
ቦርከና
የሩሲያ የመገበያያ ገንዘብ ሩብል በግብጽ ተቀባይነት ካላቸው የመገበያያ ገንዘቦች ተርታ ሊመደብ አንደሆነ ተሰምቷል::
“አር ቲ” የሩሲያን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን (ሪያ ኖቮስቲን) ጠቅሶ እንደዘገበው የግብጽ ውሳኔ ከሩሲያ የሚገኝ የቱሪዝም ገቢን ከማሳደግ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ነው የተጠቆመው::
በፈረንጆቹ የክረምት እና መኽር ወራት በግብጽ ከሚደረጉ የሆቴል ክፍል አና የጉዞ አገልግሎት ሺያጮች እስከ አርባ ስድስት በመቶ የሚሆነው የሚገኘው ከሩሲያ ቱሪስቶች እንደሆነም ተጠቁሞኣል::
በዮክሬን እየተደረገ ያለውን ጦርነት ተከትሎ ሩሲያ ዘርፈ ብዙ የሆነ ማዕቀብ የተጣለባት ሲሆን ፤ ሩሲያም በበኩሏ ማዕቀቡ የሚፈጠረውን የምንዛሬ ግሽበት ለመቋቋም ሩብልን ከወርቅ ጋር በማያያዝ ምንዛሬዋን ማጠናከሯ ይታወቃል::
ግብጽ በሩሲያ ቱሪስቶች ተወዳጂ ከሚባሉት መዳረሻዎች አንዷ ናት::
እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2015 የሩሲያ የመንገደኞች አውሮፕላን በግብጽ በሳይናይ በረሃ ጋይቶ 244 ሰዎች ማለቃቸው ይታወሳል ::
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ