
ጀማል ሰይድ
ቦርከና
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 9/2014 በጽህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ በቅርቡ ከፓርቲው ፕሬዝዳንትነት መልቀቃቸውን ያሳወቁት አቶ እስክንድር ነጋን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል።
የባልደራስ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አምሃ ዳኛው፤ የፓርቲው አመራሮች አቶ እስክንድር ስላሉበት ሁኔታ ከእርሳቸው በቀጥታ መረዳት ባይችሉም፤ “የመታፈን አደጋ ደርሶባቸዋል” የሚል እምነት እንደሌላቸው አስታውቀዋል።
“ባልደራስ እስክንድርን ከድቷል ወይስ እስክንድር ነው ባልደራስን የከዳው?” በሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበ ጥያቄ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ በሰጡት ምላሽ፤ “እስክንድርን ሊከዳ የሚችል ፓርቲ አይኖረንም። የተሰበሰብነውም እስክንድር ብለን ነው” ብለዋል። “እስክንድርን ያህል የጽናት ተምሳሌት፤ ባለበት የፖለቲካ ጫና ምክንያት ከፖለቲካ ትግሉ ገሸሽ አለ ማለት፤ ፖለቲካው ላይ ያለው ተጽዕኖ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መረዳት [የሚያስችል ነው]” ሲሉም ተናግረዋል ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena