
ጀማል ሰይድ
ቦርከና
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የተደረጉ ጥረቶችን በስፋት አብራርተዋል።
በገለጻቸውም በመንግሥት ለሰብአዊ ድጋፍ ሲባል የተደረገውን የተናጥል ተኩስ አቁም ውሳኔ እና ያልተገደብ ሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል ለማስገባት የተደረጉ ጥረቶችን አብራርተዋል።
መንግስት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሰላም አማራጭ ዐብይ ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ሥራ መግባቱንም አስታውሰዋል።
መንግስት የሥስተኛ ወገን ስምምነት በተመድ ጽ/ቤት በመፈረም እንዲሁም ከዓለም ባንክ በተገኝ ድጋፍ የአደጋ ጊዜ እና የማገገሚያ ፕሮጀክት በትግራይ ክልል ተግባራዊ እንዲደረግ መስማማቱን ገልፀዋል።
ይሁን እንጂ የህወሓት ቡድን መንግስት የወሰዳቸውን የሰላም አማራጮች ወደ ጎን በመተው ጦርነት መክፈቱን እና የሚደርሰውን እርዳታም ለጦርነት እያዋለው መሆኑን ገልፀዋል።
ይህ ቡድን በአፍሪካ ሕብረት ማዕቀፍ የተጀመረውን የሰላም ጥረት በመግፋት ወደ ጦርነት መግባቱን ተናግረዋል።
ዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ ይህን ድርጊት በጽኑ እንዲያወግዝ እንዲሁም ቡድኑ ወደ ሰላም አማራጭ እንዲመጣ ግፊት እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
መንግሥት በንጹኃን ዜጎች ላይ ተጨማሪ ጉዳት እና ጥፋት እንዳይደርስ ቅድሚያ በመስጠት አሁንም ለሰላም አራጭ ዝግጁ ነው ያሉት አቶ ደመቀ መኮንን፤ የአገሪቱን ሉዓላዊ የግዛት አንድነት እና የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆኑን ጨምረው መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ