
ከአልማዝ አሸናፊ
Wyoming, USA
IMZZASSEFA5@GMAIL.COM
በልጅነት ወጥቼ በሰባዎች እድሜ የተወለድኩባትን ኢትዮጵያ ተመልሼ ሳያት በአምስት ሳምንታት ቆይታየተመለከትኩትን ላጋራ እወዳለሁ:: በቅድሚያ ግልፅ ማደርገው ስለማንነቴና ስለማንነት ያለኝን የማያወላውል አቋሜን ነው:: በሰፊው ትውልደ ኢትዮጵያ ሆኜ በጠባቡ የኦሮሞና የወላይታ ብሔረሰቦች ትውልድ ነኝ:: ከሃምሳዓመት በላይ በአሜሪካ አገር ስኖር በቆዳዬ ቀለም የደረሰብኝን በደል ስለምረዳ ዘረኝነትንና ጠባብ ጎሰኝነትን አጥብቄ አወግዛለሁ:: ስንወለድ ስው ስንኖር እንደሰውና ስንሞትም እንደሰው እንጂ ሞት ጥቁርን አጥቅቶ ነጭን ምሮ አማራን ጎድቶ ኦሮሞን አልነካም ብሎ ሀብት ያለውን ጠቅሞ ደሃውን በድሎ ለተማረው ሰስቶ መሃይሙን ጨቁኖ ወገናዊነትን የማያሳይ አስተካካይ ፈራጅ ነው:: ሞት እስካለ እኩልነት እንዳለ በመረዳትና የመሬትን እድሜ አጠንጥኜ የሰውን እድሜ ሳሰላስል የተገነዘብኩት የሰው ሕይወት በአንፃሩ ዓይን ድንገተኛ ነገር ገብቶበት ሲቆረቁረው የአይን ሽፋኖች ሳይታሰብ ተዘግተው ወዲያኑ እንደሚከፈቱ ያህል ፈጣን ነው:: ሳናውቀው ኖረን ሳናውቀው እንሞታለን:: ይህንን ለመረዳት የተሳናቸው የአስተሳሰብ ድክመት ያለባቸው ስግብግቦች በሰው መልክ የተፈጠሩ ጅቦች የሚመሯት አገር ኢትዮጵያ መሆኗን ለማየት ችያለሁ::
ሕግን ለማስከበር መጀመሪያ ሕግን የሚያወጣው አመራር ላወጣው ሕግ ተገዢ መሆን ይኖርበታል:: ራሱ ላወጣው ሕግ የማይገዛ አመራር ያለው አገር የሕዝብን አንድነትና የአገርን ሕልውና ማስጠበቅ አይችልም:: ይህን የምልበት ዋናው ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ በፌደራል መንግስትና በክልሎች በተለይ ባየሁት የኦሮሞ ክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ስሩን የዘረጋ ጉቦና ሙስና በትክክል የግል ጉዳይ ማስፈፀም አይሞከርም:: ጉቦሳ ይሰጥ ለማስፈፀም ባለሥልጣን ማወቅ ያስፈልጋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለሙስና ደጋግመው ይናገራሉ:: ግን ከትልቁ ባለስልጣናት እስከ ትንሹ ዘበኛ የእሳቸውን እሮሮታ ሰምቶ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ያለ ነው:: ይህም ሕዝብን መቋቋም የማይችለው ችግር ላይ በመጣል ኢትዮጵያ የብዙሃን በሰላም መኖሪያ ሳትሆን የጥቂቶችና በስልጣናቸው የሚመኩ የሰው አውሬዎች መንደላቀቂያና መስረቂያ ሆናለች:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ለአገሪቱ መልካም ፍላጎት አላቸው:: የሕዝብ አደራ የተጣለባቸው የመንግስታቸው አካል የሆኑ ሹማምንቶችና ሠራተኞች የመልካምና የእኩልነት አስተዳደር መርሆችን ካልተከተሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልካም ፍላጎት ብቻ አስፈላጊውን መልካም ለውጥ አያመጣም::
ወያኔ በመራበት ዘመን ሁለቴ ኢትዮጵያን ጎብኝቻት ነበር:: ምንም እንኳ ወያኔ ራስ ወዳድና ስግብግብ ቢሆንም አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያየሁትን የኦሮሞ ጠባብተኞችን ስግብግብነትን ያህል አላየሁም ነበር:: ከቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ በመላው ኢትዮጵያውያን ልፋት የተሰሩትን ፓርኮች ጀምሮ እስከ አዲስ አበባ ቀበሌ ደረጃ ድረስ የአንድ ጎሳ ዋናነት ያለ እፍረት ጎልቶ ይታያል:: በፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች : በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆነ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ኦሮሞነት የሌለው ኢትዮጵያዊ በምንም ዓይነት በትክክልና የዜጋ መብቱ በሚፈቅድለት መጠን ጉዳይ ለማስፈፀም አይችልም:: ጉቦ ጥያቄው ሃፍረት የሌለበት አይን ያወጣ ማንም የማይቆጣጠረው የአስተዳደር ውድቀት መሆኑን በግልፅ ያሳያል:: ዶ/ር አቢይ አህመድ ለአገር ልዑላዊነትና ለሕዝብ አንድነት የሚሰራ ቢሆንም የተከበበው ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና ለኢትዮጵያ ህልውና የቆሙ ሳይሆኑ በማንኛውም መንገድ የግል ሃብት ለማጋበስ ሒሊናቸውን በሸጡና ስብእና በተሳናቸው አረመኔዎች ነው:: በተለይ የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ ሁለት መልክ ያለው ነው:: ቀን ቀን ብልፅግና ፓርቲን ሲያስተጋባ ማታ ማታ የአረመኔው ሸኔ አካል በመሆን የሸኔን የጎሳ ፖለቲካ በግልፅ የሚያራምድ ውዳቂ ፓርቲ ለመሆኑ ብዙሃን ይናገራሉ:: የኦሮሚያ ክልል የፌደራል ፍርድ ቤት ውሳኔ የማይገበርበት : የፌደራል ሕግ የማይከበርበት ከኦሮምኛ በስተቀር ሌላ ቋንቋ ተናጋሪ እውቀቱን ለግሉ ለሕብረተሰብና ለማህበረሰብ የማይጠቀምበት የጠባብ ጎሰኞች በረት ሆኖ ይታያል:: የሚያሳዝነው እነዚህ ጠባብ ባለተራ ጎሰኞች የዛሬ አራት ዓመት ከወደቀው የወያኔ ቡድን ያለመማራቸውና ያለመገንዝባቸው ምን ያህል የደደቦችና የደንቆሮዎች ስብስብ መሆኑ ነው :: በሄድኩበት አካባቢ የኦሮሞን ብልፅግና ፓርቲንና የወደቀውን የዉያኔን ቡድን ሲያወዳድሩ : ወያኔ የትግርኛ ቋንቋን መናገር አለባችሁ ብሎ የትግራይ ተወላጅ ያልሆነውን ኢትዮጵያውያንን በትግራይ ክልል ውስጥ አላሰቃየም ነበር:: አማርኛን የአገሪቱ የመንግስትና የስራ ቋንቋነትን ያረጋገጠና ያጠናከረ ነበር:: ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ኦሮሞ ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ በተለይ በስመ አማራ የተደረገውና የሚደረገውን ጭፍጨፋ ስናነፃፅር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ትግራይ ሄዶ ውጣ የተባለበትና የተገደለበት ጊዜ ፍፁም አልነበረም ይላሉ:: የኦሮሞ ክልል መሪዎች ትህትናና ሰባዊነት የተሳናቸው አረመኔዎች መሆናቸውን የክልሉ ኗሪዎች በምሬት ይናገራሉ:: ዛሬ ጎልቶ የሚታየው አስቀያሚ የኦሮሞ ተረኝነትና የበላይነት ስሜት ከስሩ በጨቅላነቱ ካልተቀጨ ኢትዮጵያን ወደ1994 የሩዋንዳ እልቂት አይነት ሁኔታ ይመራታል የሚል ፍራቻ ተሰምትኛል:: በዚህ አጋጣሚ የኦሮሞ ሕዝብን ከኦሮ ሞክልል መሪዎች ከሸኔዎችና ከጠባብ ጎሰኞች ለይተን ማየት አለብን:: ለፖለቲካ ጨዋታቸው ሲሉ ጠባብ ጎሰኞችና ፅንፈኞች ለዘመናት በጅምላ አማራውን ሲኮንኑት እንደነበረ ዛሬም የኦሮሞ ጎሰኞችና ፅንፈኞች አማራውን ቤተክርስትያን እንደገባ ውሻ እያደረጉ ሲቀጠቅጡና ሲገድሉ ማየትን መስማት እንደሚያንገበግበን በጥቂት ጠማማና ኢሰብአዊ በሆኑ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ምክንያት ሰፊውን ኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ጎሰኛና ዘረኛ ከማድረግ መቆጠብ ተገቢ ነው:: እንደ ሽመልስ አብዲሳ በአማሪኛ ሲናገር ኢትዮጵያዊ ኦሮምኛ ሲናገር ፀረ-ኢትዮጵያዊ ኬኛ እንደ አያቶላህ ጀዋር ሃይማኖትንና ጎሳን እያቀላቀል ሕዝብ የሚያስፈጅ እንደሸኔ አረመናዊነትን የተጎናፀፈውን ከንፁሁ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ሰፊ ሕዝብ ለይተን ማንነታቸውን ማጋለጥ እንጂ መላውን ኦሮሞ ኢትዮጵያውያንን ከእነዚህ ፀረ-ኢዮጵያዊና ፀረ-አንድነት ኩበቶች ጋር መደመር አግባብ አይሆንም:: እነዚህ ዘረኞች በአማራ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀሙትንና እየፈፀሙ ያሉትን በደል በነዚህ ዶማዎች ምክንያት በኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ላይ መጣል አስፈላጊም ትክክልም አይሆንም::
በወለጋ ውስጥ የተፈፀመውን ግፍ ሳጠያይቅ ጎልቶ የሚሰማው የአማራ ተወላጆች በጠባብ የኦሮሞ ጎሰኞችመጨፍጨፋቸውን ነው:: ግን ስንት ኦሮሞ ኢትዮጵያውያን በሸኔና በጠባብ የኦሮሞ ጎሰኞች እንዳለቁና እንደተጎሳቆሉ አስተዋዮች ይናገራሉ:: አንድን አገር አይቶ ለመገምገም አምስት ሳምንታት በቂ ላይሆኑ ይችላል:: ሆኖም የአንድ አካባቢን የኑሮን ሁኔታን ታዝቦ የአገሪቱን አጠቃላይ ሁኔታ መገምገም አስቸጋሪ አይሆንም:: የአዲስ አበባ የኑሮ ሁኔታ የሸቀጦች ውድነት የሕግ ወጥነት የአንድ ጎሳ በላይነት የአመራር ዝቃጭነት የሕግ አስከባሪ ክፍል ከእኔ ትውልድ ቀጥሎ ያለው ትውልድን አኗኗርንና አስተሳሰብን ሳስተውል ከእኔ ትውልድ አናኗር ተሽሏል የምለው ነገር አይቻለሁ ለማለት አልደፍርም:: አኗኗር ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል:: በመጀመሪያ የሰው ልጅ በሕይወት ለመኖር መሰረታዊ የሆነ ምግብ ማግኘት አለበት:: የአገሪቱን የምግብ አቀራረብ ስመለከት : የምግብ ምርት ካለው የሕዝብ ቁጥር እድገት ጋር የሚመጣጠን እንዳልሆነ ልታዘብ ችያለሁ:: ላለው የምግብና የኑሮ ውድነት ያለውን መንግስት መውቀስ ፍታዊ ነው ብዬ አላስብም:: የኢትዮጵያ ነጋዴዎች ምን አይነት ጨካኞችና አረመኔዎች እንደሆኑ ልገነዘብ ችያለሁ:: እነዚህ ስግብግብና ገንዘብ ወዳድ ጅብ ነጋዴዎች በሚያደርጉት ሻጥር መታሰር ብቻ ሳይሆን በሻጥር ያካመቹትን ሃብት መወረስ ያለባቸው የአገር ጠላቶች ናቸው::
ሌላው አሳዛኝ ትዝብቴ የሐኪሞች ስግብግብነትና ገንዘብ በመውደድ ለሰው ልጆች ሕይወት ዋጋ አለመስጠታቸው ነው:: በየትኛውም አገር ሕዝብን በአግባብ አክመው ከሕመማቸው ለማዳን በማሉበት ማላ መሰረት የሚጥሩ ሐኪሞች እንዳሉ ሁሉ ስብእናና ርህራሄ ያላቸው ሙያቸውንና የማዳን ተልእኳቸውን እንጂገንዘብ የማያስቀድሙ እውነተኛ ሐኪሞች በኢትዮጵያም እንዳሉ እገነዘባሁ:: የእነዚህ ሃቀኛ ሐኪሞች ችግር አስፈላጊ የሕክምና መሳርያዎችና መድኃኒቶች እጥረት ነው:: ሆኖም የማሉበትን የኢፖክራትያን ማላ ተልእኮ ረግጠው ገንዘብ ላይ በማተኮር በሽተኛ ከማዳን ይልቅ ገንዘብ ለመስራት ያልሆነና ጊዜው ያለፈበት መድኃኒት በመስጠት ሰው እየጨረሱ ያሉ ሐኪሞች እንደ አሸን እየፈሉ ነው:: መንግስት ይህንን ሊቆጣጠር ያልቻለበት ምክንያት ምን ይሆን? እስከመቼ ድረስ በሐኪሞች ስግብግብነት ምክንያትና በመንግስት ቸልተኝነት ሕዝብ በተሳሳተ ምርመራ አግባብ ባልሆነ ሕክምናና ጊዜው ባለፈበትና በተሳሳተ መድኃኒት ሕዝብ ሊታከም ሄዶ መሞት ያለበት? የማዲንጎ አፈወርቅ ነድቶ ክሊንክ ሄዶ መሞት ሐኪሞችን ኪሊኒኮችንና ሆስፒታሎችን ተጠያቂ ለማድረግ ጤና ጥበቃ ሚኒስትሪ መመሪያዎች እንዲያወጣ መነሽያ ሊሆን ይችላል:: አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ታዋቂ ስለሆነ ሞቱ ሊታወቅ ችሏል:: ግን ስንቱ ደሃ ኢትዮጵያውያን በሐኪሞች እጅ ያላግባብ በየቀኑ የሚያልቀው? ጥሩ ሐኪሞች ሙያቸውን ማስከበር የሚችሉት ስግብግቦችንና ስብእናና ሰባዊነት የተሳናቸውን ሐኪሞች ከመሃላቸው ጦቁመው ሲያወጡ ነው:: የሐኪሞች ተጠያቂነት የሌለው አገር የሕዝብን ጤና በአግባብ ያስጠብቃል ለማለት አያስደፍርም::
ሌላው የታዘብኩት ነገር የአገርን ኢኮኖሚ የሚያቃውስ የኑሮን ውድነት ከሚፈጥሩት ምክንያቶች አንዱ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለጥቁር ገበያ ምንዛሬ መስፋፋት በቂ ሚና ይጫወታል:: ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ ለመላክ የጥቁር ገበያ ምንዛሬ አንድ ዶላር መቶ የኢትዮጵያ ብር ደርሷል:: ይህንን የጥቁር ገበያ የሚያካህዱት አብዛኛዎቹ ሱማሌዎች ቢሆኑም : ጁንታው ከመውደቁ በፊት ከኢትዮጵያውያኖች አብዛኛዎቹ የትግራይ ተወላጆች ነበሩ:: አሁንግን የኦሮሞ ተወላጆች ጥቁር ገበያ ምንዛሬውን በየስቴቱ እያጦፉት ይገኛሉ:: ይህ ነው የባለጊዜ ጥቅም:: ዶክተር አቢይ አህመድ ይህንን አያውቅም ብዬ በእርግጠኝነት ለመናገር አልችልም:: ዶክተር አቢይ አህመድ በሚናገረው የሽንገላ ቃላቶች እታለል ነበር:: እያደርኩኝ ሳሰላስል ቁም ነገር የሌላቸው የድለላ ቃላቶች መሆናቸውን እየተረዳሁ መጣሁ:: ይህንን ያልኩበት ምክንያት ይህንን ያህል የጥቁር ገበያ ምነዛሬ ሲካሄድ የመረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደርን (Information Network SecurityAdministration)ን በኢትዮጲያ ያቋቋመ ግለሰብ ይህንን የጥቁር ገበያ ምንዛሬ ሂደት አያውቅም ለማለት አልደፍርም:: ይህ የጥቁር ገንዘብ ምንዛሬ በእርግጠኝነት ከኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ጉሮሮ በስግብግብ የኦሮሞ ክልል መሪዎች ከክልሉ እየተሰረቀ የሚወጣ ነው:: ይህንን ለመቆጣጠር መንግስት ምን ያህል እንደሚሞክር አላውቅም:: ለዚህም አገር ጎጂ ድርጊት የዲያስፖራው ኢትዮጵያውያን ተባባሪዎች ናቸው:: አዎን እነዚህ ዲያስፖራዎችቤተሰቦቻቸውን አገር ቤት ይረዱበታል:: ግን መረዳት ያቃታቸው የጥቁር ገበያ ምንዛሬ እዚሁ አገር ይቀርና አገራችንን የውጭ ምንዛሬ በማሳጣት ድርጊታቸው የዋጋ ግሽበት ላይ ሚና በመጫወት አገር ቤት ባሉት ቤተሰቦቻቸው ላይ የኑሮ ውድነት ማምጣቱን ነው:: ሌላው መንግስት ወዲያውኑ ማድረግ የሚችለው ከአገር ውጭ ያሉት ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያ ውስጥ ቤትም ሆነ ሌላ ንብረት ሲገዙ መግዣው ገንዘብ በባንክ መግባቱን ማረጋገጫ መጠየቅ ይኖርበታል:: አሥር ሃያ ሰላሳ ዓመታት በዲያስፖራ ተቀምጦና እየተቀመጠ ኢትዮጵያ ቤት ሲገዛ የሚገዛበት ገንዘብ ከየት መጣ? እንዴት አገር ቤት ገባ? ይህንን ጥያቄ መንግስት ስራ ላይ ካዋለ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በጥቂቱ የጥቁር ገበያ ምንዛሪን ሊመታ ይችላል:: ዲያስፖራዎች በጥቁር ገበያ ምንዛሬ ገንዘብ በማስገባት ቤት ሲገዙ ቤት እየተወደደ የአገሪቱ ኗዋሪዎች የመግዛት አቅም እያጡ ይገኛሉ:: ኢትዮጵያ ምን ያህል በኢኮኖሚ ብታድግ ነው የቤት ዋጋ ከምኖርበት ከአሜሪካን ዋያሚንግ ስቴት በላይ ሊሆን የቻለው? ስንት ኢትዮጵያዊ ነው የአንድ መቶ ሺ ዶላር ቤት መግዛት የሚችለው? ኢትዮጵያ ውስጥ ዲያስፖራዎች ቤት ለመግዝት ከፈለጉ ገንዘባቸውን በባንክ እንዲያስገቡ መንግስት ሕግ ካወጣ በከፊሉ የጥቁር ገበያ ምንዛሬን መቆጣጠር ይችላል የሚል ግምት አለኝ::
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ብዙ የኢትዮጵያን ችግሮች መፍትሔ መፈለግ ላይችሉ ይችላሉ:: ግን ከገንዘብ ለዋጪዎች ጋር የሆነ ግኑኝነት ባይኖሮትም የጥቁር ገበያ ምንዛሬን ለመግታት ችሎታ እንዳሎት እረዳለሁ::
ኢትዮጵያ ሰው ለሰው የሚተሳሰብበት የሰላም የእኩልነትና የአንድነት አገር እንድትሆን ፈጣሪ ይርዳን!!
__
በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ