
ጀማል ሰይድ
ቦርከና
በሀገር አቀፍ የፀጥታ ጉዳይ የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽነሮች የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል
የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ወይይቱ አጠቃላይ ሀገር አቀፍ አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታን ለመገምገም እና ከሰሞኑ በብሔራዊ የደህንነት ም/ቤት የተላለፈው መመሪያ ላይ በመምከር አስፈላጊ ዝግጅት ለማድረግ እንደሆነ ነው ያነሱት፡፡በተጨማሪም መድረኩ የሽብር እንቅስቃሴዎችን ለመከላከልና በቀጣዮቹ ሶስት ወራቶች እቅድ ላይ በትኩረት፤ እንዲሁም በቅንጅት ለመስራት እድል የሚሰጥ እንደሆነም ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።
በመድረኩ የፌደራል እና የክልል የአስተዳደርና የፀጥታ ጉዳይ ኮሚሽነሮች የተገኙ ሲሆን ጠንካራ የደህንነትና የፀጥታ ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችል እንደሆነም ታምኖበታል። በተለይም አሸባሪው ህወሓት ከሰሞኑ የተለያዩ ትንኮሳዎችን ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ በመሆኑ የደህንነት ፀጥታ ግብረ ሀይሉ በጋራ በመስራት እኩይ አላማቸውን ማክሸፍ እንደሚገባም ተነስቷል።
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena