spot_img
Thursday, November 30, 2023
Homeዜናየሕወሐት ዕብሪት ለሰላም የተዘረጉ እጆች እንዲታጠፉ እያስገደደ ነው ሲል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት...

የሕወሐት ዕብሪት ለሰላም የተዘረጉ እጆች እንዲታጠፉ እያስገደደ ነው ሲል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ

advertisement

የሕወሐት ዕብሪት ለሰላም የተዘረጉ እጆች እንዲታጠፉ እያስገደደ ነው ሲል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ያወጣው ወቅታዊ መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

“የሕወሐት ዕብሪት ለሰላም የተዘረጉ እጆች እንዲታጠፉ እያስገደደ ነው! 

መንግሥት ለሰላም አማራጭ ዕድል ለመስጠት ሲል የሕዝብ ማዕበል አስነሥቶ ሕጻናትን፣ ወጣቶችንና አረጋውያንን ለመማገድ የመጣውን የሕወሐት ታጣቂ፣ በምሥራቅ አማራ በኩል በጀግንነት ሲከላከል ቆይቷል።

ሕወሐት በምሥራቅ አማራ በኩል በቆቦና አካባቢው የከፈተው ወረራ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና በደጀኑ ሕዝብ ጠንካራ የመከላከል ብቃት የተነሣ ባሰበው ልክ አልሄደለትም። 

በዚህም ምክንያት ለሰላም የተሰጠውን ሁለንተናዊ አማራጭ አሽቀንጥሮ ጥሎ ወረራውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች እያስፋፋ ይገኛል።

ያለ ጦርነት መኖር የማይችለው ሕወሐት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አካባቢ ወረራ ከፍቷል። ይሄንን የሕወሐት ወረራ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት በተሟላ ዝግጅትና በጽኑ ቁመና እየተከላከለ ይገኛል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ አቅጣጫዎች የተከፈቱበትን ጥቃቶች በጽናት እየተከላከለ፣ አሁንም ለሰላም አማራጮች የዘረጋቸውን እጆች ዛሬም ድረስ አላጠፈም።

ለሰላም የተዘረጋው እጅ በሕወሐት ዕብሪታዊ ወረራ ምክንያት እንዳይታጠፍ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚቻለውን እንዲያደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት አሁንም ያሳስባል። ወገናችን የሆነው የትግራይ ሕዝብም ይሄንን የዕብሪት ወረራ በማውገዝ ሕወሐት ከሚያስከትልበት መከራ ራሱን ነጻ እንዲያወጣ ጥሪ እናቀርባለን።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት “

__

በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here