ጀማል ሰይድ
ቦርከና
ወራሪው የህወሃት ቡድን ትናንት ከሰአት በሗላ የቆቦ ከተማን ከተቆጣጠረ በሗላ ፣ ዛሬ ረፋድ ላይ ወደ ወልዲያ ከተማ
እየተጠጋ መሆኑን የወልዲያ ነዋሪዎች ጠቁመዋል። የቦርከና ዘጋቢ ፣ የከተማዋን ነዋሪዎች በስልክ አናግሮ እንዳገኘው
መረጃ የህወሃት ጦር ከወልዲያ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘውን የሮቢት ከተማን ተቆጣጥሯል።
የወልዲያ ከተማም ባለመረጋጋት ውጥ መሆኗ ተነግሯል። በሌላ በኩል፣ የወልድያ ከተማ አስተዳደር የከተማው ሕዝብ
ተረጋግቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ እና ለጥምሩ ጦር ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ዛሬ ጥሪ አቅርቧል።” የሀገር
መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚኒሻው እየተፋለሙ ነው ” ያለው የወልድያ ከተማ ” የአካባቢው
ማኅበረሰብ አካባቢውን ተረጋግቶ በመጠቅ ለጥምር ጦሩ የተለመደ ሁለተናዊ ደጀንነቱን አጠናክሮ ይቀጥል ” ሲል
ጥሪውን አቅርቧል። ከተማ አስተዳደሩ ” የጦርነቱ የፍልሚያ ቦታ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ከራያ ሚዳ አልዘለለም ” ያለ
ሲሆን ሾልኮ ለማለፍና በወሬ ለመፍታት የተደረገው ስልትም እስካሁን አልሰመረም ብሏል።
የከተማ አስተዳደሩ ዛሬ መልዕክቱን ያሰራጨው የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ በአካላዊ እንቅስቅሴ ጭምር በማጣራት
መሆኑን አመልክቷል።
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ