
ጀማል ሰይድ
ቦርከና
ከተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ተነስተዉ ደብረ ብርሃንን አቋርጠዉ ወደ አዲስ አበባ የሚጓጓዙ መንገደኞች እንግልት እየደረሰባቸዉ ስለመሆኑ ሰሞኑን በተደጋጋሚ ሲገልፁ ተደምጧል፡፡
ዛሬ ደግሞ ጫጫ ከተማ ላይ መንገድ በመዘጋቱ ወደ አዲስ አበባም ሆነ ከአዲስ አበባ ወደ ምስራቅ አማራ የሚመጡ በርካታ ተሽከርካሪዎች ቆመዋል። ተጓዦችም ለእንግልት ተዳርገዋል።
መንገዱ የተዘጋው ሰሞኑን ወደ አዲስ አበባ በሚጓዙ መንገደኞች ላይ በኦሮሚያ ክልል ከተሞች ሲደርስ በነበረው እንግልት ቁጣ ውስጥ በገባው የጫጫና አካባቢው ማህበረሰብ መሆኑን በስፍራው የሚገኙ ምንጮች ገልፀዋል። ደብረ ብርሃንም ላይ በተመሳሳይ መንገድ ተዘግቷል። የደብረ ብርሃን ዞናል መናሃሪያ አገልግሎት መስጠት አቁሟል፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ትራንስፖርት መምሪያ ኀላፊ ሲሳይ ወልደአማኑኤል፤ መንገደኞችና አሽከርካሪዎች እስከዛሬ ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱ መቆየታቸዉን አስታዉሰዉ ለችግሩ መፍትሄ ባለመቀመጡ አሁን ጉዳዩ የከፋ ገፅታ መላበሱን ገልጸዋል፡፡
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena