spot_img
Friday, June 14, 2024
Homeዜና በኢትዮጵያ ርዳታ የሚጠብቁ ዜጎች ቁጥር አሻቅቧል ተባለ

 በኢትዮጵያ ርዳታ የሚጠብቁ ዜጎች ቁጥር አሻቅቧል ተባለ

 ርዳታ የሚጠብቁ ዜጎች

ከ19 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ተረጂዎች ይገኛሉ

በአትዩጵያ ውስጥ በሚገኙ 11 ክልልሎች ውስጥ በ5 ማለትም በትግራይ ፣ በአፈር ፤ በአማራ ፣ ኦሮሚያ እና ሶማሊያ ክልልሎች ከ 19 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ተረጂዎች እንደሚገኙ የፌደራል አደጋና ስጋት አመራር ኮሚሽን ገለጿል።

በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ መጠለያዎች ውስጥ ከነቤተሰባቸው ተጠልለው የሚገኙ ወገኖች ከመንግስት ምንም ድጋፍ አላየንም እያሉ ነዉ። አቶ እስክንድር ማሞ ከወለጋ ሆሮጉጉ ወረዳ ከአራት ቤተሰባቸው ጋር ተፈናቅለው በደብረ ብርኃን ከተማ 09 ቀበሌ ቻይና መጠለያ ጣቢያ ይገኛሉ በአሁኑ ሰአት ያሉበን ሁኔታ ለዶቼ ቬሌ እንዲ ሲሉ ገልፀዋል። 

«ግለሰቦች ናቸው እንጂ ድጋፍ የሚያደርጉልን ከመንግስት አካል ምንም አይነት ድጋፍ እየተደረገልን አይደለም ። ተፈናቃዩ  ቁጥር እለት ከእለት እየጨመረ ነው።  በአሁኑ ሰአት በተለያየ አገራት ያሉ ይመለከተናል ያሉ  ናቸው እየደገፉን ያሉት እንጂ እዚ ከመጣን ጀምሮ የመንግስትን እጅ እኔ አይቼ አላውቅም»ብለዋል እርሳቸው በሚገኙበት መጠለያ ከስምንት ሺ በላይ ተፈናቃዩች እንዳሉ የተናገሩት አቶ እስክንድር  «መሬት ላይ ነው የምንተኛው ከፍራሽ አቅም እን ኩዋን ምንም የለም» ብለዋል። 

ሌላው ዶቼ ቬሌ ያናገራቸው በድርቅ ምክንያት ተፈናቅለው  ከመኖሪያቸው እርቀው በኦሮሚያ ከባሌ ዞን ጉራ -ዳሞሌ ወረዳ iየሚገኙ እናለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ  የወረዳው ነዋሪ በወረዳችን ያለዉ ሁኔታ አስቸጋሪ እንደሆነ ተናግረዋል። 

“በወረዳችን ያለው አሁናዊ ሁኔታ አስቸጋሪ ነው፡፡ የእዚህ ወረዳ ነዋሪዎች 80 በመቶ አርብቶ አደር ናቸው፡፡ ይሄው አሁን ሦስተኛ ዓመት አልቆ ወደ አራተኛ ዓመት እየሄድን፤ ዝናብ የሚባል ነገር ባለመኖሩ ህዝባችን ከቦታ ቦታ በመጉላላት እየተፈተነ ይገኛል፡፡ ግጦሽ ፍለጋ ህዝቡ የማይንቀሳቀስበት አቅጣጫ የለም፡፡ የድርቅ ጉዳይ እንዲህ ስፈትነን ይባስ ብሎ ደግሞ በወረዳው ሰባት ቀበሌያት አስቸጋሪ የፀጥታ ሁኔ ውስጥ ነው የከረሙት፡፡ ከሁለት ቀበለያት ለምሳሌ ኦኮልቱ ከተባለች ቀበለ ህብረተሰቡ ሙሉ በሙሉ ተፈናቅለው አጎራባች ወደ ሆነው ደሎመና ወረዳ ሸሽተዋል፡፡ ሃሮ የተባለች ቀበሌም በርካቶች የተፈናቀሉባትና አሁንም የደህንነት ስጋት ውስጥ የሚገኙባት ነው፡፡ ሰው በድርቁም ክፉኛ ነው የተጎዳው፡፡ በዚህ ላይ የናረው የኑሮ ሁኔታ አርብቶ አደሩ የሚሸጠውና የሚገዛው እንዳይመጣጠን አድርጎታል፡፡ ወደ ደሎ መና ከተፈናቀሉት ውጭ ሌላው አከባቢ የሚደረግ እርዳታ ባለመኖሩ ኅብረተሰቡ አስከፊ ችግር ውስጥ ነው የሚገነው” ብለዋል።  በተቃራኒው በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ ምክንያቶች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች ወይንም በየመኖሪያቸው ሆነው ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በመንግስት እና ለጋሽ አካላት ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ያሉት  የፌደራል አደጋና ስጋት አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደበበ እሸቱ፦ «ኢትዩጵያ ውስጥ በተፈጥሮ ይሁን  በሰው ሰራሽ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው የኢትዩጵያ መንግስትም ሆነ ሌሎች አካላት  ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ  ለምሳሌ ትግራይ ላይ 5.2ሚሊየን እርዳታ ፈላጊዎች አሉ ለነዚ ወገኖች ከ ገንዘብ አንስቶ እስቶ እስከ ነዳጅ ድረስ በአየርና በየብስ ትራንስፖርት እየተደረገላቸው ነው እስካሁን ድረስ በጥሬ ገንዘብ 2.9 ቢሊየን  ወደ ትግራይ ሊገባ ችልዋል።

ምግብ በሜትሪክ ቶን ሁለት መቶ አርባ  ሺ ሰባ ሶስት ነው የገባው። በአፈር ክልል ወደ ስድስት መቶ አርባ አምስ ሺ ወገኖች  የምግብ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሀያ ሰባት  ሺ  ዘጠኝ መቶ ስልሳ  ሁለት ሜትሪክ ቶን  በጦርነት ምክንያት ለተፈነቀሉ እየተሰጠ ነው ያለው። አማራ ክልል በአሁኑ ሰአት ወደ 8.7 ሚሊየን ሰዎች ናቸው ድጋፍ እየተደረገላቸው ያሉት ሀምሳ ሰባት  ሺ አራት መቶ አስራ ዘጠኝ ሜትሪክ ቶን ምግብ እንዲቀርብ ተደርግዋል ።  ኦሮሚያ ክልል  3.2 ሚሊየን ሰው ነው ድጋፍ ጠያቂው ለዚህም አንድ ሚሊየን  ስድስት መቶ ሰባ አንድ ሺ ሶስት መቶ አርባ ኩንታል እህል በዋነነት  በምእራብ ባሌ እና በምስራቅ ጉጂ  እንዲሰራጭ ተደርግዋል። ቀጣዩ ሱማሌ ክልል በተፈጥሮ አደጋ 2.2 ሚሊየን ሰዎች ድጋፍ ይፈልጋሉ አንድ ሚሊየንአንድ መቶ ሀምሳ ሶስት ሺ ኩንታል  ድጋፍ እየተሰጠ ነው» ሲሉ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።  

የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዊች በምን ሁኔታ እርዳታው እየደረሰ እንደሆነ  ላቀረብንላቸው ጥያቄ፦ «የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ኢመርጀንሲ ኮርዲኔሽን ሴንተር እና ኮማንድ ፖስት በማቋቋም ነው የምንሰራው  ችግር የለም አይደለም ችግር አለ ችግሩን ለማቃለል ግን  እየሰራን ነው» ብለዋል። ሰሞኑን  የዓለም ምግብ ድርጅት ከዩክሬን ወደብ በመርከብ ያስጫነው 23 ሺህ ሜትሪክ ቶን እህል በኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ሱማሊያ እና የመን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚያከፋፍል ዕርዳታ መሆኑን የድርጅቱ ኃላፊዎች መናገራቸዉ ይታወሳል።

__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here