
ጀማል ሰይድ
ቦርከና
ኤክስፖው ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች ለማስተዋወቅ ያለመ ነው። ኤክስፖው ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጅዎች ለማስተዋወቅ እና በቴክኖሎጂ ዙሪያ አፍሪካንና የሌላውን አለም የንግድ ትስስር ለማበረታታት የተዘጋጀ ነው ተብሏል።
ከአፍሪካ፣ ከአውሮፓ፣ከእስያ፣ ከሰሜን አሜሪካ አንጋፋ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበትም ተገልጿል። ከ45 ሺህ በላይ ጐብኚዎችና ገዥዎች የአፍሪካ ቴክ ኤክስፖን ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።
የዘንድሮውን ኤግዚቢሽን ለየት የሚያደርገው በሶላር ቴክኖሎጂ፣ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች፣በዲጂታል ክፍያ ስርአቶች፣ ቴሌኮሙኒኬሽን የባንክ ስራዎች፣( በኦንይን የባንክ ቴክኖሎጂዎች ላይ ፈጠራዎችን ጨምሮ) በኢንሹራንስ ላይ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥበት ነው ኤክስፖውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው ጆርካ ኤቭንት ኦርጋናይዘር ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ማርኬቲንግና ኮሙኒኬሽን ሀላፊ አቶ ሳምሶን ሀይለእየሱስ የገለፁት።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ይህ ኤክስፖ በአዲስ አበባ መካሄዱ በርካታ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጠቀሜታው ጉልህ ነው ብለዋል። ኤክስፖው ለቴክኖሎጂና እውቀት ሽግግርን ይጠቅማል ያሉት አምባሳደሩ፣ ለአገር ገጽታ ግንባታ ያለው ጠቀሜታም ከፍተኛ ነው። ለሰላም መከበርና ለዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደሚጠቅም ገልጸዋል።
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena






