ቀሪዎቹ የሀድያ ዞን፣ ሀላባ ዞን፣ ከንባታ ጠንባሮ ዞን፣ ጉራጌ ዞን፣ ስልጤ ዞን እና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ ክልል ይቀጥላሉ ተብሏል

ጀማል ሰይድ
ቦርከና
ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት እያካሄደው ባለው አስቸኳይ ስብሰባ ከቀረበው የውሳኔ ሀሳብ አስቀድሞ በማንነት አስተዳደር እና የወሰን ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኩል በደቡብ ክልል10 ዞኖ ችአቅርበው ስለ ነበረው በተናጠል እንደራጅ ጥያቄ እና ይህንኑ መሰረት በማድረግ ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ዝርዝር ቀርቧል፡፡
ሕዝበ ውሳኔ የሚያካሂዱት ፦
– የወላይታ ዞን፣
– የጋሞ ዞን፣
– የጎፋ ዞን፣
– የደቡብ ኦሞ ዞን፣
– የጌዴኦ ዞን፣
– የኮንሶ ዞን፣ እንዲሁም
– የደራሼ ልዩ ወረዳ፣
– የአማሮ ልዩ ወረዳ፣
– የቡርጂ ልዩ ወረዳ፣
– የአኧ ልዩ ወረዳ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ናቸው።
በዚህም የክልልነት ጥያቄ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ስራዎች ሲከናወኑ ቢቆዩም በተለይም ባለፉት 3 ወራት ዝርዝር የዳሰሳ እና መነሻ ሃሳብ እንዲቀርብ መደረጉ ተመላክቷል፡፡
በመነሻ ሃሳቡ በወጡት እቅዶችውስጥ መሰረታዊ ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት ጥያቄዎቹን የህዝብን ጥቅም በሚያስከበር መልኩ መልስ እንዲያገኙ ማድረግ እና ዞኖች ከተናጠል ይልቅ በክላስተር ቢደራጁ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚኖረው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena