spot_img
Monday, May 29, 2023
Homeአበይት ዜናህወሓት ሕፃናትን ከፊት ለፊት በማሰለፍ የጥይት ቀለብ በማድረግ የጦር ወንጀል እየፈፀመ መሆኑ...

ህወሓት ሕፃናትን ከፊት ለፊት በማሰለፍ የጥይት ቀለብ በማድረግ የጦር ወንጀል እየፈፀመ መሆኑ ተመለከተ

- Advertisement -
ህወሓት ሕፃናትን

ጀማል ሰይድ
ቦርከና

ከመንግስት የቀረቡለትን በርካታ የሰላም አማራጮች ሁሉ ወደጎን በመተው የሽብር ቡድኑ ህወሓት፥ ሲፈጽም የሰነበተውን ትንኮሳ ገፍቶበት የትግራይ ክልል በሚዋሰንባቸው የአማራና አፋር ክልሎች አካባቢዎች ሰፊ ጥቃት መክፈቱን መንግስት ገልጿል።

አሸባሪው ህወሓት የተለመደውን የሰው ማዕበል በመጠቀም የትግራይን ሕፃናት እና ወጣቶች ወደ እሳት እየማገዳቸው ይገኛል። እየወጡ ያሉ የምስል መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት፥ የሽብር ቡድኑ ከ12 ዓመት ጀምሮ እድሜ ያላቸው ሕፃናትን የጦር መሳሪያ በማስያዝ ጥቃት በከፈተባቸው አካባቢዎች ከፊት እያሰለፈ የእሳት  ራት እንዲሆኑ እያሰገደዳቸው ነው።ያረጀ የጦርነት ስልት የሆነውን የሰው ማዕበል በመጠቀም ሕፃናቱን ከፊት አሰልፎ የጥይት ቀለብ እያደረጋቸው እንደሚገኝም ተገልጿል።

የኢፌዴሪ መንግስት፥ አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት እንደሚገደድም  አሳስቧል።

በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሽብር ቡድኑ ህወሓት ህፃናትን ለጦርነት በማሰለፍ የጦር ወንጀል እየፈፀመ መሆኑን  አንስተዋል።

ይህን የሽብር ቡድኑን የጦር ወንጀል ድርጊት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለምን ዝም አለ? ሲሉም እየጠየቁ ይገኛሉ።

__

በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,864FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here