spot_img
Wednesday, May 29, 2024
Homeዜናህወሓት ልጂ አዋቂ እና ሽማግሌ የማይለይ አዲስ ወታደራዊ ክተት አውጆአል

ህወሓት ልጂ አዋቂ እና ሽማግሌ የማይለይ አዲስ ወታደራዊ ክተት አውጆአል

ቦርከና

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ዛሬ “የትግራይ መንግስት ማዕከላዊ ኮማንድ” በሚል ስያሜ ባሰራጨው ጥሪ ልጂ አዋቂ እና ጭማግሌ ሳይባል ሁሉም ትግራይዋይ በሙሉ አቅሙ መክተት አና “ጠላቶቻችን” ሲል የጠራቸውን የኢትዮጵያ ጥምር ጦር እና የኤርትራ ጦር በብዙ ግንባር ክፈተውብናል ያለውን ወረራ ለመቀልበስ ሁለ ገብ ዝግጂት እንዲደረግ አዟል::

ራሱን “የትግራይ መንግስት” እያለ የሚጠራው እና የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የፈረጀው ቡድን በመግለጫው ላይ ተከፍቶብኛል ያለው ወረራ “ትግራዋይን ከምድረገጽ ለማጥፋት” እንደሆነ ገልጾ የጠላቶቻንን ህልም ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማምከን እያንዳንዱ ትግራዋይ በጦርነቱ በሙሉ አቅሙ መሳተፍ አለበት ብሎኣል ::

በሌላ በኩል ደሞ በኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ህዝብ ባቀረበው ጥሪ የጦርነቱ ተባባሪ እንዳይሆኑ ጠይቋል::

ለኤርትራኖች ባስተላለፈው መልዕክት የኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት የኤርትራን ህልውና “ከማይቀበሉ ኃይሎች” ጋር ትብብር ፈጥሮ የከፈተብንን ጦርነት እንዳይደግፉ ጥሪውን አስተላልፏል:: የኢትዮጵያን ህልውና የማይቀበሉ ያላቸውን ኃይሎች በስም ባይጠቅስም ጦርነት ከፍተውብኛል ያላቸው የኢትዮጵያ ሰራዊት ፋኖ እና የ ኤርትራ ሰራዊት መሆናቸውን በመግለጫው ጠቁሟል::

የኢትዮጵያንም ህዝብ በተመሳሳይ በተለይም ደሞ የአፋር አና የአማራን ህዝብ ልጆቹን ወደ ጦርነት እየላከ “የሳት ራት” እንዳያደርጋቸው ጥሪ አቅርቧል ::

ይህ ዜና አስከወጣበት ጊዜ ድረስ ድረስ ከህወሓት በስተቀር በሁሉም ግንባር ተከፍቷል ስለትባለው ውጊያ የሚያረጋግጥ ወይንም የሚያስተባብል ዘገባ አልወጣም::

ለሰላም ንግግር በመንግስት እና በዓል አቀፍ ደረጃ ጥረት እየተደረገ በነበረበት ሰዐት በነሃሴ አጋማሽ ላይ የህወሓት ቡድን የሶስተኛ ዙር ጦርነት በመክፈት ቆቦን መቆጣጠሩ እና በምዕራብም በኩል በሁመራ ጦርነት መክፈቱ ይታወሳል::

እስካሁን የ አዳርቃይ ከተማ በምዕራብ ግንባር ከህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ነጻ መሆኑ ከመሰማቱ በስተቀር መንግስት ስለ ጦርነቱ ዝርዝር መግለጫ ከመስጠት ተቆጥቧል::

ህወሓት ዛሬ ያወጣው የክተት ኣዋጂ ከታች በተያያዘው የድምጽ ፋይል ማዳመጥ ይቻላል::

(የድምጽ ፋይሉ የተገኘው ከትግራይ ቴሌቭዥን ነው )

__

በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here