advertisement

ጀማል ሰይድ
ቦርከና
በደሴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አገልግሎት የሚሰጡ የላቦራቶሪ እቃዎች ተሠርቀው ሊወጡ ሲሉ በጥበቃ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዶክተር ሀይማኖት አየለ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ገልጸዋል፡፡
ከወረራ በኋላ ለቆጠራ ታሽጎ የነበረው የላብራቶሪ ስቶር ክፍል ተከፍቶ 4 ማይክሮስኮፕ: 1 የኬሚስትሪ ማሽን ፕሪንተር 1የላብራቶረ ድቫይደር 5የበር ዶረሎክ ቁልፍ ተሠርቀው ሊወጡ ሲል ተይዟል፡፡
እንደ ዶክተር ሀይማኖት ገለጻ ከዚህም በፊት መድሀኒት ተሠርቆ ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል፡፡ የመድሀኒት ኦዲት ስራ ተሰርቶ 600ሽህ ብር በጉድለት የተገኘ ሲሆን አጥፊውን በዲስፕሊን እርምጃ በመውሰድ የተባረረ ሲሆን ጉድለቱን የክፍሉ ባለሙያዎች እንዲከፍሉ ተደርጎል፡፡
ሆስፒታሉ አሰራሩን እያሻሻለ ሲመጣ ልዩ ልዩ ያልተገባ ጥቅም የለመዱና የሚፈልጉ አካላት ወደ ስርቆትና ስም የማጥፋት ዘመቻ ገብተዋል ሲሉ ዶክተር ሀይማኖት ገልጸዋል ሲል የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena