spot_img
Saturday, September 30, 2023
Homeዜናየጉራጌ ዞን ምክርቤት በክልል የመደራጀት ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ "ሁከትና ብጥብጥ በሚፈጥሩ አካላት...

የጉራጌ ዞን ምክርቤት በክልል የመደራጀት ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ “ሁከትና ብጥብጥ በሚፈጥሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ” እንደሚወስድ የጉራጌ ዞን የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ገለፀ

advertisement

ቦርከና
ጀማል ሰይድ

የጉራጌ ዞን የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሌተናንት ኮሎኔል ፈጠነ ፍስሃ እንደገለፁት የጉራጌ ዞን ምክርቤት በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሀሳብ ላይ በጥልቀት ከተወያየበት በኋላ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አድርጓል። የዞኑ ምክርቤት በክልል የመደራጀት ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ህብረተሰቡ ደስታውን በተለያየ መንገድ እየገለጸ ሲሆን ህብረተሰቡ ደስታውን ሲገልጽ በሰላማዊ መንገድ መሆን እንዳለበት አስተባባሪው አሳስበዋል።

የዞኑ ህዝብ ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል። በቀጣይ የዞኑ ምክርቤት ያጸደቀው በክልል የመደራጀት ውሳኔ መንግስት ምላሽ እስኪሰጥበት ድረስ የዞኑ ህዝብ በትዕግሥት መጠበቅ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የዞኑ ህብረተሰብ የአካባቢውን ሰላም ሲያስጠብቅ እንደነበረ የገለጹት አስተባባሪው እስካሁን በነበረን ቆይታ ከህዝቡ ጋር ተግባብተን ስንሰራ ነበር ። በቀጣይም የአካባቢውን ሰላም እንደሚያስጠብቁ እምነታቸውን ገልጸዋል። በቀጣይም የህብረተሰቡን ሰላም ለማወክ የሚንቀሳቀሱ የውስጥና የውጭ ጠላቶች በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ሁሉም የዞኑ ነዋሪዎች ለጸጥታ አካላት መረጃ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል ሌተናንት ኮሎኔል ፈጠነ ፍስሃ ።

ምንጭ:-የጎራጌ ዞን ኮምንኬሽን

__

በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,705FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here