spot_img
Monday, October 2, 2023
Homeአበይት ዜናየትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ነኝ የሚለው ወገን በትግራይ እና በፌድራሉ መንግስት...

የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ነኝ የሚለው ወገን በትግራይ እና በፌድራሉ መንግስት ላለፉት ስድስት ወራት በሶስተኛ ወገን የተደረሰው የተኩስ አቁም ተጣሰ የሚል ስሞታ አሰምቷል

advertisement
Ethiopian News _ TPLF

ጀማል ሰይድ
ቦርከና

የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ በትግራይ እና በፌድራሉ መንግስት ላለፉት ስድስት ወራት በሶስተኛ ወገን የተደረሰው የተኩስ አቁም መጣሱን አስታውቋል

የወታደራዊ ሰራዊት ኮማንዱ ይህን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል፡፡ እንደሚከተለው ቀርቦአል:-

በኢትዮጵያና በትግራይ መንግስታት መካከል በሦስተኛ ወገን በኩል ለሰብአዊነት ሲባል ግጭትን የማቆም የተናጠል ውሳኔ በተደረሰው መግባባት መሰረት በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እና በትግራይ ሰራዊት መካከል ላለፉት ስድስት ወራት ወታደራዊ ግጭት ቆሞ እንደቆየ የትግራይ ህዝብ፣ የኢትዮጵያ ህዝቦች እና መላው የዓለም ማህበረሰብ የሚያውቁት ጉዳይ ነው፡፡ 

የተደረሰው ግጭትን የማቆም ውሳኔ ወደ ጦርነት ያደረሰውን ፖለቲካዊ ምክንያት ለመፍታት ወደ የሚያስችል ድርድር ለማሳደግ የአፍሪካ ህብረትና መላው የዓለም ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ  እያካሄዱት ያለውን ያላሳለሰ ጥረቶችን አጠናክሮው እየቀጠሉበት እንዳሉ ግልጽ ሆኖ ለሁሉም ጥረቶቻቸው ያለውን አድናቆት የትግራይ  ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ሳይገልጽ አያልፍም።

የትግራይ መንግስት ለሰላም ያለውን ጽኑ አቋም መሰረት አድርጎ በሰጠው አቅጣጫ የሰላም አማራጭ አማጥጦ እስኪያአጠናቅቅ ድረስ የትግራይ ሰራዊት ለማንኛውም ዓይነት ወታደራዊ ግጭት ምክንያት እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ እንዲህ ሆኖ ሳለ ነሓሴ 09/2014 ዓ/ም በምዕራብ ትግራይ የማይደፈር የብረት መከላከያ ገንብቻለሁ እያለ ያለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በደደቢት አቅጣጫ መደበኛ የመከላከል ተግባሩ እየፈጸመ ባለው የትግራይ ሰራዊት ሃይል ከሰዓት በኃላ ከቀኑ ከ10:00 ሰዓት ጀምሮ ለአንድ ሰዓት የቆየ የከባድ መሳሪያዎች እና በታንኮች የታገዘ ድብደባ አካሂዷል፡፡

የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ከወገን ምንም ዓይነትሸ የአጸፋ ምላሽ እንዳይኖር በማድረግ ይህ በግጭት የማቆም ውሳኔ ላይ የተፈፀመው ጥሰትን በአከባቢው ባለው አዛዥ የተፈጸመ ጉድለት ወይም ከላይ ሆን ተብሎ የተደረገ ስለመሆኑ በትአግስት ሲያጠናው ከቆየ በኃላ ድርጊቱ በበላይ አካል ታውቆ ሆን ተብሎ የተፈጸመ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል። ምዕራብ ትግራይን የትግራይ ላለማድረግ የኢትዮጵያ መሪዎች ይዘውት ያለው የተቀናጀ ወታደራዊና እና ፖለቲካዊ ሴራ በዚህ የግጭት ማቆም ውሳኔ ጥሰት አጠናክረውታል።

ይህ ድርጊታቸው የትግራይ መንግስትም የምዕራብ ትግራይ ነጻ ማድረግ እና የተፈናቀለው ህዝባችን ወደ ቦታው መመለስ ሃይል ብቸኛ አማራጭ እንዲሆን እያደረጉ እንደሆኑ የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ተገንዝቦታል።

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት ይህ እንዲሆን የሚገፋፋው የሆነ ይሁን ግምገማ ትክክለኛ ያለሆነና አሁንም ያለው አማራጭ ሰላምና ለሰላም ቁርጠኛ መሆን ብቻ እንደሆነ እያሳሰብን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦችና የፖለቲካ ሃይሎች ፣ለመላው የኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲሁም የዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ሃገርን ወደ አውዳሚ እና ጠቅላላ ውድቀት የሚዳርግ ጦርነት ዳግም እንዲለኮስ በማድረግ ላይ ብቸኛው ተጠያቂው ቀድሞውንም በትግራይ ህዝብ ላይ የጆኖሳይድ ጦርነት ያወጀ ፣የፈጸመና እየቀጠለበት ያለው የኢትዮጵያ መንግስት መሆኑን ሁሉም እንዲያወቀውና እንዲገነዘበው የትግራይ  ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ያሳውቃል፡፡

ትግራይ ትስዕር !!

የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ 

__

በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,723FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here