spot_img
Wednesday, October 4, 2023
Homeአበይት ዜና"የኢትዮጵያ አየር ኃይል የአየር ክልሉን ከማንኛውም ጥቃት መጠበቅና መከላከል የሚያስችል ቁመና ላይ...

“የኢትዮጵያ አየር ኃይል የአየር ክልሉን ከማንኛውም ጥቃት መጠበቅና መከላከል የሚያስችል ቁመና ላይ ነው” ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ 

advertisement

ቦርከና
ጀማል ሰይድ

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሀገሪቷን አየር ክልል ከማንኛውም ጥቃት መጠበቅና መከላከል የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከ93 ዓመት በፊት በአፍሪካ የመጀመሪያ አየር ኃይል ኾኖ የተመሠረተ አንጋፋ ተቋም ነው። 

በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ነሐሴ 12/1921 ዓ.ም ‘ጃን ሜዳ’ ላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምሥረታ ከተበሰረ በኋላ በ1954 ዓ.ም በኮንጎ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ የጎላ ተሳትፎ ማድረጉም ተመልክቷል፡፡ ኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ለኢዜአ እንዳሉት፤ አየር ኃይሉ ቴክኖሎጂ በማፍለቅና የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት በ2022 ዓ.ም ከአፍሪካ ቀዳሚ የአየር ኃይል የመኾን ራዕይ ሰንቋል፡፡ 

የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት ቀደም ባሉት ዓመታት በፖለቲካ አመለካከት እና በብሔር ማንነት ተከፍለው አየር ኃይሉ ችግር ውስጥ ወድቆ እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡  ከለውጡ በኋላ ግን ይሄንን አስተሳሰብ በመቀየር የሠራዊት አባል ኹሉ ከፖለቲካና ከብሔር አስተሳሰብ እንዲወጣ በማድረግ ኢትዮጵያዊ መልክ ያለው አየር ኃይል መገንባት ተችሏል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ያላትን የተለያየ መልከዓ ምድራዊ አቀማመጥና የተለያየ አየር ጸባይ መቋቋም የሚችል ሠራዊት መገንባት የሚያስችል ጸጋ ያላት ሀገር መኾኗንም አንስተዋል፡፡ 

በዚህ ወቅትም የኢፌዴሪ አየር ኃይል “ለታላቅ ሀገር ታላቅ የአየር ኃይል” በሚል መሪ ሐሳብ የዘመኑን ቴክኖሎጂ የሚረዳ የሰው ኃብት፣ ዘመናዊ ትጥቆችና የውጊያ መሠረተ ልማት አሟልቷል ነው ያሉት፡፡ ሌተናል ጀነራሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል የአየር ክልሉን ከማንኛውም ጥቃት መጠበቅና መከላከል የሚያስችል የተሟላ ቁመና ላይ መኾኑን አረጋግጠዋል፡፡ ሠራዊቱ የኢትዮጵያን የአየር ክልል 24 ሰዓት ሙሉ በተጠንቀቅ እየጠበቀ መኾኑን የገለጹት ሌተናል ጀነራል ይልማ፤ አየር ኃይሉ በማንኛውም ሁኔታ ለግዳጅ ዝግጁ የኾነ ኃይል ነው ብለዋል፡፡በዚህም ሠራዊቱ በየቀኑ የመሳሪያ፣ የአካልና የዕውቀት ፍተሻ በማድረግ የተሟላ ሥነ-ልቦና ተላብሶ ሀገሩን እየጠበቀ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡
_

በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,733FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here