advertisement

ጀማል ሰይድ
ቦርከና
የከፍተኛ ትምህርትን አገራዊ ቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የተዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ማስፈፀሚያ መመሪያ ፀድቋል።
መመሪያው በፍትህ ሚኒስቴር ተመዝግቦ እና ፀድቆ ለትግበራም ይፉ ሆኗል። መመሪያው በመውጫ ፈተና ዝግጅት ሊካተቱ ስለሚገባቸው ሃገራዊ ዝቅተኛ የትምህርት ብቃት መመዘኛዎችን ፣ የሙያ ሥነምግባር ደምቦችን እና ተቋማት ሊከተሏቸው የሚገቡ የአሠራር ስነ- ስርዓቶችን አካቷል ።
መመሪያው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሠለጠነ የሠው ሀይል ለማፍራት ከሚደረጉ ማስፈፀሚያ ስልቶች አንዱ ነው። በመመሪያው ዝግጅት ሂደት ውስጥ በስርዓተ ትምህርት እና ፈተና ዝግጅት ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣የሙያ ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ግብአት ሰጥተውበታል ።
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena