spot_img
Sunday, October 1, 2023
Homeአበይት ዜናየመንግስት ሃይሎች በቆቦ፡ ሮቢትና ጎብዬ  አካባቢዎች ከፍተኛ ዉጊያ እያደረጉ ነው ተባለ

የመንግስት ሃይሎች በቆቦ፡ ሮቢትና ጎብዬ  አካባቢዎች ከፍተኛ ዉጊያ እያደረጉ ነው ተባለ

advertisement
በቆቦ፡ ሮቢትና ጎብዬ

ጀማል ሰይድ
ቦርከና

የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ እንዲገባ በማድረግ በተናጠል ያደረገውን ተኩስ አቁም ተጥሶ ከአምስት ወራት በኋላ በአሸባሪው ህውሃት ተንኳሽነት ጦርነቱ ተጀምሯል፡፡ ባለፈው በተደረገው ጦርነት የወሎ ህዝብ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጉ የሚታወስ ነው፡፡ አሁን የተጀመረው ጦርነትም ከደረሰበት ጉዳት በፅኑ ያላገገመውን የወሎ ህዝብ ለሌላ ስጋትና እንግልት ዳርጎታል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪው የህውሃት ቡድን በሰው ማእበል የተሞላ ህዝባዊ ጦርነት እያካሄደ መሆኑን በመግለፅ በከተማ ውስት ጦርነት ላለማድረግ እና ህዝቡን አደጋ ውስጥ ላለመጣል ከሰሜን ወሎዋ ቆቦ ከተማ ወደ ኋላ ማፈግፈጉን በይፋ ገልፆ ነበር፡፡ ይህ ከተሰማ በኋላ በባለፈው ጦርነት ከፍተኛ ጉዳትና እንግልት የደረሰባቸው የወልድያ እና መርሳ እና አካባቢው ነዋሪዎች ለመፈናቀል ተገደዋል፡፡

ለወራት በርካት የሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቃዮችን ተቀብላ ያስተናገደችው ደሴ ከተማ ዛሬም በተፈናቃዮች ተሞልታለች፡፡ የቆቦ ከተማ በህውሃት አሸባሪ ቡድን እጅ መውደቋ ትልቅ ስጋት እና ድንጋቴን በማህበረሰቡ ዘንድ የፈጠረ ሲሆን አሁንም የፌደራል መንግስት ጥምር ጦር የህወሃትን ተዋጊዎች ለመደምሰስ ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ይፋ ያላደረጋቸው ፡ ጥምር ጦሩ ወደፊት በመገስገስ ቆቦ እና ዋጃ ከተማን በቁጥጥር ስር በማድረግ ወደ አላማጣ እየተጓዘ ነው  የሚሉ መረጃዎች ጧት አካባቢ የወጡ ቢሆንም፤ በተቃራኒው ከቆቦና አካቢው ነዋሪዎች ደውለን አረጋግጠናል የሚሉ አካላት ህወሃት አሁንም የቆቦ ከተማን ስለመያዙ ይናገራሉ፡፡ በራያ ግንባር ከሰአት በኋላም በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ሃይል እና በመከላከያ ሰራዊት በሚመራው ጥምር ጦር መካከል በሮቢትና ጎብዬ አቅራቢያ ከፍተኛ ጦርነት እየተደረገ መሆኑ እየተሰማ ነው፡፡

የአሸባሪው ትግራይ ወራሪ ሃይል በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ሀይል፣ በፋኖ እና ሚሊሻ ከፍተና ጥቃት እየደረሰበት እንደሆነ ማሳያው በአሸናፊነት መንፈስ ከበሮ ሲደልቁ የነበሩት የቡድኑ አፈ ቀላጤዎች ስለ ሰላም መዘመር መጀመራቸው ነው የሚሉ ወገኖችም አሉ፡፡ በትናንትናው እለት አልጀዚራ፤ ወልዲያ ከተማ በሽብር ቡድኑ ቁጥጥር ስር ውላለች በማለት ፍፁም ከእውነት የራቀ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ ይህም የውጭ ሚዲያዎች በአሸባሪው ቡድን አባላት የሚዘወሩ ስለመሆናቸው ማሳያ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡
__

በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,718FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here