spot_img
Thursday, November 30, 2023
Homeአበይት ዜናጀርመን በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለመፍታት እየተወሰደ ያለውን ተግባር እንደሚትደግፍ ገለጸች

ጀርመን በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለመፍታት እየተወሰደ ያለውን ተግባር እንደሚትደግፍ ገለጸች

advertisement
የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን በጀርመን

ጀማል ሰይድ
ቦርከና

በጀርመን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን በጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና ላቲን አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ክርስትያን ባክ (ዶ/ር) ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ በወቅቱም በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እየተረጋጋ እና እየተሻሻለ መሆኑን ያስረዱት አምባሳደሯ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ምክክር ለማድረግ እየተደረገ ያለውን ጥረት፣ የሰሜኑን ግጭት በሰላማዊ ድርድር ለመፍታት እየተወሰዱ ስላሉ እርምጃዎች፣ ሦስተኛ ዙር የሕዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በድርቅ፣ ጎርፍ፣ ግጭት እና በረሃ አንበጣ ምክንያት ችግር ለደረሰባቸው በአማራ፣ አፋር፣ ትግራይ እና ሶማሌ ክልል ለሚገኙ ወገኖች የሰብአዊ ዕርዳታ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸውም ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ የሚገኙ አገራትን ለመርዳት የሰላም አስከባሪ ኃይል በማሰማራት የበኩሏን ሚና እየተጫወተች መሆኗንም ገልጸዋል፡፡

ክርስትያን ባክ (ዶ/ር) በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ላለው ሰላምና መረጋጋት ወሳኝ አገር መሆኗን ጀርመን እንደሚትገነዘብ ገልጸው በአፍሪካ ሕብረት መሪነት በሰሜኑ ያለውን ግጭት ለመፍታት እየተወሰደ ያለውን ተግባር አገራቸው እንደሚትደግፍ መሳወቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here