍተኛ የጫት መጠን ከኢትዮጵያ በመቀበል የተመዘገቡ አገራት መሆናቸውም ተጠቁሟል::
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena