
ቦርከና
በሩሲያ ምክር ቤት (ዱማ) አባል እና በዱማው የጤና ኮሚቴ ነባር አባል የሆኑት ሰርጌ ሊዮኖቭ በብቸኝነት ዙሪያ የሚሰራ መንግስታዊ ኤጀንሲ እንዲቋቋም ጥሪ አቀረቡ።
የሩሲያው አር ቲ የሃገሪቱን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ጠቅሶ ከትላንት በስቲያ እንደዘገበው ሰርጌ ሊዮኖቭ ከአምስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሩሲያውያን ከአእምሮ ህመም ጋር እየታገሉ ነው በሚል በመረጃ የተደገፈ መከራከሪያ አቅርበዋል።
የመንግስታዊው ተቋም መቋቋም ከተረጋገጠ የብቸኝነት ችግር ጋር ተያያዥነት ያለውን የአእምሮ ህመም እንዲቋቋሙ ያግዛል የሚል አቋም አንጸባርቀዋል። አያይዘውም አገልግሎቱ በመንግስት ደረጃ ለህዝብ ተደራሽ መሆን አለበት በማለት ተከራክረዋል።
በእንግሊዝ አና በጃፓን በብቸንነት የሚሰቃዮ ሰዎችን ችግር ለማገዝ በሚኒስተር ደርጃ ተቋማት መመስረታቸውንም ጠቁምዋል።
በእንግሊዝ ሃገር እንደ አውሮፖውያኑ አቆጣጠር በ2018 የብቸኝነት ሚኒስተር መቋቋሙን እና ዘጠኝ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የችግሩ ተጠቂ እንደሆኑም በዘገባው ተጠቁሟል።
ምንጭ : አር ቲ
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ