spot_img
Sunday, July 21, 2024
Homeነፃ አስተያየትየተቋረጠው የሰላም ንግግር እና የመሰረታዊ አገልገሎቶች ጉዳይ በትግራይ

የተቋረጠው የሰላም ንግግር እና የመሰረታዊ አገልገሎቶች ጉዳይ በትግራይ

ቃለወንጌል ምናለ 

ህወሃት የሰላም አማራጩን በመተው ወደ ሃይል አርምጀ ተመልሷል፤ በአማራ እና አፋር ክልል አጎራቦች በሚገኙ አካባቢዎችም ውጊያ ከፍቷል፡፡ ከሰላም ሂደቱ ለመውጣት እና ለሶስተኛ ጊዜ የከፈተው ጦርነት ፍታሃዊ (Just War) መሆኑን ለማሰማን በተደጋጋሚ የሚያነሳው የመሰረታዊ አገልገሎቶችን ጉዳይ ነው፡፡ ህወሃት መሰረታዊ አገልግሎቶች ለምሳሌ ባንኪንክ፤ ቴሎኮም፤ መብራት ወዘተ ያለቅደም ሁኔታ ሳይጀመሩ ወደ ወይይት እንዳማይገባ ግልጽ አድረጓል፡፡ እጃችን የፊጥኝ ታስሮ፤ እየተራብን እና እየተጠማን ወደ ንግግር እንገባም የሚለው ከህወሃት በኩል የምንሰማው ድምጽ ነው፡፡ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጉዳይ ተጀምሮ ለነበረው የሰላም ጥረት ዋነኛ ምክኒያት ተደርጎ ይቀርባል፡፡

ነገር ግን የህወሃት አገልግሎት ሳይጀምር ንግግር አልጀምርም ክርክር ፓለቲካዊ ማደናገሪያ ከመሆኑም በላይ ቡድኑ የሰላም ሂደቱን ለፍትሃዊ ጦርነት ማጀቢያ ከንቱ የፕሮፓጋንዳ ግብአትነት ይጠቀምበት እንደነበር ማሳያ ነው፡፡ አንኳን ራሱን እንደ ሉዓላዊ መንግስት ከሚቆጥር ሀይል ይቅርና የትኛውም ግለሰባዊም ሆነ ማህበራዊ አግልግሎት የሚጀመረው በንግግር እና ስምምነት ነው፡፡  

የአገልግሎቶች መጀመር ጉዳይ ጠቅላላ የሁለቱን የመንግስት እርከኖች  ግንኙነት እና የሰላም ሂደቱን የሚመለከት የሰላም ንግግሩ  አካል ነው፡፡ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ህወሃት የፊደራል መንግስቱን እና ህጋዊ ስርዓት ባለመቀበል፤ ይልቁንም በሃይል አመራጭ ለመገርሰስ ለውጡንም ለመቀልበስ ሲተጋ የቆየ፤ አሁንም አየተጋ ያለ ሃይል ነው፡፡ ከሁሉም የፌደራል መንግስት ህጎች በተፀራሪ የትግራይ መንግስት ብሎ ባደራጀው መዋቅር ራሱን እንደ አንድ ሉዓላዊ ሰራዓት-መንገስት የሚቆጥር የራሱ መከለከያ ሃይል ያደረጀ፤ የውጭ ግንኘነት ቢሮ ሰይሞም ይነሰም ይብዘም አለመአቀፍ ግንኘነት እያደረግ የሚገኝ ሃይል ነው፡፡ 

በእንዲህ ያለ ሁኔታ አገልግሎት እንዴት ነው የሚሰጠው፤ የአገልግሎት ክፍያውስ  እንዴት ይሰበሰባል፤ ለሚመለከታቸው የፊደራል አካላት  ሪፓርት እንዴት ይቀርባል፤ የፊደራል ህግች ይማላሉ ወይንስ እንደት ይሆናሉ የሚለው ንግግር እና ስምምነት ያሚያስፈልገው ጉደይ ነው፡፡ በተጨማሪም አግልግሎት ለመክፈት እና ለመስጠት፤ በትንሹ አስቻይ የሆነ መረጋጋት እንዲኖር ያስፈልጋል፡፡ ሁለቱም ሃይሎች ከጠብ አጫሪነት እና እርስ በእርስ ከመፈላለግ   መታቀብ አለባቸው፡፡ ይህም ሁኔታ የሚፈጠረው በሰላም ንግግር ሂደት በሚመጣ ስምምነት ነው፡፡

መሰረታዊ አግልግሎቶች ከህይወት አድን ድጋፎች ጋር መምታት የለባቸውም፡፡  ህይወት አድን ሰብአዊ ድጋፎች እና አግልግሎቶች ምንም ቅደም ሁኔታ የማይቀርብባቸው ናቸው፡፡ አግልግሎት ማግኘት የዜግነት መብት መሆኑ የታወቀ ቢሆንም ይህን ለማግኘት  የሚጠየቀውን ግዴት ደግሞ ሟሟላት ያስፈልጋል፡፡ አገልግሎቶች ያለምንም ሁኔታ፤ ያለምንም ሰጥቶ መቀበል  መርህ እና አካሄድ የሚቀርቡ አይደሉም፡፡

በተጨማሪም በትግራይ የአግልግሎቶች መመለስ ጉዳይ የመሰረት ልማቶችን ለመጠገን እና ወደ ስራ ለመመለስ ለሚሰማሩ ባላሙያወች የሚሰጥ የድህነት ማረጋገጫ  ብቻ ተደርጎ  አንሶ እና ኮስሶ መቅረብ የለበትም፡፡ አግልገሎቶችን  ለመክፈት እና ሳይቆረረጡ ለማቅረብ የህዋሃት ቡድን፤ የጦርነት አማራጭን በመተው ግጭቱን በሰላማዊ  መንገድ ለመፈታት ዝግጁነቱን መግለጽ እና ይሀንንም በተግባር ማሳየት ያስፈልገዋል፡፡ በተጫማሪም በፌደራል ስራዓቱ ውስጥ ያሉ የህግ ማእቀፎችን ለመተግበር እና ለማስተግበር፤ አፈፃፀማቸውንም ለመከታተል እና ለሚመለከታቸው አካላት ሪፓርት ለማድርግ ዝግጁነቱን መግለጽ አለበት፡፡ ህወሃት  መንግስትና ህዝብን እየወጋ፤ በተግባር ነፃ መንግስት አውጆ ያለምንም ቅደመ ሁነታ አግለጎሎት እንዲቀርብለት መጠየቅ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሃሳብ ነው፡፡

እስከአሁን አለም አቀፍ እውቅና  ያላገኘቸው ጉረቤታችን ሰማሊላንድ ከሶማሊያ ምንም አይነት የበጀት ድጎማ፤የማህበራዊ አግለግሎት አትጠይቅም፡፡ የራሷን መንግስት ሰይማ ነፃነቷን ካወጀች አስርት አመታት ተቆጠረዋል፡፡ በሌላ በኩል የፊደራል መንግስቱን የበላይነት እና የፌዴሬሽኑን ሀጋዊ ስራዓት ተቀብላ ራሳን በራሳ የምታስተዳድረው ራስ ገዟ ፑንትላንድ ደግሞ በጀት እና ሌሎች አገልግለቶችን ከሶማሊያ ታገኛለች፡፡ የትግራይ መንግስት ሌላውን የኢትየጲያ አካባቢዎች አየወረረ፤ አያፈናቀለ፤ የፊደራል መንግስቱን ለማፈረስ እና በሃይል ለመቀየር አየዛተ፤ በተጫባች እና በግላጭ ነፃ ሃገር-መንግስት  አወጆ፤ ከኢትዮጲያ የመገንጠል አጀንዳ እያረመደ፤ ቀለብ ይሰፈርልኝ ማለቱ አይናቸሁን ተጨፉኑ እና ላሞኞችሁ አይነት ነገር ነው፡፡

በአጭሩ መሰራተዊ አግለግሎቶች የአደጋ ጊዜ እና ሰብአዊ ድጋፎች አይደሉም፡፡ የመጀመሪዎቹ የልማት (Welfare Needs) መብቶች ጋር የሚገናኙ ሲሆን ኃለኞች ደግሞ በህይወት ለመቆየት (Survival Needs) የሚያስፍልጉ ናችው፡፡ ግጭት እና ፈጥጫ ባላበት ሁኔታም በተሟላ መንገድ ሊቀርቡ የሚችሉ አይደሉም፡፡ የአግልግሎቶች ጉዳይ ግጭቱን እና የሰላም ንግግሩን የሚመለከት ነው፡፡ አገልግሎት ማግኘት መብት ነው፡፡ ነገር ግን ግዴታም የሚጥል፤ የአጭር እና የረጀም ጊዜ  ስምምነት እና ውለታ የሚያስፈልገው ነገር ነው፡፡ በትግራይ የተቋረጠውን ሁሉንም አገልግሎቶች ዳግመኛ ለመመለስ ግጭቱ በዘላቂነት የሚቆምበት፤ህጋዊ ስራዓት ወደ ቦታው ተመልሶ የተረጋጋ ሁኔታ  የሚፈጠርበትን መንገድ ማሰብ እና መነጋገር ያስፍልጋል፡፡ ያህ ደግሞ በቀጥታ የሰላም ንግግሩን የሚመለከት ነገር ነው፡፡ ስለሆነም  መፍትሄው የሰላም ንግግሩ በአፈጣኝ እንዲጀመር ማድረግ፤ ሁሉንም ለዪነቶች በአብሮ መኖር  እና በሰጥቶ መቀበል መርሃ ድረጀ በደረጀ ለመፍታት መሞከር ነው፡፡ ሲጠበቅ የነበረው እና አሁን የተቋረጠው የሰላም ንግግር ዳግም በሚጀመርበት ጊዜ የመጀመሪያው ምእርፍ እንዲያሳካው ከሚጠበቁ ጉዳዪች እንዱ እና ዋነኛ ነገርም ይሀ ነው – የሃይል እና የጦርነት አማራጭን ዝግ ማድረግ፤ ሁሉም ልዪነቶች በሰላማዊ አማራጭ ለመፍታት መሰማማት እና አገልግሎቶቸን መክፍት፡፡

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena 

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

1 COMMENT

  1. The TPLF is demanding the resumption of the provision of basic services to survive and rebuild its armed forces. It is not concerned about the well being of its cannon fodder (ordinary Tigrayans). It is using humanitarian aid for its invasion and will do the same thing with services to destabilize the country. Thus, the TPLF should be denied any service until it surrenders and faces justice. Enough is enough specially for the residents of the Afar and Amhara regions.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here