
ጀማል ሰይድ
ቦርከና
ሰመራ ውስጥ በሚገኝ የማቆያ ካምፕ ውስጥ ያለፈቃዳቸው ተይዘው ከነበሩት መካከል የተወሰኑት በአውቶብሶች እና የደረቅ ጭነት መኪኖች ተሳፍረው ወደ ቀደመ መኖሪያቸው እየተወሰዱ እንደሆነ ትናንት ነሐሴ 10/2014 ዓ.ም. ለቢቢሲ ገልጸዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩት የትግራይ ተወላጆች ከአፋሯ አብኣላ ተይዘው ወደ ሰመራ
መዘዋወራቸውን ለቢቢሲ ገልጸው ነበር።
ከስምንት ወራት እስር በኋላም ወደ አብኣላ እየተመሰሉ መሆኑን ተናግረዋል።
በሰመራ ተይዘው የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሰዎቹ “በብሔራቸው” ምክንያት ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ተይዘዋል ብሎ ነበር።
የትግራይ ተወላጆቹ ወደ ቀደመ የመኖሪያ ስፍራቸው እንዲመለሱ ሲያመቻች የነበረው የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ ሰዎቹን “የአገር ውስጥ ተፈናቃይ ሲል” ገልጿቸዋል።
በሰመራ ያለ ፍላጎታቸው ተይዘው ከነበሩ ሰዎች መካከል ቃላቸው ለቢቢሲ የሰጡ፤ ከመኖሪያቸው በአፋር ክልል ፀጥታ አስከባሪ ኃይል አባላት ተይዘው ወደ ሰመራ መወሰዳቸውን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በበኩላቸው ሰዎቹ ከነበሩበት ቦታ እንዲዘዋወሩ የተደረገው ግጭት መስፋፋቱን ተከትሎ ለራሳቸው ደኅንነት ነው ብለው ነበር።
በሺዎች የሚቆጠሩት እዚህ ሰዎች ለወራት ተይዘው በቆዩበት ካምፕ ውስጥ የምግብ እና ሌሎች አገልግሎቶች ችግሮች እንደነበሩባቸው የተናገሩ ሲሆን፣ ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተጋልጠው መቆየታቸውን ተናግረዋል።
ሁለት ዓመት ሊሞላው የተቃረበው ጦርነት ከትግራይ ጠነስቶ ወደ አፋር ክልል ከተዛመተ በኋላ በርካታ ሰዎች ለመፈናቀል መዳረጋቸውን የረድኤት ድርጅቶች መግለጻቸው ይታወሳል።
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena