spot_img
Wednesday, November 29, 2023
Homeአበይት ዜናመከላከያ ሰራዊት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተወካዮች ማብራሪያ ሰጠ

መከላከያ ሰራዊት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተወካዮች ማብራሪያ ሰጠ

advertisement
መከላከያ ሰራዊት

ጀማል ሰይድ
ቦርከና

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የውጭ ግንኙነት ክፍል በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በኢትዮጵያ ላሉ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተወካዮችና የሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች እንዲሁም ለሀገራት ወታደራዊ አመራሮች ሰጥቷል።

የመከላከያ የውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር ጀነራል ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ ÷የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያ ላይ የሚቃጡ ማናቸውም አይነት የጥፋት ሙከራዎችን በአስተማማኝ መልኩ መቀልበስ እና መመከት የሚያስችለው ቁመና ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የህወሓት የሽብር ቡድን የሰላም አማራጮችን በመግፋት የኢትዮጵያ ጦር ላይ ዳግም ጥቃት መክፈቱን ይህም የሽብር ቡድኑ ለሰላም ፍላጎት እንደሌለው የሚያሳይ እንደሆነ ሜጀር ጀነራል ተሾመ ለወታደራዊ አመራሮቹ አብራርተዋል። ህወሓት የጀመረው ጦርነት በቴክኖሎጂ መረጋገጥ የሚችል እንደሆነ የሽብር ቡድኑ በወትወት ራማ ቢሶበር እና ዞብል እንዲሁም በአፋር ድንበር ጦርነት መክፈቱን ገልፀዋል።

መከላከያ ሰራዊት የሀገሩን ዳር ድንበር የህዝቡን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነት እንዳለበት ያነሱት ሜጀር ጀነራል ተሾመ ÷ መከላከያ እንደ አንድ ቁልፍ የብሄራዊ ማስፈፀምያ አቅም የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም በተለይም የህልውና ጥቅም የማስከበር ተቋማዊ ግዴታ አለበት ብለዋል። ስለሆነም፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን እውነት ለሰላም የተከፈለውንም ዋጋ መረዳት እና ከኢትዮጵያ ጎን ሊቆም እንደሚገባው ማብራራታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡። በሽብር ቡድኑ በሚፈበረኩ የተዛቡ መረጃዎችም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊሳሳት እንደማይገባው ጥቃቱ እንዴት እንደተጀመረ በቀላሉ መለየት እንደሚቻል አንስተዋል። 

የኢትዮጵያ ሰራዊትም በሽብር ቡድኑ የተቃጣበትን ጥቃት በአግባቡ እየመከተ እንደሆነና ለዚህ ደግሞ የማንም ፍቃድ እንደማያስፈልገው ነው ያስገነዘቡት።

__

በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here