spot_img
Monday, October 2, 2023
Homeዜናበማህበራዊ ሚዲያው በኢትዮጵያ ላይ ትግራይ ጂኖሳይድ በሚል የሳይበር ጦርነት ተከፍቶ እንደነበር ጌት...

በማህበራዊ ሚዲያው በኢትዮጵያ ላይ ትግራይ ጂኖሳይድ በሚል የሳይበር ጦርነት ተከፍቶ እንደነበር ጌት ፋክት ሰራሁት ባለው ጥናት አጋለጠ

advertisement
ትግራይ ጂኖሳይድ _ Tigray

ጀማል ሰይድ
ቦርከና

ህወሃት ከወራት በፊት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከፍቶ በነበረው ጦርነት፣ አላማውን ለማሳካት እንዲያግዘው ሲያደርስ ከነበረው ዘረፋና ጭፍጨፋ ጎንለጎን በሀገር ውስጥና በውጭ በሚገኙ የፕሮፖጋንዳ ተጠሪዎቹ የተለያዩ ዘመቻዎችን ከፍቶ በርካታ የተዛቡና የተሳሳቱ መረጃዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል። ከዚህ ጋር በተገናኘ ፣ማህበራዊ ሚዲያውን በመጠቀም በኢትዮጵያ ላይ ትግራይ ጂኖሳይድ በሚል የሳይበር ጦርነት ተከፍቶ እንደነበር ጌት ፋክት በማህበራዊ ሚዲያው ላይ በካሄደው ጥናት አጋለጠ። 

በማህበራዊ ሚዲያ “በትግራይ ጂኖሳይድ ተፈጽሟል በሚል የተከፈተው የሳይበር ጦርነት ለፕሮጋንዳና ሐሰተኛ መረጃዎችን ለማሰራጨት እንደተጠቀሙት ጌት ፋክት አረጋግጧል። በእነዚህን አካውንቶች ሆን ተብሎ፣ በታቀደና በተቀናጀ መልኩ ያልተረጋገጡ ትረክቶችን ለማሰራጨት ተጠቅመውባቸዋል።

በውሸት ላይ ተመስርተው ግጭቶችን እያባባሱ ሚሊዮኖችን ለሞትና መፈናቀልም ዳርገዋል። ጌት ፋክት በመረጃው እንዳመላከተው የሳይበር ዘመቻ ከህወሓት ወታደራዊ እዝ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ነበረው።ለዚህ ተግባር ማከናወኛ የሚሆን ከ17 በላይ አካውንቶች መከፈታቸውን በጥናቱ አመላክቷል። 

የሰሜን ዕዝ ላይ ከተፈጸመው ጥቃትን ተከትሎ ከ17 በላይ አካውንቶች መከፈታቸውን በጥናቱ ያመላከተው ጌት ፋክት የመጀመሪያው ትግራይ ጂኖሳይድ እንደነበር ገልጸዋል። 

ከ200 በላይ አካውንቶችን በተለያዩ ሀገራት ተከፍተው በመጠቀም የውሸት ትርክቶችን አሰራጭተዋል።ከአንድ ሚሊዮን በላይ አካውንት ተከታዮች ያሏቸው ኢትዮጵያዊያን ያልሆኑ የታንዛኒያና የኬንያ ግለሰቦች የተቀናጀ ጥረት ይህንን ሃሽታግ በትዊተር ገፁ ላይ በማሰራጨት ለአለም አቀፍ የማህበራዊ ሚዲያ ድምጽ መስጠታቸውን ጥናቱ አመላክቷል።

__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,723FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here