spot_img
Sunday, May 19, 2024
Homeአበይት ዜናበአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ላይ ታጣቂዎች ጥቃት መፈጸማቸው ተገለጸ

በአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ላይ ታጣቂዎች ጥቃት መፈጸማቸው ተገለጸ

ጀማል ሰይድ
ቦርከና

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ለተከሰተው የሰላም እጦት ዋነኛ ተዋናዮች በፌደራሉ መ፣ንግስቱ በሽብርተኝነት የተፈረጁት ሀወሃና የኦነግ ሸኔ ቡድኖች ናቸው፡፡

የህወሃት ቡድን ለ3ኛ ጊዜ በከፈተው ወረራም ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት በከፍ ጦርነት ውስጥ ትገኛለች፡፡ ከህወሃት ባሻገር ኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ንጹሃን የአማራ ብሄር ተወላጆችን በተለያዬ ጊዜ በግፍ በሚሰራው አረመኔያዊ ተግባር በርካቶችን ለእልቂት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ንጹኀን ዜጎችን ለመፈናቀል አብቅቷል፡፡ አሸባሪ ቡድኑ ንጹሃንን ሲጨፈጭፍ በአሁናዊ የሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ የአድራጊ ፈጣሪ ሚና ያለው የኦሮሚያ ብልጽግና የጸጥታ ሃይሎን ድጋፍ እያገኘ ነው ሲሉ ብዙዎች ይከሳሉ፡፡ የኦነግ ሸኔ ቡድን ከንጹሃን ጭፍጨፋ እኩይ ተግባሩ ባሻገር ባንኮችንና የተለያዩ የመንግስት ተቋማትን መዝረፍ ሁነኛ መለያው ሆኗል፡፡

ባለፈው ሳምንትም በአርጆ ኦዴሳ ስኳር ፋብሪካ ላይ የቡድኑ ታጣቂዎች ጥቃት መፈጸማቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ በዘገባው አስነብቧል፡፡

ታጣቂዎቹ ማሰኞ ነሀሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረሱት ጥቃት የፋሪካውን ተሸከርካሪዎች እንዳቃጠሉና ጥቃቱን ከፈጸሙ በኋላ ከአካባቢው መውጣታቸውን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ማስታወቁን ነው ጋዜጣው ያስነበበው፡፡ የግሩፑን የሕዝብ ግንኙነት ተሳትፎ ክፍል ዋና ሃላፊ አቶ ረታ ዘለቀን ጠቅሶ ሪፖርተር እንደዘገበው ታጣቂዎቹ በስኳር ፋብሪካው ውስጥ በሚገኙ ተሸከርካሪዎች እና የሸንኮራ ማሳ ማሽነሪዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ታጣቂዎቹ በፋብሪካው ላይ ጉዳን ያደረሱት ህወሃት በከፈተው ጦርነት ሳቢያ በአካባቢው የተፈጠረውን ክፍተት ተጠቅመው

መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

እንደ ዋና ኃላፊው ገለጻ፣ በፋብሪካው ላይ የደረሰው ጥቃት በሰሜን ኢትዮጵያ በድጋሚ ካገረሸው ጦርነት ጋር የሚያያዝ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ በጦርነቱ ምክንያት አካባቢው ላይ የተፈጠረውን ክፍተት ተጠቅመዋል፡፡

‹‹ኦነግ ሸኔ ተብሎ በዚያ ደረጃ የሚጠቀስ አይደለም፣ ግርግር ተጠቅመው ታጣቂዎች ሊገቡ ይችላሉ፣ ወለጋ አካባቢ ስለሆነ ግን እንደዚያ [ኦነግ] ተብሎ ነው የሚታወቀው፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

በክረምት ወራት ላይ ሁሉም የስኳር ፋብሪካዎች የስኳር ምርት አቁመው ሙሉ ማሽነሪ ጥገና ላይ እንደሚሰማሩ የገለጹ አቶ ረታ፣ ጥቃቱ ሲደርስ የፋብሪካው ሠራተኞች በማሽነሪ ጥገና ላይ እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡ ፋበሪካውን ወደ የሚያስተዳድረው የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሪፖርት የደረሰው ረዕቡ ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. መሆኑን ጠቅሰው፣ ጥቃቱ የደረሰበትን ሰዓት ለመናገር እንደሚቸገሩ ተናግረዋል፡፡ ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ ለምን ያህል ጊዜ በፋብሪካው ቅጥር ጊቢ ውስጥ እንደቆዩ ያልተገለጸ ሲሆን፣ የፋብሪካው ሠራተኞች ግን ወደ ፋብሪካው ተመልሰው የጥገና ሥራውን እያከናወኑ መሆናቸውን ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

አርጆ ዲዴሳ 16 ሺሕ ሔክታር የእርሻ መሬት የያዘ ሲሆን፣ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ቡኖ፣ በደሌና የጅማ ዞኖች መካከል የዲዴሳ ወንዝን ተከትሎ በዲዴሳ ሸለቆ ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ በ395 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ፋብሪካው በ2001 ዓ.ም. አልሀበሽ በተባለ የፓኪስታን የግል ኩባንያ የተቋቋመ ሲሆን፣ ኩባንያው ከሦስት ዓመት በኋላ የግንባታ ሥራው ሳይጠናቀቅ ለቀድሞው የስኳር ኮርፖሬሽን ተሸጧል፡፡

በ2007 ዓ.ም. ሥራ የጀመረው አርጆ ዲዴሳ፣ በዓመት 100 ሺሕ ቶን ስኳርና 39 ሺሕ ሞላሰስ የማምረት አቅም አለው፡፡ ፋብሪካው ካለው ለእርሻ የሚሆን 16 ሺሕ ሔክታር መሬት ውስጥ አሁን የሸንኮራ አገዳ እያመረተ ያለው 3‚700 ሔክታር በሚሆነው መሬት ላይ ነው፡፡

__

በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here