spot_img
Monday, December 4, 2023
Homeአበይት ዜናበመቶዎች የሚቆጠሩ ንጽሁን በወለጋ ሌላ ዙር የዘር ማስዳት ጥቃት አንደደረሰባቸው ተሰምቷል

በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጽሁን በወለጋ ሌላ ዙር የዘር ማስዳት ጥቃት አንደደረሰባቸው ተሰምቷል

advertisement
በወለጋ ሌላ ዙር የዘር
በወለጋ በዚህ ሳምንት የደረሰውን የዘር ፍጂት ተከትሎ በማህበራዊ ድረ ገጽ በስፋት ከተዘዋወሩት ፎቶ ግራፎች አንዱ ነው:: ልጂ ይዛ ብቻዋን ትታያለች ፤ባለቤቷ አጠገቧ አይታይም::

ቦርከና

በያዝነው ሳምንት በወለጋ ዞን ሌላ አሰቃቂ እና አሳዛኝ የተባለ ጭፍጨፍ በንጹን ላይ አንደተፈጸመ ተሰምቷል :: አንግር ጉተን ከተማ በደረሰው ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹን በአሰቃዊ ሁኔታ እንደተገደሉ እየተነገረ ነው::

በማህበራዊ ሚዲያ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የዚህ ሳምንቱን ከዚህ በፊት ከደረሱት እልቂቶች ለየት የሚያደርገው የኦሮሚያ ክልል ልዮ ኃይሎች በግላጭ መንግስት ራሱ ኦነግ ሼኔ እያለ ከሚጠራው አካል ጋር በቅንጂት ጥቃቱን መፈጸማቸው ነው::

አንድ የአካባቢው ነዋሪ ነኝ ያለ ከኢትዮጵያ ሚዲያ አገልግሎት ጋር ትላንት በስልክ ባደረገው ቆይታ ታጣቂው ቡድን እና የኦሮሚያ ልዮ ኃይል አካባቢውን “የዶጋ አመድ አድርገውታል” ሲል ገልጿል::

በስልክ ሲያወራ በነበረበት ሰዐት ይሰማ የነበረውን የተኩስ ልውውጥ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ እንደሚያመላክት ገልጾ እሱ ራሱ ውንድሙ እንደተገደለበት ተናግሯል::

እስካሁን ድረስ የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት በግልም ይሁን እንደ መንግስት አካል የከፋ ነው ስለተባለለት የዘር ፍጂት የሰጡት አስተያየት የለም::

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ “በወለጋ አስከፊ ጦርነት እየተካሄደ ነው” በሚል ሁኔታውን ገልጾታል::

በደረሰው የዘር ፍጂት ዙሪያ አብን መግለጫ አውጥቷል:: ጭፍጨፋው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቶ አደገኛ ወደ ሆነ ደረጃ መሸጋገሩን አንስቷል::

“የኦሮሚያ ክልል መንግስት በወለጋ እና ሌሎች አካባቢዎች በንፁሃን አማሮች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ፣ ማፈናቀል፣ እገታ እና ንብረት ዝርፊያ ለማስቆም ፍላጎት እና አቅም እንደሌለው በተደጋጋሚ ጊዜ ታይቷል፣ ቀላል የማይባለው የክልሉ መዋቅርም የጭፍጨፋው ተሳታፊና ሽፋን ሰጭ ሆኗል” በማለት የፌደራሉ መንግስት ባስቸኳይ ጣልቃ እንዲገባ አና የዜጎችን ደህንነት እንዲታደግ ሲል ጥሪ አቅርቧል ::

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንም ይሁን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ይሄ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በጉዳዮ ላይ የሰጡት መግለጫ የለም::

አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸውን ተከትሎ በኤርትራ የነበሩ የኦነግ ተዋጊዎች ለሰላማዊ ትግል በሚል ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ከተደረገ ጀመሮ ባለፉት አራት እና አምስት አመታት ብቻ በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን በግፍ ማለቃቸው ይታወቃል ፤ በሚሊዮን የሚገመቱ አርሶ አደሮች ደሞ ከኦሮሚያ ክልል ከተለያየ አካባቢ እንዲፈናቀሉም ተደርጓል::

_

__

በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here