
ቦርከና
ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ማክሰኞ እለት ዘግባዋል፡፡
በባህላዊ እና ዘመናዊ ሙዚቃዎቹ ታዋቂነትን ካተረፉ ድምጻውያን ተርታ የሚመደበው ማንዲጎ በህክምና ሲረዳ የቆየ ከመሆኑ ውጭ ለህልፈተ ህይወት ስላደረሰው ህመም አልተገለጸም፡፡
ገና በልጂነት እዲሜው ተወልዶ ባደገበት ጎንደር እካባቢ ሙዚቃ እንደጀመረ የሚነገርለት አቀንቃኝ አዲስ እበባ መጥት የሙዚቃ ባንድ ውስጥ የተቀጠረው በአስር ዓመት እድሜው እንደነበረ ታቋል፡፡
እድናቆትን ካተረፉልት የሙዚቃ ስራዎቹም ባሻገር ማዲንጎ የህወሃት ሰራዊት ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ከከፈተ በኋላ ግምባር ድረስ በመሄድ ሰራዊቱን በስራዎቹ በማበረታት ከሙያ አጋሮቹ ጋር አስተዋጾ እድርጓል፡፡ አዲስ ምልምል ሰልጣኞችን በማሰልጠኛ ተቋም በመገኘት አበረታቷል ፤ የዜግነት ድርሻውን ተወቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በድምጻዊው ህልተፈህይወት የተሰማቸውን ሃዘን በመግልጽ ያበረተውንም አስተዋጾ ዘክረዋል፡፡
“አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ በማረፉ የተሰማኝ ኀዘን ከባድ ነው። ለሀገሩ በአጭር እድሜው ብዙ የሠራ ከያኒ ነው። ሀገር በተደፈረች ጊዜ ሕመሙን እየቻለ ግንባር ተገኝቶ ሠራዊቱን አጀግኗል። ሠልጣኞችን አበርትቷል። ነፍሱ በሰላም ትረፍ” በማለት በማህበራዊ ድረ ገጻቸው ጽፈዋል፡፡
ስለ አርቲስቱ የቀብር ቀን እና ቦታ ይሄ ዜና በተጻፈበት ሰዓት አልተገለጸም::
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ