
ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት
ዋሽንግተን ዲሲ
ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት በእዉቁና ታላቁ ኢትዮጵያዊ ምሁር ፕሮፌሰር ወሰኔ ይፍሩ እረፍት የተሰማውን መሪር ሀዘን ለቤተሰብ ለአገር እና ለወገን ሁሉ ለመግለፅ ይወዳል::
ፕሮፌሰር ወሰኔ ይፍሩ ከልብ በሚወዷት አገራቸው ኢትዮጵያ እውነተኛ ለውጥ እንዲመጣ፤ ፍትህ እንዲሰፍን፤ እኩልነት በተግባር እንዲረጋገጥ ደከመኝና ሰለቸኝ ሳይሉ የተቻላቸውን ሁሉ ሲያደርጉ ነበር::
ሕገ-መንግስት በመደንገግ አማራውን በተለየ-መልኩ ለማዳካም፤ ብሎም ለማጥፋት እየተካሄደ ያለውን ፀረ አማራዊ መጠነ ሰፊ ዘመቻ በመረዳታቸው፤ አማራው የተጋረጠበትን አደጋ ተባብሮ እንዲመከት ሲያስተምሩ፣ አጥብቀውም ሲመክሩ ነበር።
በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፤ በተንኮል የተሸረበው ጎሳንና ቋንቋን መሠረት ያደረገው ሕገ-መንግስት በአዲስ ሕገ-መንግስት እንዲለወጥ ብዙ ደክመዋል። ለጠቅላይ ሚንስትሩም ጥልቅና ሰፊ ደብዳቤ ልከው ነበር።
በሚዲያ እየቀረቡም ሃሳባቸውን ለሕዝብ አቅርበዋል።
ይህን አስተዋፅዖ ማንኛውም አማራ ብሎም ፍትሕና እኩልነት ናፋቂው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሲያስታውሰውና ሲዘክረው ይኖራል።
ፕሮፌሰር ወሰኔ ይፍሩ ብዙ መፅሃፍትን ጽፈው ለትውልድ መማሪያነት አስተላልፈዋል። ታሪካችንን ከስሩ እንድናውቅም ጥረት አድርገዋል። ለዚህም አስተዋጽዖአቸው እናመሰግናቸዋለን።
በዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት ከምስረታው ጀምሮ በተለያዩ ኃላፊነቶች በንቃትና በትጋት ስለሰሩ አጥብቀን እናመሰግናለን። ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት፤ ፕሮፌሰር ወሰኔን የመሰለ ትልቅ ምሁር ማጣቱ ከባድ ሀዘን ነው፡፡ ነገር ግን የሚገባውን በመፅሃፍ ስላስተላለፉልን በዚህ ስራቸው ስንዘክራቸውና ስራዎቻቸውን ለትውልድ ለማስተላለፍ ቃል እንገባለን፡፡
በመጨረሻም ለውድ ቤተሰባቸው፤ ዘመድ ጓደኞቻቸው፤ የስራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እግዚአብሔር መፅናናቱን እንዲሰጣችሁ እንለምናለን።
ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት
ዋሽንግተን ዲሲ

__
በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
መቸ? እንዴት? የት? ሞቱ፤ የት ተቀበሩ? ቤተ ሰብ አላቸው? ፕሮፌሰርነታቸው በየትኛው ትምህርት ቤት ነው? ጨርሶ ትዝም አላላችሁም! አይ ጋዜጠኛነት!