spot_img
Sunday, September 24, 2023
Homeአበይት ዜናየህዳሴው ግድብ 2ኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ

የህዳሴው ግድብ 2ኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ

advertisement
የኃይል ማመንጫ   _ የኢትዮጵያ ሕዳሴ

ጀማል ሰይድቦርከና
ነሃሴ 5, 2014 ዓ. ም.

በአፍሪካ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ  የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በሁለተኛ ተርባይኑ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀምሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ነው በዛሬው ዕለት ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረው።

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል ዩኒት 9 የሚባለው ሁለተኛው ተርባይን የተሳካ ተከላ እና ሙከራ ከተደረገ በኋላ ኃይል የማመንጨት ስራው እውን ሆኗል። ዛሬ በይፋ ሥራ የጀመረው ሁለተኛው ዩኒት 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል።

በተያዘው ዓመት ከስድስት ወራት በፊት የካቲት 13፣2014 ዓ.ም  ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ታሪካዊ  የተባለለትን 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ዩኒት 10 የሚባለው  የመጀመሪያው ተርባይን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በስኬት ኃይል የማመንጨት ስራ መጀመሩም የሚታወስ ነው፡፡ 

ግድቡ በአጠቃላይ የሚኖሩት 13 ተርባይኖች ግንባታና ተከላ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የማመንጨት አቅም 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት ይደርሳል።

__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 

ትዊተር@zborkena

ፌስቡክ ፡ Borkena

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,682FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here